Page 1 of 2

ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 05 Aug 2023, 16:26
by Horus
ፋኖ የሚለው ቃል በግእዝ፣ በላቲን፣ በግሪክ፣ በሳንስክሪት (ሂንዲ) ምንም ሳይለወጥ በድምጽም በትርጉምም አንድ የሆነ እጅግ ትንታዊና ግዙፍ ቃል ነው ።

ቃሉ የተወለደው በጥንታዊት ግብጽ ነው ። ዛሬ ‘ፋ’ የተባለው የቃሉ መጀምሪያ ክፍል ግብጾች ባ፣ ወይም ፓ፣ ወይም ፋ ይበሉት አይበሉት በውል አይታወቅም ።

በእኔ ግምት ‘ባ’ ይባል ነበር ባይ ነኝ። ይህም ያልኩት የፋ ተዛማጅ ግእዝ ቃል ቦ (ሆነ፣ ታየ፣ ተከሰተ) ስለሆነ ነው።

የግብጽ ትርጉሙ ግን ይታወቃል ። በራ፣ ታየ፣ ተገለጸ ማለት ነው። ይህ ዛሬም ያለው ትርጉሙ ነው ።

ፋኖ የሚለው ቃል ሁለተኛ ክፍል ‘ኖ ‘፣ ነ ፣ የሚለው ቃል ነው ።

ይህ ድምጽ በጥንታዊ ግብጽ ‘ረ ‘ ነበር ። ወደ ጥንታዊ ሴም ቋንቋ ሲለወጥ ‘ለ’ ሆነ ። በግእዝና አማርኛ ‘ነ ‘ ሆነ።

የግብጾች ‘ረ’ ብርሃን ወይም ጸሃይ ማለት ነው ። የሴማዊያን ‘ለ’ ብርሃን’ ማለት ነው ።

የብርሃን አምላክ ስም ‘ኧል‘ ‘ኤል‘ ኤላ፣ ኤሎሄ፣ ወዘተ ከዚያ ቃል የተቀዱ ናቸው ።

ስለዚህ ፈና፣ ፋና፣ ፌኖ፣ ፊና፣ ፋኖ ማለት ፏ ያለ ብርሃን፣ ፋ ያለ የበራ ብርሃን ፣ በብርሃን መገለጽ ማለት ሲሆን የቀሩት ልዩ ልዩ አጠቃቀሞቹ እንደ ሚከተለው ነው።

ፋኖ (ቅጽል) መሪ ብርሃን፣ አመልካች፣ ጠቋሚ፣ አቅጣጫ የሚያሳይ ማለትም ቀዳሚ ማለት ሲሆን ባንድ ቃል ግምባር ቀደም መሪ ማለት ነው ።

ፈነው ተገለጸ ብሩህ ሆነ ማለት ነው ።

ፍኖት መንገድ፣ አቅጣጫ ፣ አመልካች ማለት ነው ። ለምሳሌ ፍኖተ ሰላም፣ ፍኖተ ብርሃን፣ ፍኖተ ሰማይ ..

ፋና የወደፊት ጉዞ የሚያሳይ ሲሆን ሌሎች ፋና ወጊ ይሉታል

ሌሎችም ብዙ የኢትዮፒክ ዝርያዎች አሉት ።

በግሪክና ላቲን ፌኖማ መገለጽ፣ አፒራንስ ማለት ሲሆን ፌኖሜና ባይምሮ ውስት የሚታይ ማለት ነው ።

ፌኖሜኖሎጂ የሚባለው የፍልስፍና መስክ በዚያ የተሰየመ ነው ። ሪያሊቲ የሚታወቀው ባይምሮ ውስጥ በሚገለጽ ምስል ነው የሚለው ፍልስፍና ።

ኤፒፋኒ ወይም ጥምቀት እግዚአብሄር ለሰው ወይም ለሰው አይምሮ የተገለጸበት ማለት ነው ።

በአጭሩ በዚህ እጅግ ጥልቅና ጥንታዊ ቃል ነው በቅጽል ፎርሙ ፋኖ ብሎ አማራ የነጻነት ትግል ግምባር ቀደም ጦረኞችን የሰየመው ።

ድል ላማራ! ድል ለኢትዮጵያ!!!

