ኣንድ የኢትዮጵያ ኣቀንቃኝ ተማር ልጄ ብሎ ይመክራል።
ከምክሩ ባሻገር መማር ማለት ምን ማለት ነዉ? ተማረ ወይም ተማረች ማለት ምን ማለት ነዉ?
እነዚህ ቀላል ጥያቄዎች ይመስለሉ። ኣንዱ ተነስቶ ተማር ብሎ ሆዬ ቢል ብዙዎች ተነስተዉ ሆያ ሆዬ ሊሉ ይችላሉ።
ግላዊ ሳይሆን ቁሳዊ የሆነ መለኪያዉ ምንድነዉ? በእንግሊዘኛ ቋንቋ አነጋገር ሰብጄክቲቭ ሳይሆን ኦብጄክቲቭ የሆነ መለኪያዉ ምንድነዉ?
የህይወት ትምህርት ሰዉ ከተወለደ ግዜ ጀምሮ እስከዕለት ሞቱ የሚማረዉ ነዉ። ህይወት እራሱ እስከመጨረሻዉ የማያቆም ትምህርት ቤት ነዉ።
መደበኛ ትምህርት በአምስት አከባቢ መደበኛ ደረጃዎች ተከፍሎ ያስተምራል። ኣንደኛ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ፣ ለመጀመርያ ድግሪ፣ ለሁለተኛዉ ድግሪ፣ እና ለመጨረሻ ድግሪ።
ሙያ ተኮር ትምህርት ጥልቀት ኖሮት የተለየ ሊሆን ይችላል። ስለተፈጥሮ ሳይንስ የተማረ ስለሰብ ያልተማረ ወይም ስለሰብ ተምሮ ስለ ተፈጥሮ ሳይንስ ያልተማረ ሙያ ተኮር ትምህርት ተማር ብሎ መምከር ተገርቢ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ ተማር ማለት ምን ማለት ነዉ? ስለየትኛዉ ትምህርት ነዉ? ማንስ ነዉ ስለየትኛዉ ትምህርት ተማር ማለት የሚችለዉ?
የህይወት ትምህርት እና መደበኛ ትምህርት ተምሬ ልምድ ኣለኝ። ኣስተምሬ ልምድ ኣለኝ። ሰርቼ ልምድ ኣለኝ።
እነዚህ ልምዶች ለተማር ባዮች ምን ያስተምሩ ይሆን? ለተማር ባይ ሆዬዎች እና ሆያ ሆዬዎች ምን ያስተምሩ ይሆን?
ለተማር ባዮች ሊጠቅሙ ስለሚችሉ ላካፍል። ከቀላል እስከ ዉስብስብ አስተሳሰብ ኣለባቸዉ።
የኢትዮጵያን የትምህርት ተቋማት ማን ለፍቶበት እንዳቋቋመዉ በዉል ባላዉቅም የሚደነቅ ለመሆኑ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ልምዶች ይመስሉኛል። ሌሎች ልምዶችም ሲጨመሩበት ይዳብራል። ዋናዉ አላማ መሆን ያለበት ይህ ነዉ።
ኣንደኛ ደረጃ ትምህርት ጀምሬ ሳምንታት ሳልቆይ ከኣንድ ክፍል ወደሚቀጥለዉ ክፍል ለብቻ ተለይቼ ኣልፌኣለሁ።
ሶስተኛ ክፈል ባገኘሁት ዉጤት አረተኛ ክፍልን ዘልዬ አምስተኛን ተምሬኣሉ። በመጀመርያዉ ሰምስተር ባገኘሁት ዉጤት ሁለተኛ ሰምስተርን ስድስተኛ ከፈል ተምሬ ብሔራዊ ፈተና እንድወስድ ተጠይቄ ገና እንደተጠየኩኝ፣ ማንንም ሳላማክር፣ እምቢ ብዬኣለሁ።
ሁለተኛ ከፍተኛ ደረጃ እያለሁ የህንድ ኣስተማሪ የህሳብ ጥያቄን ክፍል ዉስጥ ስትሳሳት ኣስተዉዬ ተማሪዎች ፊት እንድታርም ኣድርጌኣለሁ።
ሶስቱንም ብሔራዊ ፈተናዎችን ወስጄ ኣልፌኣለሁ።
