Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Assegid S.
- Member
- Posts: 950
- Joined: 11 Aug 2013, 07:11
-
Contact:
Post
by Assegid S. » 31 Jul 2023, 16:11
ተቀበል …
ተቀበል …
ንቆ ዝም ቢል … የፈራ መስሏቸው
ሲወዛወዙ … ምድር ጠቧቸው
ደግሞ ተነሳ …
ሊያስቀምጣቸው
ከደጅ
ጉድጓዱ … ሊወዝፋቸው
ተቀበል …
ያልበላውን ሲያክ … በጥፍር ጥርሱ
ለያዥ ቸግሮ … ለገናዥ ቄሱ
መጣ ያ ፋኖ … ፎጣ ለባሹ
በልኩ ቀዶ … ከፈን አልባሹ
ተቀበል …
ለውብ ሳዱላ … ትላንት ተዳሮ
ማልዶ ሸፈተ … ክላሻ አፍቅሮ ፥
ድሮስ መች ለምዶ … መኝታ ከአልጋ
ተዉት ከሜዳው …
ሲ ያ ጋ ድ መ ው ይንጋ
*** (
የቀለም ቃላቱን ስውር ፍቺ ለኣንባቢ ትቼዋለሁ)
-
Union
Post
by Union » 08 Aug 2023, 23:54
-
Assegid S.
- Member
- Posts: 950
- Joined: 11 Aug 2013, 07:11
-
Contact:
Post
by Assegid S. » 09 Aug 2023, 17:29
Revelations wrote: ↑08 Aug 2023, 23:48
ይሄንን ዘፈን/መዝሙር ስፈልግ ቆይቼ አገኘሁት::
ሰላም ወንድሜ Revelations; ለመዝሙሩ
እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። ከቤተሰብ እንደሰማሁት ከሆነ ... በትክክል ማስታወስ ከቻልኩ ... ዶ/ር ደረጀ ከበደ መሠረተ ክርስቶስ ( Bole Road ከኦሎምፒያ ትንሽ ገባ ብሎ የነበረ ቤተክርስቲያን) ውስጥ አገልጋይ (ዘማሪ) ነበር። ይህን መዝሙር እንኳን ኣሜሪካን ከገባ ቦኃላ እንደዘመረው በደንብ አስታውሳለሁ ("
ካድማስ ማዶ ያለች... " የሚለው ሓረግም ያንን ይገልፃል)። እንግዲህ እነዚህ ቀድሞ ስለ እምነታቸው
የታሰሩት፣
የተሰደዱትም ... አሁን ደግሞ
የሚያስሩት፣
የሚያሳድዱትም (እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩና ወይዘሮ አዳነች አበቤ ያሉት) እኩል 'የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች' ይባላሉ። ለነገሩ ቤተክርስቲያኒቱን ጭምር ወደ Shaolin Temple ቀይረዋት የለ ... ካራቴ እየተቀጣቀጡባት።
መልካም ሰንብት ... ወንድሜ Revelations

-
Assegid S.
- Member
- Posts: 950
- Joined: 11 Aug 2013, 07:11
-
Contact:
Post
by Assegid S. » 09 Aug 2023, 17:36
union wrote: ↑08 Aug 2023, 23:54
ሰላም ወንድሜ union; ለዘፈኑ
እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። ቆንጆ ምርጫ ነው! ፀሐዬ ዮሐንስም የሚወደድና የሚያኮራ ፅኑ ኢትጵያዊ ነው።
መልካም ሰንብት ... Brother union

-
Union
Post
by Union » 09 Aug 2023, 18:12
አመሰግናለሁ ወንድሜ አሰግድ።
I love this one too.
Assegid S. wrote: ↑09 Aug 2023, 17:36
union wrote: ↑08 Aug 2023, 23:54
ሰላም ወንድሜ union; ለዘፈኑ
እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። ቆንጆ ምርጫ ነው! ፀሐዬ ዮሐንስም የሚወደድና የሚያኮራ ፅኑ ኢትጵያዊ ነው።
መልካም ሰንብት ... Brother union