ሆረስ ዐይነ ብርሃን

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 05 Aug 2023, 16:31
by Axumezana
ፋነነ፥ አኢምሮውን፥ ሳተ፥ ፈረጠጠ፥ ለያዥ፥ ለገናዥ፥ አስቸገረ፥
የሰው፥ ባህሪ፥ ሳይሆን፥ የእንስሳ፥ ባህሪ፥ነው።

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 05 Aug 2023, 16:34
by Abere
ሆረስ፤

ይህን ነገር ቀጥታ ትርጉሙን አንተ በደንብ ያስቀመጥከው ይመስለኛል - ስርወ-ቃሉን።የነጻነት ፋና ወጊ (ፈር ቀዳጅ ብርሃን) አይነት ነው አሁን የሚመስለው በአንተ አገላለጽ።

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 05 Aug 2023, 16:38
by Horus
Axumezana wrote:
05 Aug 2023, 16:31
ፋነነ፥ አኢምሮውን፥ ሳተ፥ አበደ፥
አይ ይህ እስላንግ ይባላል ። በአንጎሉ ውስጥ የሚኖር እንደ ማለት እንጂ በቋንቋው መሰረት ከሄድን ነ ሲደገም በጣም የሚል ማጠንከሪያ ትርጉም ነው የሚኖረው ማለትም በጣም የሚያይ ሰው እንደ ማለት እንጂ ያበደ ያይምሮ በሽተኛ ማለት አይደለም ። እብድ ከሪያሊቲ ስለሚለይ የሌለ ነገር ነው የሚያየው ። ፌኖሜኖሎጂ ሪያሊቲን ባይምሮ ምስል ማየት ማለት ነው ። ተቃራኒው ማለት ነው።

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 05 Aug 2023, 16:44
by Horus
Abere wrote:
05 Aug 2023, 16:34
ሆረስ፤

ይህን ነገር ቀጥታ ትርጉሙን አንተ በደንብ ያስቀመጥከው ይመስለኛል - ስርወ-ቃሉን።የነጻነት ፋና ወጊ (ፈር ቀዳጅ ብርሃን) አይነት ነው አሁን የሚመስለው በአንተ አገላለጽ።
አበር፣
ፈር የሚላው እኮ ፈን/ፋና ነው ። አንድ ጨመርክ ማለት ነው ። ሌሎችም ብዙ አሉ ። ለምሳሌ በጉራጌኛ ፋራ ማለት ፋይዳ ፣ አላማ፣ ፐርፐዝ ማለት ነው ። ቃሉ በጣም ጥልቅ ነው! ራ/ላ/ና ሺፍት ያደርጋል ብያለሁ ። ለምሳሌ ክስታኔ መስቀ(ል) ሲል አንዳንድ ሰባት ቤቶች መስቀ(ር) ይላሉ ።

ፋኖ የሚለው ግ ን እንዳለከው ነው ።

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 05 Aug 2023, 16:46
by Assegid S.
ሰላም Brother Horus; ለዚህና ለሌሎችም አስተማሪ መጣጥፎችህ ብዙ ብዙ ልትመሰገን ይገባል። የ ፋኖስ ም ስያሜ ከዙሁ ጋር የተያያዘ ነው ብዬ እገምታለሁ።

መልካም ሰንበት ይሁንልህ, ወንድም ሆሩስ 8)