ኮሌጅ ገብቼ ተምሬኣለሁ።
የካልኩለስ አስተማሪ የህሳብን ጥያቄ መፍታት ወይም ሶልቭ ማድረግ ግራ ሲገባዉ ተማሪዎች ፊት መንገዱን ኣስረድቼዋለሁ።
ከፍተኛ ደረጃ አሜርካ ዉስጥ ስማር ኣንድ ፕሮፌሰር ኣንድ ለእኔ ቀላል የመሰለኝን የእንተግሬሸን ጥያቄ ክፍል ዉስጥ ኣምጥታ እስቲ ኣብረን እንፍታዉ ስትል መንገዱን ኣሳይቼኣታለሁ። ከሁሉም የገረመኝ ኣምና እንዲሁ ክፍል ዉስጥ ሞክራን ኣልፈታንም ማለቷ ነበር። የኣሜርካ ፕሮፈሰር ሆና ኣንድ ቀላል የመሰለኝን የእንተገሬሽን ጥያቄ ላይ ኣንድ ዐመት ሁሉ መተኛቷ ነዉ።
ክፍሉ ዉስጥ የነበረ ኣንድ የፓኪስታን ሃገር ባለሙያ ከቀናት በኋላ ከቡታን የመጣ ጓደኛዬ ፊት ኢትዮጵያዊ መሆኔን መገመቱን እና ኣላን ኣለን የሚሉትን የኣሜሪካ ፕሮፌሰሮች እንደዛ መንገድ ስለማሳየቱ ኣጫዉቶኝ ነበር።
ሌላ ዕዉቅ የእንደስትርያል ኢንጂነሪግ ፕሮፌሰር የሰጠዉ የቤት ስራ ዉስጥ ኣንድ ጥያቄ ስህተት እንዳለዉ ኣስተዉዬ ቢሮዉ ሄጄ ሳስረዳዉ ተከራከረኝ። በኋላ ክፍል መጥቶ ስለጥያቄዉ ስህተተ በማይመስል ሁኔታ ለማስረዳት ሲሞክር ፍጹም ገርሞኝ በሆዴ ትዝብት ነዉ ትርፉ ብዬ ኣለፍኩኝ። ግምቴ ስህተቱ ያልገባዉ ሳይሆን እርምቱ ከእኔ መምጣቱን ኣለመፈለጉ እና የመጽሓፉን ጸሓፊ እና ኣሳታሚ ላለማሳጣት ነበር ነዉ።
ኣንዱን ትምህርቴን ጨርሼ ሌላዉን እስክጀምር የኣንድ የትምህርት መጽሓፍ ወይም ቴክስትቡክ ጥያቄዎችን እና መልሶችን ኣዘጋጅቻለሁ። ያረካኝ ስራ ነበር። ይሀን ስራ ስሰራ የኣሜርካ የመንግስት ተቋም ያሳተመዉ መጽሓፍ ዉስጥ ስህተት ኣስተዉዬ ከፕሮፌሰሬ ጋር ተወያይተን ኣርሜኣለሁ።
መጽሓፉ ከነጥያቄዎቹ መልሶች መጽሓፍ ወይም ሶሉሽንስ ማኑዋል ለህትመት በቅተዋል። ዛሬ መጽሓፉ ሶስተኛ እትም ላይ ደርሷል።
አሜርካ የሰራሁት የመጀመርያዉ ስራ ዉስጥ ሳምንታትን ሳልቆይ ኣንድ የኣሜሪካ ኣማካሪ የሰራዉን ስራ ማየት ወይም ሪቪዉ እንዳደርግ ተመደብኩኝ። የመደበኝ አለቃዬ የተማረ ነዉ። ያዉም እስከ መጨረሻ። እሱም ስራዉን ኣይቶት ወይም ሪቪዉ ኣድርጎት እኔ ያላየሁትን ስህተት ኣለዉ ኣለ። እኔ ዬለዉም ኣልኩኝ።
ኣማካሪዉ የተጠቀመዉን ፎርሙላ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለሁ እንዴት እንደሚወጣ የተማርኩኝ ነዉ። ፎርሙላዉን ማዉጣት አምስት ደቂቃ ኣያስፈልግም።
አለቃዬ ሸምድዶ የምያስታዉሰዉ ፎርሙላ ነበር። የታወቀ ሃንድቡክ ዉስጥ የታተመ። ያም ፎርሙላ ልክ ነዉ። ኣማካሪዉ የተጠቀመዉም ፎርሙላ ልክ ነበር። ልዩነታቸዉ ከሁለት ኣንግሎች የትኛዉን መርጠዉ በመነሳት ነዉ ፎርሙላዉን ያበጁት ነዉ።
