Page 1 of 1

የሃገር መቅናት እና የሃገር መሸርሸር

Posted: 03 Aug 2023, 04:57
by Naga Tuma
ወደ እድሜ ባለጸጋነት የደረስኩ ነኝ ማለት ብችልም ከሁለት ትዉልዶች ግዜ በላይ ኖሬኣለሁ ማለት የምችል ኣይዴለሁም።

በእኔ ትዉልድ ዘመን ኣቡን ጴጥሮስን፣ ዘርዓይ ደረስን እና አብዲሳ አጋን ለያይቶ መጥቀስ ኣይቻልም ነበር። የኢትዮጵያ ድንቅ ጀግኖች እና ሰማዕታት ምሳሌዎች ነበሩ።

ፋኖ ከእኔ ትዉልድ በፊት ይታወቅ ነበር። ፋኖ እና አርበኛ ትልቅ ክብር የነበራቸዉ ስያሜዎች ነበሩ። ፋኖ ከተባለ ከሰሜን እስከ ደቡብ እና ከምዕራብ እስከ ምስራቅ የተከበረ ዝና ይመስለኝ ነበር።

የታሪክ ተማሪ ባልሆንም ስማቸዉ ኣብረዉ የሚነሱ ኢትዮጵያዊያንን ኣስታዉሳለሁ። ራስ አሉላ፣ ራስ አበበ፣ በላይ ዘለቀ፣ ጃገማ ኬሎ፣ ገረሱ ዹኪ ኣብረዉ የሚጠቀሱ ስሞች ነበሩ።

ታድያ በዚህ ትዉልድ ዘመን የበላይ ዘለቀ ሠፈር ልጆች ፋኖ ሲሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ እና ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ፋኖዎች እነ ማን ነበሩ የማይሉት ለምንድነዉ?