sarcasm wrote: ↑03 Aug 2023, 20:57
ወንድም አሠግድ፤ ሰላም የስራ ሳምንት እንዲኖንልህ ምኞቴ ነው። ስለ የትግራይ ዳያስፖራ ያለህ ምልከታ በጣም ከreality የራቀ ይመስለኛል። እንደሚመስለኝ ከሆነ፤ ባለፉት 3 የጦርነት ዓመታት የሆነው በደምብ ካለመንገንዘብ የሚነሳ ይመስለኛል። ጦርነቱ ከአንድ ፓርቲ ጋር የተደረገ የዜግነት ፖለቲካ (አሃዳዊ ስርዓት ተብሎ ይነበብልኝ) ለመመለስ የተደረገ ግጭት ኣድርገህ እንደምትመለከተው ይመስለኛል። ለዛም ይመስለኛል ሌላ ሰው ዳግም ቢሞክረውም የምትደግፈው።
የጦርነቱ ጥልቅ ትርጉም ግን ሁሉም ተፋላሚዎችና ሕዝቦች ልብ ያሉት ይመስለኛል። የአማራ ሕዝብ መሪ ይህ ሕዝብ የእንትና የእንትና ጠላት ነው .... ይህ ሕዝብ እስካልጠፋ ድረስ ...... ሲል የጦነቱ እውነተኛ ጥልቀትና ስፋት ለመላ ዓለም ግልጽ እያደረገ ነበር። ጦርነቱ የmillennia ቃልኪዳን እያፈረሰ እንደነበር ያልገባው በጣም ጥቂት እንደነበር ይመስለኛል። ኣሁን አማራ ክልል ያለው ሁኔታም የጦርነቱ ጥልቀት የገባቸው ሰዎች ግብግብ ይመስለኛል።
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም (ጦርነቱ የሃይማኖት ጦርነት ይመስል) እንደ
አንድ የጦርነቱ መሪ ተዋናይ (በሞራል በገንዘብ እና ጦርነቱ እስከ ታችኛው የሕብረተሰብ እርከን ደገፍ እንዲኖረው በማድረ)፤ የጦርነቱ ኣይቀሬ ጥልቅ consequence መቅመስዋ ሁሉም የጦርነቱ ጥልቀት የገባው ሰው የጠበቀው ነገር ነው። ፓትርያሪኩ በትናንቱ ሲኖዶሱ ለያፍነው በሞከረው ንግግራቸው "ፈጥነን
ወደ ውግዘት የምንገባ ከሆነ ግን ለቤተክርስቲያን መለያየት
ትልቅ የመሰረት ድንጋይ እንደማስቀመጥ ይቆጠራል" ሲሉ የጦርነቱ ጥልቀት የሚያሳይ አይመስልህም? ብየ ልጠይቅህ ኣሰብኩና፤ "ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው" ብለህ ትመልሰኛለህ ብየ ተውኩት።
To think that የኢትዮጵያ ህዝብ ጭውነትና በፈርሃ-እግዚአብሔር የተሞላ እለታዊ ኑሮ የትግራይ አባቶች በነአቡነ ጴጥሮስ ሲኖዶስ ስር ስለሆኑ ነው፤ ከነአቡነ ጴጥሮስ ሲኖዶስ ስር ሲወጡ ጭውነቱና ፈርሃ-እግዚአብሔሩ ይጠፋል ብሎ ማሰቡ በጣም preposterous ነው። እንዲያውም እውነታው ጭውነቱና ፈርሃ-እግዚአብሔሩ ያለው despite የነአቡነ ጴጥሮስ ሲኖዶስ ነው።
ሰላም Brother Sarcasm; ለሰጠኸኝ መልስ
ብዙ አመስግኛለሁ። ይሁንና ግን ባለፉት ሦስት ዓመታት
ምን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን
ለምን እንደሆነም ጭምር በሚገባ እገነዘባለሁ … የህወሃትን ክልላዊ ምርጫ የማድረግ ጥድፊያንም ጨምሮ ማለቴ ነው

አሁንም ቢሆን ግን ... እኔ በሚገባኝ መልኩ ‘
suicide’ መባል የሚገባው ድርጊት ህወሃትና ደጋፊዎቹ ጋር ሲመጣ ለፖለቲካዊ ጥቅም ‘
genocide’ ተብሎ የሚሰጠውን የተሳሳተ ትርጉም በፍፁም አልቀበለውም። ይህን በዚህ እንለፈውና …
እውነት ለመናገር … ህወሃት ‘ፊውዳላዊው’ እያለ የሚያጥላላውን ሥርዓት በጭራሽ፣ ‘አሃዳዊ’ እያለ የሚያወግዘውንም በቅጡ አላውቀውምና እነዚህን ሥርዓቶች ናፍቄ ‘ለመመለስ’ የምደግፈው ጦርነት የለም። እኔ ህወሃትን ‘የምጠላው’ በየትኛውም ሥርዓት ውስጥ ኣማራ ሆኜ
ሳገኝ የነበረውን የተለየ ጥቅም ስለነጠቀኝ ሳይሆን፥ በእራሱ አገዛዝ ውስጥ ኣማራ በመሆኔ