ኣማካሪዉ የተጠቀመዉን ፎርሙላ እንዴት ማዉጣት እንዳሚቻል ለአለቃዬ እያስረዳሁት ግትር ብሎ ከእኔ ጋር ክርከር ሆነ። እኔን ግትር ወይም ስተቦርን እስከማለትም ደረሰ። ግራ ገብቶኝ ብዙም ሳልቆይ እሱ ለአለቃዉ ስህተት ነዉ ብሎ ተናግሮ ኣይ ስህተት ኣይዴለም መባል እንዳይባል መፈለጉ መሰለኝ። ያ ገጠመኝ ሲገርመኝ ይኖራል።
ኣማካሪዉ ያቀረበዉ ጥናት በብልዮን ዶላሮች ከሚቆጠር የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚረዳ ነዉ። ሁለተኛ ደርጃ ትምህርት ቤት ዉስጥ የተማርኳት ቀላል የምትመስል የጂኦሜትሪ ፎርሙላ እንደዚህ አይነት ጥቅም ላይ ትዉላለች። ሀሳብን ከስራ አገልግሎት ወይም ትኦሪን ከፕራክቲስ ጋር ኣያይዞ ማስተማር ኢትዮጵያ ዉስጥ በሰፊዉ ቢለመድ።
ሌላ ቦታ ስራ ጀምሬ ወራትን ሳልቆይ ለስራዉ ቦታ የሚመጥን የመሰለኝን የአሰራር ደንብ እንድያሳዩኝ ጠየኩኝ። ስራ ላይ የዋለ ኣንዱ የሳይንቲስቱ ኒዉተን ደንብ ነዉ። ስለደንቡ የኢትዮጵያ ኮሌጅ ዉስጥ ተምሬ ኣበጥሬ የገባኝ ነዉ።
ጥያቄዉን የጠየኩት ሰዉ ስለምን እንደጠየኩት በደንብ የገባዉ ኣይመስለኝም። ቦታዉ የቢልዮኖች ዶላሮችን ኦኮኖሚ ለማንቀሳቀስ የሚረዳ ፕሮጀክት ያለበት ነዉ። ስራዉ ላይ የተማሩ የተሰማሩበት ነበር። እስከ መጨረሻ የተማሩ የነበሩበት።
ለጥያቄዬ መልስ ማጣት ገርሞኝ ለብቻዬ ዚስ ፕሌስ ሃዝ ኤ ፕሮብሌም ብዬ ተነፈስኩኝ። ግርማቱ እና ይህን ለራሴ ስናገር የት ቦታ እንደነበርኩኝ ሁሌም ከፊቴ ኣይጠፋም።
ከዛ ግርምት በኋላ ነበር ስራዉን እራሴ ሰርቼ ባሳይ የሙያ ትርፍ ይኖረዋል ብዬ ያሰብኩኝ። እንዲሰራ እየወተወትኩ ቆይቼ በኋላ የራሴን ግዜ በመጠቀም እና በቤቴ ጭምር ሰርቼ ለጆርናል ወረቀት ህትመት ኣበቃሁ። የኢትዮጵያ ኮሌጅ ዉስጥ ተምሬ፣ ኣሜሪካ ደርሼ ጠይቄ ያላገኘሁትን ስራ ላይ መዋል የነበረበትን ጽንሰሀሳብ ቁልጭ ኣድርጌ ኣሳየሁ።
የጆርናል ወረቀቱ በማያዉቁኝ ፕሮፌሰሮች ታይቶኣል ወይም ሪቪዉድ ተደርጓል። ኣንዱ የፀሓፊዉን ችሎታ ኣደንቃለሁ። ይታተም ነዉ ያለዉ። የመጀመርያዉ ፅሑፍ ላይ ምንም ኣልጨመረበትም። ምንም ኣልቀነሰም።
ዚስ ፕሌስ ሃዝ ኤ ፕሮፕሌም ላልኩት የማያዉቀኝ ፕሮፌሰር እንዲህ ማለቱ እንደ ሙያ ትርፍ ኣልሜዉ የነበረዉ ብዬ ነዉ ያለፍኩት።
የኣንድ ግለሰብ ብቻ ቢሆኑም እነዚህ የመማር እና የስራ ልምዶች ምንን ያማለክታሉ? መረባረብ ትምህርት ላይ ነዉ ብዬ ላቀረብኩኝ ሀሳብ ገንቢ ሊሆኑ ይችላሉ?
መደበኛ ትምህርት ምን እንደሆነ በትንሹም ቢሆን ግልጽ ልያደርጉ ይችላሉ? ኣንድ ተማሪ ከስንት ኣስተማሪዎች ተምሮ ወይም ተምራ ነዉ ተማረ ወይም ተማረች የሚባለዉ?
