መማር ምን ማለት ነዉ? ተማረ ወይም ተማረች ማለት ምን ማለት ነዉ?
Posted: 16 Aug 2023, 18:59
ኣንድ የኢትዮጵያ ኣቀንቃኝ ተማር ልጄ ብሎ ይመክራል።
ከምክሩ ባሻገር መማር ማለት ምን ማለት ነዉ? ተማረ ወይም ተማረች ማለት ምን ማለት ነዉ?
እነዚህ ቀላል ጥያቄዎች ይመስለሉ። ኣንዱ ተነስቶ ተማር ብሎ ሆዬ ቢል ብዙዎች ተነስተዉ ሆያ ሆዬ ሊሉ ይችላሉ።
ግላዊ ሳይሆን ቁሳዊ የሆነ መለኪያዉ ምንድነዉ? በእንግሊዘኛ ቋንቋ አነጋገር ሰብጄክቲቭ ሳይሆን ኦብጄክቲቭ የሆነ መለኪያዉ ምንድነዉ?
የህይወት ትምህርት ሰዉ ከተወለደ ግዜ ጀምሮ እስከዕለት ሞቱ የሚማረዉ ነዉ። ህይወት እራሱ እስከመጨረሻዉ የማያቆም ትምህርት ቤት ነዉ።
መደበኛ ትምህርት በአምስት አከባቢ መደበኛ ደረጃዎች ተከፍሎ ያስተምራል። ኣንደኛ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ፣ ለመጀመርያ ድግሪ፣ ለሁለተኛዉ ድግሪ፣ እና ለመጨረሻ ድግሪ።
ሙያ ተኮር ትምህርት ጥልቀት ኖሮት የተለየ ሊሆን ይችላል። ስለተፈጥሮ ሳይንስ የተማረ ስለሰብ ያልተማረ ወይም ስለሰብ ተምሮ ስለ ተፈጥሮ ሳይንስ ያልተማረ ሙያ ተኮር ትምህርት ተማር ብሎ መምከር ተገርቢ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ ተማር ማለት ምን ማለት ነዉ? ስለየትኛዉ ትምህርት ነዉ? ማንስ ነዉ ስለየትኛዉ ትምህርት ተማር ማለት የሚችለዉ?
የህይወት ትምህርት እና መደበኛ ትምህርት ተምሬ ልምድ ኣለኝ። ኣስተምሬ ልምድ ኣለኝ። ሰርቼ ልምድ ኣለኝ።
እነዚህ ልምዶች ለተማር ባዮች ምን ያስተምሩ ይሆን? ለተማር ባይ ሆዬዎች እና ሆያ ሆዬዎች ምን ያስተምሩ ይሆን?
ለተማር ባዮች ሊጠቅሙ ስለሚችሉ ላካፍል። ከቀላል እስከ ዉስብስብ አስተሳሰብ ኣለባቸዉ።
የኢትዮጵያን የትምህርት ተቋማት ማን ለፍቶበት እንዳቋቋመዉ በዉል ባላዉቅም የሚደነቅ ለመሆኑ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ልምዶች ይመስሉኛል። ሌሎች ልምዶችም ሲጨመሩበት ይዳብራል። ዋናዉ አላማ መሆን ያለበት ይህ ነዉ።
ኣንደኛ ደረጃ ትምህርት ጀምሬ ሳምንታት ሳልቆይ ከኣንድ ክፍል ወደሚቀጥለዉ ክፍል ለብቻ ተለይቼ ኣልፌኣለሁ።
ሶስተኛ ክፈል ባገኘሁት ዉጤት አረተኛ ክፍልን ዘልዬ አምስተኛን ተምሬኣሉ። በመጀመርያዉ ሰምስተር ባገኘሁት ዉጤት ሁለተኛ ሰምስተርን ስድስተኛ ከፈል ተምሬ ብሔራዊ ፈተና እንድወስድ ተጠይቄ ገና እንደተጠየኩኝ፣ ማንንም ሳላማክር፣ እምቢ ብዬኣለሁ።
ሁለተኛ ከፍተኛ ደረጃ እያለሁ የህንድ ኣስተማሪ የህሳብ ጥያቄን ክፍል ዉስጥ ስትሳሳት ኣስተዉዬ ተማሪዎች ፊት እንድታርም ኣድርጌኣለሁ።
ሶስቱንም ብሔራዊ ፈተናዎችን ወስጄ ኣልፌኣለሁ።
ኮሌጅ ገብቼ ተምሬኣለሁ።
