Page 1 of 1

"መከላከያ" አሁንም ምርኮ እየሆነ እጅ እየሰጠ ነው - መውጫ መግቢያ መፈናፈኛ አጥቷል።

Posted: 11 Aug 2023, 09:24
by Abere
"መከላከያ" አሁንም ምርኮ እየሆነ እጅ እየሰጠ ነው - መውጫ መግቢያ መፈናፈኛ አጥቷል።ወጊያው ተጧጡፏል።

ምናልባትም አሁን በምስራቅ አፍሪካ አስጊ ከሆነው የሱዳን ግጭት በከፋ ይህ በአማራ ሀይል እና በኦሮሙማ-መከላከያ መካከል የሚደረገው ዘላቂ ጦርነት ሊሆን የሚችል ነው። ለኢትዮጵያ ረዥም ጦርነት አገሪቱን አሁን ካለችበት የከፋ ውድቀት ውስጥ ይጥላታል። አሁን በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ያሉ እና መሰረት የጣለባቸው ሲሆኑ ቀሪዎቹ የግጭት ቀጠናዎች ወታደር የሰፈረባቸው ናቸው። ወታደሩም በየእዕለቱ በመክዳት እየተበተነ ነው። የዚህ ሰሞን ውጊያ የመከላከያ ዕዞችን በብዛት ያፈረሰ እና ሃይል ያደከመ ነው። ይሁን እንጅ አገሪቱ በወንጀለኛ አብይ አህመድ ስር ስለሆነች በወንጀሉ ላለመያዝ የሚችለውን ሁሉ ማድረጉ አይቀርም፤ በጥላቻ የተለከፉት ተከታይ ኦሮሙማዎች እንድሁ ስጋት ስላለበቸው ትንቅንቁ ይቀጥላል። ኢትዮጵያን ግን መምራት አይችሉም - ይህ እድል አምልጧቸዋል። ምናልባትም በቀጣይ ሌሎች ክልሎች ከአማራ ትምህርት በመውሰድ እነርሱም ተላላኪ የብልጽግና አስተዳደርን ማባረር እና መደምሰስ ይጀመሩ ይሆናል። የትግራይ ህዝብም ከአማራ ትምህርት ሊወስድ ይችላል። የትግራይ ህዝብ በትህነግ ወያኔ ዕድሜውን ሲረገጥ እና ለትህነ ተገዶ ሲሞት ያነበረ በመሆኑ እርሱም እንደ አማራ ወያኔን ጥሎ እራሱን ነጻ ሊያወጣ ይችላል። የአማራ ህዝብ ትግል ግን አሁን ከማይቀለበስበት ደረጃ ደርሷል።





Re: "መከላከያ" አሁንም ምርኮ እየሆነ እጅ እየሰጠ ነው - መውጫ መግቢያ መፈናፈኛ አጥቷል።

Posted: 11 Aug 2023, 11:07
by Axumezana
የአይጥ፥ ምስክርዋ፥ ደምቢጥ፤ አበረም፥ ደረጀም፥ ያልተፃፈ፥ ነው፥ የሚያነቡት።

Re: "መከላከያ" አሁንም ምርኮ እየሆነ እጅ እየሰጠ ነው - መውጫ መግቢያ መፈናፈኛ አጥቷል።

Posted: 11 Aug 2023, 11:12
by Revelations