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 05 Aug 2023, 16:50
by Abere
ፈነነ ማለት የትግሉ ሻማ ቀንድል ሆነ - አብሪ ወይም ተወርዋሪ ሃይል ሆነ ማለት ነው። ይህ ፋኖ ነው ትህነግ ማይካድራ እና መከላከያ ዕዝ ላይ ጥግ የደረሰ ግፍ ተሰምቶት ተንደርድሮ በመሄድ ወያኔን የፎነነው - አፍንጫውን የቆረጠው።
Axumezana wrote:
05 Aug 2023, 16:31
ፋነነ፥ አኢምሮውን፥ ሳተ፥ ፈረጠጠ፥ ለያዥ፥ ለገናዥ፥ አስቸገረ፥
የሰው፥ ባህሪ፥ ሳይሆን፥ የእንስሳ፥ ባህሪ፥ነው።

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 05 Aug 2023, 16:53
by Horus
Assegid S. wrote:
05 Aug 2023, 16:46
ሰላም Brother Horus; ለዚህና ለሌሎችም አስተማሪ መጣጥፎችህ ብዙ ብዙ ልትመሰገን ይገባል። የ ፋኖስ ም ስያሜ ከዙሁ ጋር የተያያዘ ነው ብዬ እገምታለሁ።

መልካም ሰንበት ይሁንልህ, ወንድም ሆሩስ 8)
በትክክል! ፋኖስ ብቻ አይምሰልህ

ይህው አሁን ትዝ ያሉኝ
ፎቶ (photo) ላቲን
ፎርም
ፋሽን
ፋንታሲ
????

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 05 Aug 2023, 17:01
by Wedi
"ፉኖነት፣

የበላይ ዘለቀ፣ የገረሱ ዱኪ፣ የአቡነ ጴጥሮስ፣ የኡመር ሰመተር፣ የሸዋረገድ ገድሌ፣ የአበበ አረጋይ፣ የአሞራው ውብነህ፣ የጃገማ ኬሎ፣ የአቡነ ሚካኤል የጀግንነት ነባር ቅርስ፣ የአልበገር ባይነት ቋሚ ውርስ፣ የነፃነት ፍቅር ቅጥለታዊ ንግስ እና የኢትዮጵያዊነት ህልውናዊ ነፍስ ነው።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ፣ ከዘር ልዩነት አልፎ፣ ከጎሳ ቅያድ ተርፎ፣ ከክልል ቅፍንድ ገዝፎ ሊያነበው የተገባ ልጨኛ መጽሐፍ ነው፥ ፋኖነት!

ጌትነት ይርሳው፣ የሚያውቀውን እውነት የሚናገር፣ የሚናገረውን የሚሰራ እና የሚሰራውን የሚያውቅ ብእረኛ መሆኑን ያሳየበት ብሉይ መጽሀፍ ነው፥ ፋኖነት ።"

ምንዳር አለው ዘውዴ (ፕ/ር) የፍልስፍናና የስነብዕሲ ማዕምር

:!:

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 08 Aug 2023, 02:16
by Horus
የፋኖና ጀዊሳ ርጉም ምንና ምን !!! You can't alter the meaning of Phano by reframing things. Naming is a serious business . If you want a name or framing to stick, it better be based on reality. The concept of phano is a name inseparably tied to the Glorious Battle of Adwa. Only idiots in the likes of Abiy Co. would attempt to associate Jawisa (ረባሽ) with the name of Fathers of the Free Black race. መዝጊያ ገቢር የሌለው የእረኞች ድራማ :lol: :lol: :lol:

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 09 Aug 2023, 06:26
by DefendTheTruth
Horus wrote:
05 Aug 2023, 16:26
ፋኖ የሚለው ቃል በግእዝ፣ በላቲን፣ በግሪክ፣ በሳንስክሪት (ሂንዲ) ምንም ሳይለወጥ በድምጽም በትርጉምም አንድ የሆነ እጅግ ትንታዊና ግዙፍ ቃል ነው ።

ቃሉ የተወለደው በጥንታዊት ግብጽ ነው ። ዛሬ ‘ፋ’ የተባለው የቃሉ መጀምሪያ ክፍል ግብጾች ባ፣ ወይም ፓ፣ ወይም ፋ ይበሉት አይበሉት በውል አይታወቅም ።