የካልኩለስ አስተማሪ የህሳብን ጥያቄ መፍታት ወይም ሶልቭ ማድረግ ግራ ሲገባዉ ተማሪዎች ፊት መንገዱን ኣስረድቼዋለሁ።
ከፍተኛ ደረጃ አሜርካ ዉስጥ ስማር ኣንድ ፕሮፌሰር ኣንድ ለእኔ ቀላል የመሰለኝን የእንተግሬሸን ጥያቄ ክፍል ዉስጥ ኣምጥታ እስቲ ኣብረን እንፍታዉ ስትል መንገዱን ኣሳይቼኣታለሁ። ከሁሉም የገረመኝ ኣምና እንዲሁ ክፍል ዉስጥ ሞክራን ኣልፈታንም ማለቷ ነበር። የኣሜርካ ፕሮፈሰር ሆና ኣንድ ቀላል የመሰለኝን የእንተገሬሽን ጥያቄ ላይ ኣንድ ዐመት ሁሉ መተኛቷ ነዉ።
ክፍሉ ዉስጥ የነበረ ኣንድ የፓኪስታን ሃገር ባለሙያ ከቀናት በኋላ ከቡታን የመጣ ጓደኛዬ ፊት ኢትዮጵያዊ መሆኔን መገመቱን እና ኣላን ኣለን የሚሉትን የኣሜሪካ ፕሮፌሰሮች እንደዛ መንገድ ስለማሳየቱ ኣጫዉቶኝ ነበር።
ሌላ ዕዉቅ የእንደስትርያል ኢንጂነሪግ ፕሮፌሰር የሰጠዉ የቤት ስራ ዉስጥ ኣንድ ጥያቄ ስህተት እንዳለዉ ኣስተዉዬ ቢሮዉ ሄጄ ሳስረዳዉ ተከራከረኝ። በኋላ ክፍል መጥቶ ስለጥያቄዉ ስህተተ በማይመስል ሁኔታ ለማስረዳት ሲሞክር ፍጹም ገርሞኝ በሆዴ ትዝብት ነዉ ትርፉ ብዬ ኣለፍኩኝ። ግምቴ ስህተቱ ያልገባዉ ሳይሆን እርምቱ ከእኔ መምጣቱን ኣለመፈለጉ እና የመጽሓፉን ጸሓፊ እና ኣሳታሚ ላለማሳጣት ነበር ነዉ።
ኣንዱን ትምህርቴን ጨርሼ ሌላዉን እስክጀምር የኣንድ የትምህርት መጽሓፍ ወይም ቴክስትቡክ ጥያቄዎችን እና መልሶችን ኣዘጋጅቻለሁ። ያረካኝ ስራ ነበር። ይሀን ስራ ስሰራ የኣሜርካ የመንግስት ተቋም ያሳተመዉ መጽሓፍ ዉስጥ ስህተት ኣስተዉዬ ከፕሮፌሰሬ ጋር ተወያይተን ኣርሜኣለሁ።
መጽሓፉ ከነጥያቄዎቹ መልሶች መጽሓፍ ወይም ሶሉሽንስ ማኑዋል ለህትመት በቅተዋል። ዛሬ መጽሓፉ ሶስተኛ እትም ላይ ደርሷል።
አሜርካ የሰራሁት የመጀመርያዉ ስራ ዉስጥ ሳምንታትን ሳልቆይ ኣንድ የኣሜሪካ ኣማካሪ የሰራዉን ስራ ማየት ወይም ሪቪዉ እንዳደርግ ተመደብኩኝ። የመደበኝ አለቃዬ የተማረ ነዉ። ያዉም እስከ መጨረሻ። እሱም ስራዉን ኣይቶት ወይም ሪቪዉ ኣድርጎት እኔ ያላየሁትን ስህተት ኣለዉ ኣለ። እኔ ዬለዉም ኣልኩኝ።
ኣማካሪዉ የተጠቀመዉን ፎርሙላ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለሁ እንዴት እንደሚወጣ የተማርኩኝ ነዉ። ፎርሙላዉን ማዉጣት አምስት ደቂቃ ኣያስፈልግም።
አለቃዬ ሸምድዶ የምያስታዉሰዉ ፎርሙላ ነበር። የታወቀ ሃንድቡክ ዉስጥ የታተመ። ያም ፎርሙላ ልክ ነዉ። ኣማካሪዉ የተጠቀመዉም ፎርሙላ ልክ ነበር። ልዩነታቸዉ ከሁለት ኣንግሎች የትኛዉን መርጠዉ በመነሳት ነዉ ፎርሙላዉን ያበጁት ነዉ።
ኣማካሪዉ የተጠቀመዉን ፎርሙላ እንዴት ማዉጣት እንዳሚቻል ለአለቃዬ እያስረዳሁት ግትር ብሎ ከእኔ ጋር ክርከር ሆነ። እኔን ግትር ወይም ስተቦርን እስከማለትም ደረሰ። ግራ ገብቶኝ ብዙም ሳልቆይ እሱ ለአለቃዉ ስህተት ነዉ ብሎ ተናግሮ ኣይ ስህተት ኣይዴለም መባል እንዳይባል መፈለጉ መሰለኝ። ያ ገጠመኝ ሲገርመኝ ይኖራል።
