Page 1 of 1

የአማራ አብዮትና የኦሮሙማ ወታደራዊ አገዛዝ

Posted: 05 Aug 2023, 15:30
by Horus
እኔ ሆረስ ቃላት በመክተፍ ሰው አላሰለችም ። በአጭሩ

አንድ፤
የአማራ ሕዝብ ተጋድሎ በሶሺያል ሳይንስ ምን ተብሎ ይጠራል? ሰው ሁሉ ያሻውን የዳቦ ስም ሊሰጠው ይችላል ። የዚህ ያማራ አመጽ ትክክለኛ ካራክተር አብዮት ይባላል ። ዝም ብሎ አመጽ፣ ዝም ብሎ የሽምቅ ዉጊያ፣ ዝም ብሎ መደበኛ ዉጊያ ብቻ አይደለም ። ሕዝባዊ አብዮት ወይም ፖፑላር ሬቮሉቲኦን የሚባለው ይህ ነው ። አንድ የሕዝብ አመጽ መቼ ነው ሕዝባዊ አብዮት የሚባለው ዝርዝር ገለጻ አስፈላጊ ከሆነ ሌላ ግዜ እንመለስበታለን ።

ስለሆነም ይህ የአማራ አብዮት የተለመውን አላማ ከግብ ካደረሰ ወደ ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮት ወይም ከዚያ ጠጋ ወዳለ ስርዓት ለዋጭ አገር አቀፍ ትግል ያድጋል ። ስለዚህ መላ ኢትዮጵያዊያን የአማራን ሕዝብ መደገፋቸው ላማራ ብቻ ሳይሆን ለራሳቸውም ነጻነት ሲሉ እንደ ሆነ ሙሉ ትክክለኛ ግ ን ዛ ቤ መያዝ የግድ ነው ።

ሁለት፤
ዛሬ በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በሶሺያል ሳይንስ ምን ተብሎ ይጠራል? ሰው ሁሉ በፈለገው የዳቦ ስም ሊጠራው ይችላል ። የወታደር መለዮ ለበሰ፣ ሱፍ በከረባት አደረገ፣ ወይም የዚና የዚያ ጎሳ ማሊያ አጠለቀ ዛሬ 4 ክሎ ያለው የኦሮሙማ አገዛዝ ወታደራዊ መንግስት ነው ። ላለፉት 5 አመታት አንድም ግዜ የተረጋጋ የሲቪል መንግስት አልኖረም ። ከሞላ ጎደል በኮማንድ ፖስትና በጦርነት የገዛ ወታደራዊ መንግስት ነበር ያቢይ ሪጂም። ዛሬ ከብልጽግና መፍረስና ከአገር አቀፉ ያስቸኳይ ግዜ (አገር አቀፍ ወታደራዊ አገዛዝ አዋጅ) አዋጅ በኋል ኢትዮጵያ መደበኛ ወታደራዊ መንግስት ሆናለች ።

ሶስት፣
የዛሬው የአማራ መግለጫ እንዳረጋገጠው በሁለት ቀናት ውስጥ አማራ በአማራ ጠቅላይ ግዛቶች ውስጥ ስለሚኖረው ስርዓት የአማራ አስቸኳይ ግዜ አዋጅ ያውጃል ። ይህ ደሞ የመንግስትና ስርዓት ለውጥ ይባላል። ኢትዮጵያዊያኖች ያን አዋጅ እንደ ዋዛ ባይመለከቱት ይሻላል። በዛሬቱ ኢትዮጵያ የጎሳን ስርዓት በግማሽ አፍርሶ አዲሱ የዜጎች ኢትዮጵያ መሰረት የሚጥል አዋጅ መሆኑን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ሊል ይገባል ።

አራት፣
ከአማራ ድል ቀጥላ የምትከሰተዋ ኢትዮጵያ ምን ትመስላልች ለሚለው የመጨረሻ ትያቄ የቀረነው የኢትዮጵያ ክፍሎች በያለንበት የየራሳችንን የቤት ስራ ሰርተን ለሶስተኛው ያስቸኳይ ግዜ አዋጅ። ለኢትዮጵያ አዋጅ ተዘጋጅተን የአብዮቱ ባቡር ላይ መሳፈር የግድ ይለናል ።