በእኔ ግምት ‘ባ’ ይባል ነበር ባይ ነኝ። ይህም ያልኩት የፋ ተዛማጅ ግእዝ ቃል ቦ (ሆነ፣ ታየ፣ ተከሰተ) ስለሆነ ነው።

የግብጽ ትርጉሙ ግን ይታወቃል ። በራ፣ ታየ፣ ተገለጸ ማለት ነው። ይህ ዛሬም ያለው ትርጉሙ ነው ።

ፋኖ የሚለው ቃል ሁለተኛ ክፍል ‘ኖ ‘፣ ነ ፣ የሚለው ቃል ነው ።

ይህ ድምጽ በጥንታዊ ግብጽ ‘ረ ‘ ነበር ። ወደ ጥንታዊ ሴም ቋንቋ ሲለወጥ ‘ለ’ ሆነ ። በግእዝና አማርኛ ‘ነ ‘ ሆነ።

የግብጾች ‘ረ’ ብርሃን ወይም ጸሃይ ማለት ነው ። የሴማዊያን ‘ለ’ ብርሃን’ ማለት ነው ።

የብርሃን አምላክ ስም ‘ኧል‘ ‘ኤል‘ ኤላ፣ ኤሎሄ፣ ወዘተ ከዚያ ቃል የተቀዱ ናቸው ።

ስለዚህ ፈና፣ ፋና፣ ፌኖ፣ ፊና፣ ፋኖ ማለት ፏ ያለ ብርሃን፣ ፋ ያለ የበራ ብርሃን ፣ በብርሃን መገለጽ ማለት ሲሆን የቀሩት ልዩ ልዩ አጠቃቀሞቹ እንደ ሚከተለው ነው።

ፋኖ (ቅጽል) መሪ ብርሃን፣ አመልካች፣ ጠቋሚ፣ አቅጣጫ የሚያሳይ ማለትም ቀዳሚ ማለት ሲሆን ባንድ ቃል ግምባር ቀደም መሪ ማለት ነው ።

ፈነው ተገለጸ ብሩህ ሆነ ማለት ነው ።

ፍኖት መንገድ፣ አቅጣጫ ፣ አመልካች ማለት ነው ። ለምሳሌ ፍኖተ ሰላም፣ ፍኖተ ብርሃን፣ ፍኖተ ሰማይ ..

ፋና የወደፊት ጉዞ የሚያሳይ ሲሆን ሌሎች ፋና ወጊ ይሉታል

ሌሎችም ብዙ የኢትዮፒክ ዝርያዎች አሉት ።

በግሪክና ላቲን ፌኖማ መገለጽ፣ አፒራንስ ማለት ሲሆን ፌኖሜና ባይምሮ ውስት የሚታይ ማለት ነው ።

ፌኖሜኖሎጂ የሚባለው የፍልስፍና መስክ በዚያ የተሰየመ ነው ። ሪያሊቲ የሚታወቀው ባይምሮ ውስጥ በሚገለጽ ምስል ነው የሚለው ፍልስፍና ።

ኤፒፋኒ ወይም ጥምቀት እግዚአብሄር ለሰው ወይም ለሰው አይምሮ የተገለጸበት ማለት ነው ።

በአጭሩ በዚህ እጅግ ጥልቅና ጥንታዊ ቃል ነው በቅጽል ፎርሙ ፋኖ ብሎ አማራ የነጻነት ትግል ግምባር ቀደም ጦረኞችን የሰየመው ።

ድል ላማራ! ድል ለኢትዮጵያ!!!

ሆረስ ዐይነ ብርሃን
አይ የስዶ ሳይንትስት ነገር፣ ትቀባጥር ቁጭ ብላ!