ኣማካሪዉ ያቀረበዉ ጥናት በብልዮን ዶላሮች ከሚቆጠር የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚረዳ ነዉ። ሁለተኛ ደርጃ ትምህርት ቤት ዉስጥ የተማርኳት ቀላል የምትመስል የጂኦሜትሪ ፎርሙላ እንደዚህ አይነት ጥቅም ላይ ትዉላለች። ሀሳብን ከስራ አገልግሎት ወይም ትኦሪን ከፕራክቲስ ጋር ኣያይዞ ማስተማር ኢትዮጵያ ዉስጥ በሰፊዉ ቢለመድ።
ሌላ ቦታ ስራ ጀምሬ ወራትን ሳልቆይ ለስራዉ ቦታ የሚመጥን የመሰለኝን የአሰራር ደንብ እንድያሳዩኝ ጠየኩኝ። ስራ ላይ የዋለ ኣንዱ የሳይንቲስቱ ኒዉተን ደንብ ነዉ። ስለደንቡ የኢትዮጵያ ኮሌጅ ዉስጥ ተምሬ ኣበጥሬ የገባኝ ነዉ።
ጥያቄዉን የጠየኩት ሰዉ ስለምን እንደጠየኩት በደንብ የገባዉ ኣይመስለኝም። ቦታዉ የቢልዮኖች ዶላሮችን ኦኮኖሚ ለማንቀሳቀስ የሚረዳ ፕሮጀክት ያለበት ነዉ። ስራዉ ላይ የተማሩ የተሰማሩበት ነበር። እስከ መጨረሻ የተማሩ የነበሩበት።
ለጥያቄዬ መልስ ማጣት ገርሞኝ ለብቻዬ ዚስ ፕሌስ ሃዝ ኤ ፕሮብሌም ብዬ ተነፈስኩኝ። ግርማቱ እና ይህን ለራሴ ስናገር የት ቦታ እንደነበርኩኝ ሁሌም ከፊቴ ኣይጠፋም።
ከዛ ግርምት በኋላ ነበር ስራዉን እራሴ ሰርቼ ባሳይ የሙያ ትርፍ ይኖረዋል ብዬ ያሰብኩኝ። እንዲሰራ እየወተወትኩ ቆይቼ በኋላ የራሴን ግዜ በመጠቀም እና በቤቴ ጭምር ሰርቼ ለጆርናል ወረቀት ህትመት ኣበቃሁ። የኢትዮጵያ ኮሌጅ ዉስጥ ተምሬ፣ ኣሜሪካ ደርሼ ጠይቄ ያላገኘሁትን ስራ ላይ መዋል የነበረበትን ጽንሰሀሳብ ቁልጭ ኣድርጌ ኣሳየሁ።
የጆርናል ወረቀቱ በማያዉቁኝ ፕሮፌሰሮች ታይቶኣል ወይም ሪቪዉድ ተደርጓል። ኣንዱ የፀሓፊዉን ችሎታ ኣደንቃለሁ። ይታተም ነዉ ያለዉ። የመጀመርያዉ ፅሑፍ ላይ ምንም ኣልጨመረበትም። ምንም ኣልቀነሰም።
ዚስ ፕሌስ ሃዝ ኤ ፕሮፕሌም ላልኩት የማያዉቀኝ ፕሮፌሰር እንዲህ ማለቱ እንደ ሙያ ትርፍ ኣልሜዉ የነበረዉ ብዬ ነዉ ያለፍኩት።
የኣንድ ግለሰብ ብቻ ቢሆኑም እነዚህ የመማር እና የስራ ልምዶች ምንን ያማለክታሉ? መረባረብ ትምህርት ላይ ነዉ ብዬ ላቀረብኩኝ ሀሳብ ገንቢ ሊሆኑ ይችላሉ?
መደበኛ ትምህርት ምን እንደሆነ በትንሹም ቢሆን ግልጽ ልያደርጉ ይችላሉ? ኣንድ ተማሪ ከስንት ኣስተማሪዎች ተምሮ ወይም ተምራ ነዉ ተማረ ወይም ተማረች የሚባለዉ?
በምህንድስና ትምህርት ዉስጥ የተጠቀሱት ሁለት መሠረታዊ ደንቦች ወይም ፎርሙላዎች በቢልዮኖች ዶላሮች ለሚንቀሳቀሱ ፕሮጀክቶች የሚሆኑ ከሆነ ኣንድ ተማሪ ለስራ ስንት ፎርሙላዎችን ነዉ መማር ያለበት? የተመራማሪ ለብቻ ነዉ።
ስለዚህ እነዚህ ልምዶች የሚጠቅሙ ከሆነ እነሆ። መነዛነዝ ከሆነም ሌላ መነዛነዝ ነዉ።