በምህንድስና ትምህርት ዉስጥ የተጠቀሱት ሁለት መሠረታዊ ደንቦች ወይም ፎርሙላዎች በቢልዮኖች ዶላሮች ለሚንቀሳቀሱ ፕሮጀክቶች የሚሆኑ ከሆነ ኣንድ ተማሪ ለስራ ስንት ፎርሙላዎችን ነዉ መማር ያለበት? የተመራማሪ ለብቻ ነዉ።
ስለዚህ እነዚህ ልምዶች የሚጠቅሙ ከሆነ እነሆ። መነዛነዝ ከሆነም ሌላ መነዛነዝ ነዉ።
መማር ምን ማለት ነዉ? ተማረ ወይም ተማረች ማለት ምን ማለት ነዉ?
Last edited by Naga Tuma on 16 Aug 2023, 21:18, edited 5 times in total.
Re: መማር ምን ማለት ነዉ? ተማረ ወይም ተማረች ማለት ምን ማለት ነዉ?
You’re confused-low IQ-pseudo-intellectual-food stamp addict with lots of free time.
Re: መማር ምን ማለት ነዉ? ተማረ ወይም ተማረች ማለት ምን ማለት ነዉ?
ይህ ልምድ ገና ትምህርት ቤት ላሉት እና ወደፊት ስራ ላይ ለመሰማራት ለሚዘጋጁት የወደፊት ሰራተኞ በጣም ጠቃሚ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።
ከትምህርት ቤት የበለጠ የስራ ልምድ ኣስተማሪ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል። ትምህርት ቤት ጽንሰሀሳብ ወይም ኮንሰፕት ላይ የበለጠ ያተኩራል። ስራ ተግባር ላይ የበለጠ ያተኩራል።
ጽንሰሀሳብን በተግባር ማሳየት ቀላል ኣይዴለም። ከበሮ ስያዩት ያምር፣ ስይዙት ያደናግር የተባለዉ ሳይስተዋል ኣይዴለም።
ያለችኝ ልምድ ስራን በተግባር ማሳየት በጣም ቀላል የሆኑ ሀሳቦችን ከመሠረቱ ማስተዋል እና መሠረታዊ የሆኑ ጽንሰሀሳቦችን በደንብ ማወቅ ናቸዉ።
ሶስት የማልረሳቸዉ ምሳሌዎች ኣሉ።
ኣንዱ ስራ ጀምሬ የተለያዩ የዳታ ፋይሎችን ሳገላብጥ ፋይሎቹ መቼ እንደተጀመሩ፣ ማን እንደጀመራቸዉ፣ ለምን ምክንያት እንደተጀመሩ በደንብ ያልተመዘገቡ መሆኑን ኣስተዋልኩኝ። ለራሴ እንዲመቸኝ የምጠቀማቸዉን የዳታ ፋይሎች አያያዝ በጣም ቀላል የሆነ የፋይል ፕሮቶኮል ጀመርኩኝ።
ከዛም ሌሎች እኔ የተጠቀምኳቸዉን የዳታ ፋይሎች ሲጠይቁ ከነ ፋይል ፕሮቶኮል ጋር መላክ ጀመርኩኝ።
ሌሎችም ያንን የዳታ ፋይል አጠቃቀም በራሳቸዉ ፋይል ዉስጥ እያስገቡ መጠቀም ጀመሩ። ያቺ በጣም ቀላል የሆነች የዳታ ፋይል ኣያያዝ በኣለም ደረጃ በታወቁ ሁለት ትልልቅ ኣማካሪ ድርጅቶች ኣማካሪዎች ጋርም ደርሳ ተስፋፍቶ ሲጠቀሙ ኣየሁ።
ለራሴ እንዲመቸኝ ያቺ ቀላል የሆነች ጅምር እንደዛ በሰፊዉ ስራ ላይ ስትዉል እያየሁ ይገርመኝ ጀመር። ያቺን ቀላል ጅምር ማን እንደጀመራት ለብዙ ግዜ የታወቀ ኣይመስለኝም። እኔም ዝም ብዬ እያየሁ።
ሁለተኛዉ የስራ ስምርት ስነስርዓት ነዉ። በእንግሊዘኛ ቼይን ኦፍ ኮማንድ ይሉታል።
ይህ በቅንነት ስራ እየተሰራ ያልተስተዋለ በጣም ቀላል የሆነ ነገር ነዉ።
አለቃዬ ኣንድ ስራ ላይ ያሰማራኛል። የአለቃዬ አለቃ እኔን የሚመለከት ስራ ሲመጣበት ቢሮዬ መጥቶ ሌላ ስራ ላይ ያሰማራኛል። የአለቃዬ አለቃ አለቃም እኔን የሚመለከት ስራ ሲመጣበት ቢሮዬ መጥቶ እንደገነ ሌላ ስራ ላይ ያሰማራኛል።