ፋና አፋን ኦሮሞ ዉስጥ መኖሩን ሳያዉቅ፣ ባኖ/ባና ግብፅ ዉስት መኖሩን ይቀባጥራል።

እፍረት የለሽዉ ስዶ ሳይንትስት ፋኖ እና ፋኖስ ምን ግንኝነት አላቸዉ ሳይል ዛሎ ስለ ህንድ አገር ቋንቃ ይቀባጥራል፣ ዉርደት።

የፋኖ ታርክ በኢትዮጵያ ደረጀ በ አደዋ ዘመን ሳይሆን በ2ኛዉ የኢጣሊያን ወራራ ጊዜ በፈፀመዉ ጀብደኝነት እንደምታወቅንም አደበስብሶ ለማለፍ ይቃጠዋል። ስዶ ሳይንትስት ነገር።

በመሰረቱ ፋኖ እና አማራነት በምንም አግባብ ልጣመሩ አይችሉም። ፋኖ የኢትዮጵያ ጀግኖች ነበሩ፣ አብዛኛዎቹም ኦሮሞዎች ነበሩ፣ ለኢጣሊያን ወራራ አልገዛም ብሎ ዱር የገቡ ና ጠላት ላይ የዘመቱ።

የዛሬዎቹ ፋኖ ተብዬዎች የታርክ እንክርዳድ ናቸዉ በገዛ ወገናቸዉ ላይ ጦር የነሱን ና የገዘ ሕዝባቸዉን የዘረፉ ና ያስዘረፉ፣ መጣርያቸዉም ፋኖ ሳይሆን ጀዊሳ ይባላል።

ለመሆኑ ስንት የጉራጌ ፋኖዎች ነበሩ በወቅቱ፣ ታርክ የምዘክራቸዉ?

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 09 Aug 2023, 08:33
by Selam/
አክሱም ቅዘኖ - ፋኖን እንጂ ወያኔን እኮ አይደለም ተርጉም የተባልከው።

“ወያኔ” ማለት ወየነ፣ ወገነ፣ ሽፈተ፣ አመፅ፣ እምቢአለ፣ አጋሚዶ፣ አረመኔ፣ አታላይ፣ ጨካኝ፣ ቀማኛ፣ ዘራፊ፣ ወራዳ፣ ሞራል የጎደለው ጋጠ-ወጥ፣ ሥርዓት አልባ፣ ማንዘራሽና፣ ቅሌታም ሆነ ማለት ነው።

Axumezana wrote:
05 Aug 2023, 16:31
ፋነነ፥ አኢምሮውን፥ ሳተ፥ ፈረጠጠ፥ ለያዥ፥ ለገናዥ፥ አስቸገረ፥
የሰው፥ ባህሪ፥ ሳይሆን፥ የእንስሳ፥ ባህሪ፥ነው።

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 09 Aug 2023, 11:04
by Right
DDT,
No if or but. No more debating on Ethiopia with the Abiye government.
A red line has been crossed. Like it or not, Abiye is tossed. You can’t stop the people. Remember a dead man walking.
Fano is everywhere. A new transitional government will be formed soon.
By the way Jawar and Merara Gudina want to join.

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 09 Aug 2023, 12:27
by Selam/
Is retarded Merera still alive?
Right wrote:
09 Aug 2023, 11:04
DDT,
No if or but. No more debating on Ethiopia with the Abiye government.
A red line has been crossed. Like it or not, Abiye is tossed. You can’t stop the people. Remember a dead man walking.
Fano is everywhere. A new transitional government will be formed soon.
By the way Jawar and Merara Gudina want to join.

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 09 Aug 2023, 13:38
by Right
Yes he is. He is suggesting for a new transitional government that he wants to join. So is the OLF.
What a turn of events. FANO must be helped by all means.