ማግኘት ያለብኝን ማህበራዊና ፖለቲካዊ መብት ለይቶ ስለነፈገኝ ነው።
በነገራችን ላይ ከህወሃት በላይ ኣሃዳዊ ሥርዓት የቱ ወይንም የማን ነው? የንጉሱ ወይንስ የፕሬዚደንት መንግስቱ? የሥርዓት መገለጫው የመሬት መካለል ሳይሆን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አስተዳደር (management system) እንደሆነ በሚገባ ትገነዘባለህ ብዬ አምናለሁ። ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተቋሞችንና አገልግሎቶችን በብቸኝነት በኣንድ ዘር ያሰወረረ ፓርቲ፥ ሜዳና ሸንተረሩን ሸንሽኖ ስላከፋፈለ ‘ፌደራላዊ ነው’ ብሎ ማሰብ ፌዝ ነው። ስለ ሐቅ ከሆነ’ኮ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በወረቀት ደረጃ አለ የሚባለው ፌደራሊዝም በአግባቡ መሬት ላይ ቢወርድ፥ ኣማራው ከማንም በላይ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ የሚሆንበት አንቀፅ አይደለም ዓረፍተ-ነገር የለም።
Sarcasm, ባህልና ኃይማኖት ልማዳዊ እንጂ ተፈጥሮዋዊ (hereditary) ባህሪ አይደሉም። ሰው ከሚሰማውና ከሚያየው ባህልን፣ ሀይማኖታዊ ሥርዓትን ይማራል። ሰለዚህም የትኛውም በጆሮ የሚገባ negative አመለካከትና በዓይን የሚታይ አፍራሽ ድርጊት ባህልና ኃይማኖት ላይ ተፅዕኖ (ለውጥ) ማምጣቱ አይቀሬ ነው። ለዛም ነው … የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ኃይማኖትን እና ሥርዓቷን አስፈፃሚ አባቶችን …
በተለይም ዘር ለይቶና ኣማራ የሆኑትን መርጦ … መስደብና ማንቋሸሽ ኣማኙ ማህበረሰብ (ኣማራው) ላይ ለውጥ ማምጣቱ አይቀርም ብዬ የማስበው። ይህን ደግሞ አትጠራጠር በቅርብ የምናየው እውነት ይሆናል። ህዝብን አስተሳስሮ ያለውን ቀጭን የሓይማኖት ክር በስድብና ነቀፋ መገዝገዝ መዘዝ አለው ስል ይህን ታሳቢ በማድረግ እንጂ፤ ኣንተ ተረድተኸዋል ብዬ እንደምገምተው … ኣማኙ ማህበረሰብ '
ከኣቡነ ጴጥሮስ ሲኖዶስ ስር ሲወጣ ጭዋነቱና ፈርሃ-እግዚአብሔሩን ያጣል’ በሚል የተሳሳተ አመለካከት አይደለም።
እስቲ ኣንተ ልትጠይቀኝ ባሰብከው 'ጠቋሚ' ጥያቄ ላይ ተንተርሼ እኔም ልጠይቅና ... ለሁለቱ ቤተክርስቲያን መለያየት ትልቅም ይሁን ትንሽ የመሠረት ድንጋይ የሚሆነው የኣዲስ አበባው ሲኖዶስ
ህገ-ወጥ አካሄድ ውግዘት ነው ወይንስ የትግራዩ ሲኖዶስ
ዘር-ገብ ድርጊትና ግብረገብ? በእኔ ፍላጎት ቢሆን መሠረቱን አይደለም ግድግዳና ጣሪያውን ጭምር በኣንድ ቀን ኣቆመው ነበር

ከተለያዩ መለያየት ነው! ኣሁን ትግርኛውን በትክክል ላስታውሰው ባልችልም ... ከብዙ ዓመታት በፊት ኣንዲት የሰሜን እህት "በእኛ ሀገር እንዲህ የሚባል ብሒል አለ" ብላ በኣማርኛ ተርጉማ ነግራኝ ነበር ...
ከነጣ እንደ ወተት መንጣት፥ ከጠቆረ ደግሞ እንደ ቁራ መጥቆር
ከዛ በተረፈ ግን ... Brother Sarcasm, የትግራይን ዲያስፖራ
ከሚገባው በላይ በደንብ አውቄዋለሁ 
እመነኝ ብዙ በሰው አእምሮ ለማሰብ የሚከብድ ባህሪና ልማድ እንዳላቸው በጆሮዬ ሰምቼ፣ በዓይኔ ተመልክቼ ተረድቻለሁ። ቀድሞ ሰምቼ ይፈፀማሉ ብዬ ለማመን ከተቸገርኩባቸው በላይ የሆኑ ኢሰብዓዊ ምክሮችን ከዚሁ ዲያስፖራ ኣፍ ሰምቻለሁ፣ ድርጊቶቹንም ተመልክቻለሁ።
መልካም ሰንበት ይሁንልህ, ወንድም ሳርካዝም