ይህ ማለት በኣንድ ግዜ ሶስት ስራዎች ላይ መሰማራት ሆነብኝ ማለት ነዉ። ሶስቱንም መስራት ይቻላል። የሚከብደዉ የየትኛዉን አለቃ ማሰማራት ማስቀደም ያስፈልጋል የሚል ጥያቄ ነዉ።
ይህን የሶስት አለቆች አንድ ሰራተኛ ላይ ሶስት ስራዎችን በኣንዴ ማሰማራት ያስተዋልኩኝ እኔ ብቻ ኣልነበርኩም።
ለዚህ በጣም ቀላል የሆነ መፍትሔ የስራ ስምርት ስነስርዓት ወይም ቼይን ኦፍ ኮማንድ ነዉ። እኔን ስራ ላይ ማሰማራት ሲፈልግ የአለቃዬ አለቃ አለቃ የአለቃዬ አለቃ ጋ ማድረስ፣ ከዛም እሱ አለቃዬ ጋ ማድረስ፣ የ አለቃዬ አለቃም እኔን ስራ ላይ ማሰማራት ሲፈልግ አለቃዬ ጋ ማድረስ፣ አለቃዬ የሶስቱን ስራዎች ቅደም ተከተል መወሰን እና ለእኔ ማሳወቅ።
በጣም ቀላል የሆነ፣ ነገር ግን ወሳኝ የሆነ አሰራር ነዉ።
ይህን ካስተዋልኩኝ በኋላ አለቃዬን ኣማከርኩት። ይህ ቶሎ ገብቶት የአሰራር ስነስርዓቱ ተስተካከለ።
ሰንብቼም በመከርኩኝ ተገሰጽኩኝ። ቼይን ኦፍ ኮማንድ እወቅ ተብዬ።
ሶስተኛዉ ወስብስብ የሆነ፣ ነገር ግን መሠረታዊ የሆነ ጽንሰሀሳብን ስራ ላይ ማዋል ነዉ። ኣንድ በኣንዱ የኒዉተን የሳይንስ ቀመር ላይ የተመሠረተ የሙያ ጽንሰሀሳብ ነዉ።
ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዓመት ላይ ዶክተር ስለሺ በቀለ ያስተምር የነበር የኮሌጅ ኮርስ ዉስጥ ነበረ። ወደ ፖለትካ አመራር ሳይገባ በፊት።
ያ መሠረታዊ የሆነ ጽንሰሀሳብ ተግባር ላይ ዉሏል ብዬ የጠበኩበት ቦታ ለማየት ፈልጌ ኣላገኘሁም። በተግባር ስራ ላይ ኣለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ያ መሠረታዊ የሆነ ጽንሰሀሳብ ሳይተገበር ያንን የሙያ ስራ እንዴት በስነስርዓት መስራት እንደተቻለም ገረመኝ።
ሁለቱንም ሰርቶ ማሳየት መልካም ኣጋጣሚ ነበር። ሙጭጭ ብዬም ቁልጭ ኣድርጌ ኣሳየሁኝ። ኣጥንቼ ለጆርናል ወረቀት በማብቃት። ጽንሰሀሳቡን ብቻ ሳይሆን ያ ጽንሰሀሳብ ስራ ላይ ሳይዉል ስራዉን መስራት እንዴት እንደተቻለ የሚጠቁም የሙያ ጆርናሉ ወረቀት ርዕስ ዉስጥ በማካተት።
ይህን እያጠናሁ እና ስራ ላይ እንድናዉል ስመክር ስሰነብት ኣንድ በችሎታዉ በደንብ የሚከበር ሰዉ ይህ መሠረታዊ ጽንሰሀሳብ እንዴት እንዳልተገለፀለት እንቆቅልሽ ሆኖብኝ ሰነበተ። ቆይቼም ምክንያቱ ምን ሊሆን እንደቻለ ግምት ኣገኘሁ። ትክክል ይሁን ኣይሁን ባላዉቅም የመጀመርያ ድግሪዉን ያገኘዉ በሌላ ሙያ መሆኑን ሰማሁ። ጠይቄ ሳይሆን በኣጋጣሚ የሰማሁኝ ትክክል ከሆነ መዉሰድ የነበረበት ነገር ግን ያልወሰደዉ የሙያ ኮርስ ነበረ ማለት የሚቻል ይመስለኛል። ትክክል ከሆነ ይህም ልምድ የምያዛልቅ ሙያ ላይ ለመሰማራት የሚጠቅም ሊሆን ይችላል ማለት ነዉ።
በኣጭሩ ይህ የስራ ልምድ የምያሳየዉ ስራን መስራት በጣም ቀላል የሆኑ ወሳኝ የአሰራር ስነስርዓቶችን እና መሠረታዊ የሆኑ ጽንሰሀሳቦችን ማስተዋል ነዉ።

Last edited by Naga Tuma on 22 Nov 2023, 19:43, edited 1 time in total.