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 09 Aug 2023, 18:21
by Naga Tuma
እኔ ስለ ቃላት ታሪክ የተማርኩኝ ባለሙያ ኣይዴለሁም።

ቢሆንም የማዉቃቸዉ ቃላት ብዙ ናቸዉ።

ሁለተኛዉ የጣልያን ወረራ ግዜ ፋኖ ሆነዉ የታገሉ ኣዉቃለሁ። በዛን ግዜ ከወራሪዉ ጣልያን ጦር ጋር ወግነዉ ባንዳም የተባሉ እንደነበሩ ሰምቻለሁ።

ፋኖ ሲባል ክብር፣ ባንዳ ሲባል ትዝብት እያስታወሱ ዐዋቂዎች ያወጉ ነበር።

በአፋን ኦሮሞ ፋነ ሁለት ትርጉም ኣለዉ። ኣንዱ ኣብሮ ማለት ነዉ። ሌላዉ የእግር መዳፍ ማለት ነዉ። በአማርኛ ፋና የሚባለዉ ነዉ።

ድሮ ጫማ ማድረግ ሳይጀመር በፊት የሰዉ ፋነ/ፋና የተራመደበት መሬት ላይ ቀርቶ ይታይ ነበር። የጠፋ ሰዉ ፋናዉን ፈልጎ በመከተል ማግኘት ይቻል ነበር። ጠላት ወይም ሌባንም ፋናዉን በመከተል ይደርሱበት ነበር።

ጫማም ከተፈጠረ በኋላ ዕዉቁ ራስ አሉላ ጫማቸዉ 180 ድግሪ ዞሮ እንዲሰራላቸዉ ኣድርገዉ ጠላት እሳቸዉ ከሄዱበት ታቃራኒ እንዲሄዱ ያደርጉ ነበር የሚል ታሪክ መስማቴን ኣስታዉሳለሁ። ፋኖ ማለት እንደዛ ፋና ወጊ ወይም ጥበበኛ ነዉ ቢባል ስህተት ኣይመስለኝም።

በአፋን ኦሮሞ ፋነ፣ በአኣማርኛ ፋና፣ እና በእንግሊዘኛ ፉት ኣንድ ትርጉም ነዉ ያላቸዉ።

ይህ ለብቻዉ ያለ ቃል አይዴለም። የኣንድ ሰዉ አካላት ስያሜዎች በቀላሉ የማይረሱ ነቸዉ ብል ስህተት አይመስለኝም።

ስለዚህ እስቲ ከራስ ጀምረን እስክ እግር እንይ ወይም እንፈትሽ። በአፋን ኦሮሞ/በአማርኛ፣ እና በእንግሊዘኛ።

ሃሪ/፣ ሄይር
መታ/፣ ሜታ
አደ/፣ ሄድ
ፉለ (ፉልዱረ)/ፊት፣ ፍዩቸር
እጀ/አይን፣ ኣይ
አፋን/አፍ፣
ቆንቆ/ቋንቋ፣
ላጋ/ላንቃ፣
መንጋጋ/መንጋጋ ፣
እሬ/፣ አርም
ኦኔ/ወኔ፣
ኮዴ/ሆድ፣
ሀንዹረ/አንጡራ ፣
ቅን*ሪ/ቅን*ር፣ ክሊቶሪስ
ፊ*/፣ ፈ*
ሉከ/፣ ሌግ
ፋነ/ፋና፣ ፉት

እኔ እነዚህ ቃላት የጋራ መሠረት ወይም ተመሳሳይ ትርጉም ኣላቸዉ ብዬ መደመደም ኣልችልም። ሙያዉ ዬለኝም። ድምዳሜዉን ለባለሙያዎች እተዋለሁ። እኔ ቋንቋዎቹን ስለምናገር ሳነባቸዉ እና ስሰማቸዉ ይመሳሰሉብኛል።

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 09 Aug 2023, 19:02
by Horus
ዲዲቲ/ናጋ ቱማ፣
የማትጨርሰውን ነገር ለምን ትጀምራለህ? የዛሬ ሁለት ቀን ስለ ጸጋዬ ገብረ መድህን አነሳህ! ጥያቂ ስጠይቅህ ጸጥ አልክ ። መልስ ስለሌለህ ። እኔ አንተ መሰረተ ቢስ እውቀት አልባ ጥያቂ ባነሳህ ቁጥር ላስተምር አልችል ።

አንድ ፋና ማለት አብሮ ማለት አይደለም ። ያ ያንተ ኦሮሞኛ ከሆነ የራስህ ጉዳይ ነው ። ከፋና ጋር ሳንቲም ኝኙነት የለው ።
ቦሮሞኛአ ውስጥ ያሉ ጥቂት አይደለም በመቶና ሺ የሚቆጠሩ ከግዕ የተዋስካቸው አንተ ስለቋንቋ ስለማታቅ ኦሮሞኛ አድርገው ምትቆጥራቸ አሉ
በኦሮምኛ ፈነ ማለት የርምጃ ምልክት ነው አልክ ። አው ዘላንና አዳኞች በሰሳ ኮቴ ምልክት ነው የሚከታተሏእው ። የኦሮሞ ዘላኖች በከብትና እንሰሳ ኮቴን ኣቅጣጫ ማወቃቸው ትክክል ነው ።

ፋና በኮቴ ሳይሆን በብርሃን አቅጣጫ መከተል ነው ። ስለዚህ ሳታስብ ወደ እውቀት ሰፈር ገብተህ አፀባርቅ ።

በግር ኮቴ አቅጣጫ መፈለግ ፋና ሳይሆን ዲካ ወይም ዱካ ይባላል ። ስለ ዲካ ወይም ዱካ ስረ ቃል ውስጥ አልገባም

ስለዚህ ዝብ ብለህ መደዴ በድምጽ መመሳል ቃላት ማያያዝ አቁም ወይም ግዜ ወስደህ አጥና !

በተረፈ ራሳቸውን ፋኖ ይሉት የነበሩት ኦሮሞችና ነፍጠኛ ብለህ የሰደብካቸው ተገንጣይ ድምር አንተ ነህ !

እንደ ገና በተረፈ ከጉራጌ እንካ ስላንቲያን እርሳው ! ይልቅስ እነዚያን የሰፈራችን ወሮ በሎች ሰርተው እንዲበሉ አስተምራቸው ! የሚሉሽ ባልሰማሽ :lol: :lol: :lol: :lol:

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 09 Aug 2023, 20:05
by Naga Tuma
Horus wrote:
09 Aug 2023, 19:02

ምነዉ የጅብ ችኩል ሆንክ?

ጥያቄህን መልሼ ወደዚህ ስመለስ ይህን ኣነበብኩኝ። እስቲ በተራህ ወደዛኛዉ ርዕስ ሂድ እና ጥያቄዎቹን ከቻልክ መልስ።

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 10 Aug 2023, 19:51
by Naga Tuma
ኢትዮጵያ ዉስጥ ፋኖዎች ለሃገራቸዉ እና ሕዝባቸዉ ክብር መስዋዕት ሆነዉ መቆም የቅርብ ግዜ ታሪክ ነዉ። ባህር ኣቋርጦ ከመጣ ወራሪ ፊት ነዉ የቆሙት። ከሰሜን እስከደቡብ፣ ከምዕራብ እስከምስራቅ። ማስተዋወቅ ኣያስፈልጋቸዉም።

በተቃራኒ ቅጥረኞች፣ ተላላኪዎች፣ ወይም ባንዳዎች ሆነዉ ያገለገሉ ነበሩ። የእነሱንም የኣፍራሽነት ክፋት ማስተዋወቅ ኣያስፈልግም።

በቋንቋ መለያያትን እንደምክንያት ተጠቅሞ ክፍፍልን ያስፋፋዉ ከባህር ማዶ የመጣ ወራሪ ነበር። ያም ማስተዋወቅ ኣያስፈልግም።

ህወሃት በ1983 ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ህዝብ በተለያየ መንገድ ሲታገል ቆይቷል። በቋንቋ ልዩነት መደራጀትን ጨምሮ። እዚሁ ፈረም ላይ ሆረስ እራሱ የተለያየ አከባቢ የሚኖሩ ጉራጌዎች በጉራጌነታቸዉ ኣንድ ናቸዉ ብሎ ሲከረከር ያነበብኩኝ ይመስለኛል። ጉራጌነትን ነበር የሰበከዉ። ደግ ኣይዴለም ብዬ በዛ ኣልታዘብኩትም። መለስ "እንኳ ተፈጠርና" ያለዉን እንደ ከፋት ኣልቆጠርኩበትም።