Re: መማር ምን ማለት ነዉ? ተማረ ወይም ተማረች ማለት ምን ማለት ነዉ?
ትምህርት የማያቋርጥ ሂደት ነው። ሁሉም ቦታ ትምህርት ቤት ነው የሚል መሪ ቃል ነበር በመሰረተ ትምህርት የዕውቀት እና የስራ ዘመቻ ዘመን - በደርግ ጊዜ መሆኑ ነው።
እንደ እኔ አንድ ሰው የተማረ(ች) ናት ማለት ከበፊት ከበረበት የግንዛቤ ወይም ክህሎት ተሽሎ መገኘት ነው። የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው የሚል ቅዱስ ቃል አለ። ይህ ምክር ከሁሉ በላይ ነው - አምላክህን ማክበር እና ትዕዛዛቱን በችሎታህ መጠን መፈጸም አንድ ትልቅ ጥበብ ነው። በመቀጠል ሰው ሁል ጊዜ ማወቅ ያለበት አለማወቁን ጭምር ነው። ልክ ተስፋ የህይወት የመኖር አቀጣጣይ ነዳጅ እንደ ሆነ ሁሉ አለማወቅ እንድሁ ለማወቅ ጥረትን ያቀጣጥላል እንድህ እያለ ሂደቱ ይቀጥላል:: Learning is a continuous process. It is relative with time, place and people.የተማረ(ች) እራሱ አገላለጹ አንጻራዊ ነው። የት ቦታ፤ በምን ጊዜ እነ ማን ይህን አሉ ወሳኝ ናቸው። ለምሳሌ ጥንት የትምህርት ጮራ ባልፈነጠቀበት ዘመን አንድ የሰርግ ዘፈን ነበር እንድህ የሚል " የእኛ ሙሽራ ኩሪ ኩሪ፤ በእንግሊዝ ተናገሪ"። እግዜር ያሳይህ እንግሊዘኛ መናገር በእራሱ ትልቅ ችሎታ እና የተማረ ፈላስመን ወይም ጥበበኛ ተደርጎ ይወሰድ ነበር ማለት ነው። ግን እንግሊዘኛ የሚናገር ስንት መሃይም ፈረንጅ እንዳለ ግን አያውቁም ወይም ሱዳን አልያም የሱማሌ ዘላን ከብት አርቢ እንግሊዘኛ ሲናገር አልሰሙም። የአሁኑ ዘመን ትውልድ ደግሞ እንግሊዘኛ የሚናገር በርካታ መሃይም ስላየ ወይም ስለ ሰማ ጠጅ ቤት የገባ ሰው እንግሊዘኛ ይናገራል - ወይም ሲናገር ከዩ ጠጅ ጠጥቷል መሰል ይሉሃል።

ኣበረ፣
በአጭሩ ማሰማር ማለት ማሳየት፣ መምራት ሲሆን መማር ማየት፣ መከተል ማለት ነው ። ምንድነው የሚታየው እና መሪው ከተባለ አንዱ ፈር ነው ሌላው ዲካ ነው ። አስተማሪው በዶክትሪን፣ በዶግማና በካሪክለም የቀረጸው ፈርና ዲካ ማለት ነው። ያሳዩትን ፈርና ዲካ ማየትና መከተል የቻለ ይፈተንና ሲታልፍ የተማረ ይባላል ።
አንድ ሰው በተሰጠው መስክ የተማረ ከሆነ አዋቂ እንለዋለን ፣ አወቀ ለየ ይላል ። አዋቂ አንድን ነገር ከሌላ ነገር መለየት የቻለ የሚችል ማለት ነው። እነዚህ ሁሉ በመጽሃፍ ከተከማቹ አሮጌ ልምዶች ታሪክ ማግኘት ይቻላል ። ትልቁ እጅግ ትልቁ እውቀት ግን ክህሎት ነው ። አንድን ነገር እንዴት እንደ ተሰራ ማወቅ ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደ ሚሰራ ማወቅ ነው።
ስለሆነም የእውቀት ሁሉ ቁንጮ በተግባር የታየ ችሎታና በተግባር ፣ በኤክስፔሪያንስ የተከማቸው ችሎታ ወይም እውቀት ነው። አንድ መሃንዲስ ሚሊዪዮን የምህንድስና መረጃዎች ባንጎሉ ቢያከማች ቤት ማነጻ ካልቻለ የምህድስና አዋቂ አይደለም ።