ህወሓት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ የነበረዉ ትግል የሚናቅ ኣይዴለም። የዛን ግዜ አከባቢ የህወሓትን ስልጣን ለመቀናቀን ኦነግ ሊጣናከር ይችላል ያልኩት ኣንድ በወጣትነቱ ፋኖ ሆኖ የቆመ በትዝብት ዐይኖች ኣይቶኝ "እሳን ሱን ጋራ ሳና ከኣኒ ዬሮ ኣስ ገሀን ማል ሆጀቻ ቱረን" ብሎ ጠየቀኝ። እነዛ ከዛ ከላይ ተነስተዉ እዚህ ድረስ ሲደርሱ ምን እየሰሩ ነበር እንደማለት ነዉ። በተናገርኩት ኣፍሬ አንገቴን ደፍቼ ዝም ኣልኩኝ።

በዜና የሚሰማዉ የአማራ ንቅናቄንም በ1983 በኣዲስ አበባዉ ጉባኤ ኣንዴ ተሞኝቻለሁ እና በፕሪቶርያዉ ስብሰባም መሞኘት ዉርዳቴ ነዉ ብሎ በአማራነት ተነሳ ቢባል ይገባኛል።

በኦሮሞ ወይም አፋን ኦሮሞ ተናጋሪነት የታገለዉን በህወሓትነት መታገል ነበር፣ በጉራጌነት መታገል ነበር፣ ኣለ፣ በአማራነት መታገል ኣለ እና በኦሮሞነት መታጋል ዬለም ማለት እንዴት ያለ ሎጅክ እንደሆነ ኣይገባኝም። ከዛም በላይ የምያስፈልግ ሎጅክ ነዉ ወይ?

እርግጥ ነዉ ስልጣን ላይ ሆኖ ለኣንዱ ክፍል ማድላት ተገቢ ኣይዴለም። ያስጠይቃል። ስልጣን ላይ ሆኖ በሃገሩ ዜጎች ላይ ወንጀል መስራት ያስጠይቃል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ በማንነት ክፍፍል ለወደፊት ተስተካክሎ ማንነትን ባከበረ ወይም ባላከበረ ድርጊት መከበር ወይም መወቀስ ሊተካ የሚችል ይመስለኛል። እንድያዉም ዛሬ የምንታገለዉ ባህር ኣቋርጦ የመጣዉ ወራሪ ትቶት የሄደዉን ቅሪት ነዉ ቢባል ብዙ ኢትዮጵያዊያን ከቅጥረኞች ወይም ተላላኪዎች በፍጥነት የሚሸሹ ይመስላኛል። ካልተሳሳትኩ የ1967ቱ ኣብዮት ዉስጥ ኣቆርቋዥ ተብለዉ የተወቀሱት ዉስጥ ፋኖዎች እንደነበሩ እገምታለሁ።

ሆኖም በዚህ ግዜ ስንቶች ናቸዉ ማንነትን ከድርጊት ኣበጥረዉ ማየት የሚችሉት? ለምሳሌ የአፋን ኦሮሞ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ጉራግኛ፣ እና ሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያንን ማንነት ኣበጥረዉ የሚለዩት ስንቶች ኦትዮጱያዊያን ናቸዉ?

የፋኖነት ክብርን እና የቅጥረኛ ወይም ተላላኪነትን ህፍረት ኣበጥረዉ የማይለዩ ስንቶች ኢትዮጵያዊያን ናቸዉ?

Re: ፋኖ ምን ማለት ነው?

Posted: 17 Aug 2023, 15:23
by DefendTheTruth
Here Oromo cultural celebration of girls and young women ፋና ዻዉ (something like track or trace, but I could also be wrong in the translation).

#Faana Dhawuu# Qunnii Buqqifannaa,