አቢይ አህመድን ውሰድ ካማካሪና ጉግል የሰበሰበው ነገር በብዙ መጻፍት መልክ አሳትሟል ማለትም ስለ ፖለቲካ እውቀትና አገር አስተዳደር!! ነገር ግን እሱ እራሱ አገር ማስተዳደር ፣ ሕዝብ መምራት አያውቅበትም፣ ክህሎቱ ችሎታው ፣ የለውም። ይህን ሰው የፖለቲካና መሪነት አዋቂ አንለውም ። የፖለቲካና አስተዳደር ሳይንስ ተማሪ ወይም ምሁር አንለውም ።
ከዚህ ባለፈ አሁን ያለው ፈርና ዲካን በልጠው አዲስ ፍርና አዲስ ዲካ የሚቀዱ፣ የሚያሳዩ ሊቅ ይባላሉ፣ አዲስ መንገድ ፈጣሪዎች ስለሆኑ ። ይህው ነው !

ሆረስ፤
እግዜር ይስጥልን! ፍንትው አድርገህ ነው ያስተማርከን። እንድህ አይነቱን ተግባራዊ አገላለጽ ቁልፍ ከእነመክፈቻው በእጅ መስጠት ነው። ካልተሳሳትኩ በምርምር ቋንቋ Operational Definition የሚባል ይመስለኛ።ሲጓዝ መንገዱን ያወቀ ሲመለስ አይቸገርም አይነት ነው። አንድ ነገር በቀላል ማስረዳት ግዙፉን ሳያጎድሉ መጥኖ እንደ መስጠት ነው። Simplification is the ultimate sophistication እንዳሉት እነ እስቲቭ ጆብ አይነቶቹን:: በዚህ እረገድ አንተ የማድረግ ችሎታህ የሚደነቅ ነው። አንድ ነገር ግን መማር የማያቆም ሂደትም ነው። አንድ ሰው ፕሮፌሰር ቢሆንም እንኳ ያ ሰው ገና የደራ ትምህርት ውስጥ ዋና ላይ ነው ባይ ነኝ። አስተማሪ መሆን እጅግ ክቡር ስራ እና አስጨናቂ ሃላፊነትም ነው። መምህሩ ሁል ጊዜ የተሻለ አዳዲስ ነገሮች በማንበብ እና በማጥናት ከተማሪው ልቆ መቅረብ አለበት። ልክ አንድት ላም ብዙ ወተት ለማለብ ብዙ መመገብ አለባት። ትናንት በበላቸው ዛሬ እንደማትታለብ ሁሉ። ለምሳሌ የዛሬ 35 አመት ህክምና ትምህርት ያጠናቀቀ ሃኪም ዛሬ ቴክኖሎጅ እና ኢንፎርሜሽን መስኩን ስለቀየረው ሃኪሙ እራሱን ማደስ አለበት። ሃኪም ከ Google ተሽሎ መገኘት አለበት።

Horus wrote: ↑23 Nov 2023, 02:37ኣበረ፣
በአጭሩ ማሰማር ማለት ማሳየት፣ መምራት ሲሆን መማር ማየት፣ መከተል ማለት ነው ። ምንድነው የሚታየው እና መሪው ከተባለ አንዱ ፈር ነው ሌላው ዲካ ነው ። አስተማሪው በዶክትሪን፣ በዶግማና በካሪክለም የቀረጸው ፈርና ዲካ ማለት ነው። ያሳዩትን ፈርና ዲካ ማየትና መከተል የቻለ ይፈተንና ሲታልፍ የተማረ ይባላል ።
አንድ ሰው በተሰጠው መስክ የተማረ ከሆነ አዋቂ እንለዋለን ፣ አወቀ ለየ ይላል ። አዋቂ አንድን ነገር ከሌላ ነገር መለየት የቻለ የሚችል ማለት ነው። እነዚህ ሁሉ በመጽሃፍ ከተከማቹ አሮጌ ልምዶች ታሪክ ማግኘት ይቻላል ። ትልቁ እጅግ ትልቁ እውቀት ግን ክህሎት ነው ። አንድን ነገር እንዴት እንደ ተሰራ ማወቅ ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደ ሚሰራ ማወቅ ነው።
ስለሆነም የእውቀት ሁሉ ቁንጮ በተግባር የታየ ችሎታና በተግባር ፣ በኤክስፔሪያንስ የተከማቸው ችሎታ ወይም እውቀት ነው። አንድ መሃንዲስ ሚሊዪዮን የምህንድስና መረጃዎች ባንጎሉ ቢያከማች ቤት ማነጻ ካልቻለ የምህድስና አዋቂ አይደለም ።
አቢይ አህመድን ውሰድ ካማካሪና ጉግል የሰበሰበው ነገር በብዙ መጻፍት መልክ አሳትሟል ማለትም ስለ ፖለቲካ እውቀትና አገር አስተዳደር!! ነገር ግን እሱ እራሱ አገር ማስተዳደር ፣ ሕዝብ መምራት አያውቅበትም፣ ክህሎቱ ችሎታው ፣ የለውም። ይህን ሰው የፖለቲካና መሪነት አዋቂ አንለውም ። የፖለቲካና አስተዳደር ሳይንስ ተማሪ ወይም ምሁር አንለውም ።
ከዚህ ባለፈ አሁን ያለው ፈርና ዲካን በልጠው አዲስ ፍርና አዲስ ዲካ የሚቀዱ፣ የሚያሳዩ ሊቅ ይባላሉ፣ አዲስ መንገድ ፈጣሪዎች ስለሆኑ ። ይህው ነው !
Re: መማር ምን ማለት ነዉ? ተማረ ወይም ተማረች ማለት ምን ማለት ነዉ?
አበረ፣
እኔም አመሰኛለሁ።
በመጀመሪያው ጽሁፍህ ውስጥ አንስተህው ስለነበር አልደገምኩትም እንጂ ስለ ትምህርት ቀጣይነት የምትለውኮ እጅግ እጅግ ትክክል ነው ። ለምን መሰለህ? ማንኛውም አይነት እውቀት ከተራ መረጃ እሰከ ፍልስፍና፣ ቲኦሪ በለው እስከ ክህሎትና ተግባራዊ እውቀት እንደ ማንኛው መሳሪያ ያረጃል። እንደ ምታውቀው እውቀት ቴክኖሎጂ ነው፤ በዚህ አለም ስንመላለስ እንዴት እንደ ምንኖር፣ ነገሮች እንዴት እንደ ምናደርግ የምንጠቀምበት መሳሪያችን ነው ። ስለሆነም በዙሪያችን ያለው አለም ሲለወጥና የትላንት ክህሎታችን ላዲሱ ሁኔታ አልሰራ ሲል በግድ እውቀትና ክህሎታችን ማደስ አለብን። ስለዚህ ያልከው የማይቋረጥ ትምህርት ወድደን ሳይሆን በግድ ማድረግ ያለብን ነገር ነው። All knowledge or information has limited shelf life. Like all things, knowledge and skills expire in time. በሌላ አባባል ዛሬ ወደ ኋላ የቀሩ ሕዝቦች የምንባለው እንዳልከው ከስር ከስር ያለ ማቋረጥ በመማርና ክህሎትና ቴክኖሎጂዎችን በማደስ በግዜ ቀስት ላይ አብሮ መጋለብ ስላልቻልን ነው እንጂ ድሮማ ከም ዕራብ የቀደመ እውቀትና ክህሎት ነበረንኮ ። ለምሳሌ ይህን ዘመን የሚነዳው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ሰው ሰራሽ ክህሎት (አርቲፊሻል ኢቴል) ቢበዛ ከ2 አመት ያለፈ እድሜ የለውም። እኔ ምናልባት 90% አሁን ያሉት ቴክኖሎጂዎች መጠቀም አልችልም። ያለ ማቁረጥ ብትማር እንኳ ሁሉን ማዳርስ ስለማንችል!!

Telling your own history and life experiences based on your understanding of your national and cultural identity, principles, values and ideals that has shaped you to be the person that you are today, are key measures of intelligence. IQ. Unfortunately, in our neck of the woods, asking a white man to tell you about your own history has become the accepted norm that people have developed an addiction to hearing lies when it would be simpler to tell their own truth (no matter how bitter or sweet).