Page 1 of 1

የጉራጌ ልጃገረድ ከሰርጓ 3 ቀን በፊት ገንየ እንሾሽላ ሲታሰርላት ዛሬ እሁድን ማሰናበቻዬ ነው!!!

Posted: 30 Jul 2023, 21:14
by Horus

Re: የጉራጌ ልጃገረድ ከሰርጓ 3 ቀን በፊት ገንየ እንሾሽላ ሲታሰርላት ዛሬ እሁድን ማሰናበቻዬ ነው!!!

Posted: 30 Jul 2023, 23:10
by Horus
የጀርመኑ ፈላስፋ አማኑኤል ካንት እንዳለው ሳይንስ የተደራጀ እውቀት ነው፤ ጥበብ የተደራጀ ሕይወት ነው ። የጉራጌ ሕይወት ማደራጃ ጥበብ የጉራጌ ሴራ ይባላል ። የጉራጌ ስርዓት ማለት ነው ። ጉራጌ ለሁሉም ነገር ሴራ አለው ። አንዲት ሴት ልጅ ላቅመ ሄዋን ደርሳ ሚስት፣ እናት፣ የቤት እመቤት እና ክቡር የሰውና የህዝብ ወላጅ ፈጣሪ ለመሆን ስተጋጅ ትልቅ ደስታ ብቻ ሳይሆን ትልቅ ሴራ ነው ። ሴትና እናት የሚያከብር ካልቸር ነው የጉራጌ ሴራ ! አሁን ይህ ሴራ በሙሉ ክብሩ እየተመልሰ ነው ። 7 ቢሊዮን የአለም ሕዝብን ወልዳ ያሳደገች ሴት ነች!!!!

Re: የጉራጌ ልጃገረድ ከሰርጓ 3 ቀን በፊት ገንየ እንሾሽላ ሲታሰርላት ዛሬ እሁድን ማሰናበቻዬ ነው!!!

Posted: 31 Jul 2023, 00:09
by Horus

Re: የጉራጌ ልጃገረድ ከሰርጓ 3 ቀን በፊት ገንየ እንሾሽላ ሲታሰርላት ዛሬ እሁድን ማሰናበቻዬ ነው!!!

Posted: 31 Jul 2023, 00:18
by Horus
የቢሊኒየሩ ሳሟኤል ታፈሰ ልጅ እንሾሽላ !

Re: የጉራጌ ልጃገረድ ከሰርጓ 3 ቀን በፊት ገንየ እንሾሽላ ሲታሰርላት ዛሬ እሁድን ማሰናበቻዬ ነው!!!

Posted: 31 Jul 2023, 02:13
by Horus
አዲስ ሙላትን የፈተነችህው መልካሚ የሹርቢ ቀንዠ !!!

https://www.youtube.com/shorts/ospO3s1tmt0

Re: የጉራጌ ልጃገረድ ከሰርጓ 3 ቀን በፊት ገንየ እንሾሽላ ሲታሰርላት ዛሬ እሁድን ማሰናበቻዬ ነው!!!

Posted: 31 Jul 2023, 03:08
by Horus
ይህን ቪዲዮ የምላጥፈው ለትምህርት እንዲሆን ነው ። አደሬዎች ወይም ሃረሬዎች ብዙ ባህል ከጉራጌ ጋር ይጋራሉ ። ለምሳሌ ሰርግ በጉራጌ ሸባል ወይም ዠመኘ ይባላል ። አዠመኘ ሰርገኛ ማለት ነው። አደሬዎች ሸዋል ይሉት ነበር ። አሁን ምን እንደ ሚሉት አላውቅም ።

እንሾሽላም ልክ እንደ የገንየ በስልጤም በአደሬዎች ዘንድ ነበር ። እዚህ ላይ ቁስላ የሚሉት ስርዓት ከእንሾሽላና በጉራጌ የጥፍር ከሚባለው ባህል ጋር አንድ ነው። እነዚህ የጉራጌ፣ ስልጤና ሃረሬ ልጃገረዶች ከሰርጋቸው አንድ ቀድሞ ጥፍራቸው ተቆርጦ ለሰርጋቸው አዲስ ጥፍር ያበቅሉና ያን አዲስ ጥፍር እንሶስላ የሚታሰርበት ቀን ነው እዚህ ሃረግ ላይ የለጠፍኩት ። ጥፍር መቁረጥ አሁን በሴራ የተከለከለ ነው፤ በጣም ስለሚያሳምም ።

ያን የጥፍር በ ዓል ይመስለኛል ቁስላ የሚሉት ሃረሬዎች! ግን ይህው እንደ ሚታየው ባህሉን ሙሉ በሙሉ አልረሱትም ። ግ ን እዚም በስልጤም በጣም ደክሟል፣ ተበርዟል ።

የጥፍር ባህል በአረቦች ዘንድም አለ ይባላል ።

Re: የጉራጌ ልጃገረድ ከሰርጓ 3 ቀን በፊት ገንየ እንሾሽላ ሲታሰርላት ዛሬ እሁድን ማሰናበቻዬ ነው!!!

Posted: 31 Jul 2023, 17:21
by Horus
አረቦች፣ ህንዶችና ቱርኮች የሂና ወይም እንሶስላ እለት (ምሽት) ይሉታል ብሎ አንድ ሰው ዛሬ ነገረኝ ።

በነግራችን ላይ እንሾሽላ የምንለው ሶስና ወይም ዋተር ሊሊ (የዉሃ ሊሊ) አበባ ነው ። ዛሬ ላይ ቀለሙ ከእጽ ስር ይሰሩታል እንጂ ሌላ ቦታ ከቀይ ወይም ቢጫ ሊሊ አበባ ነው ይሰሩት የነበረው በተለይ ጥንታዊ ግብጾች ! እንሾሽላ ያካባቢያችን ሴቶች ሁሉ ባህል ነው ። አተገባበሩ ቢለያይም!!!

Re: የጉራጌ ልጃገረድ ከሰርጓ 3 ቀን በፊት ገንየ እንሾሽላ ሲታሰርላት ዛሬ እሁድን ማሰናበቻዬ ነው!!!

Posted: 01 Aug 2023, 02:57
by Horus
በጉራጌ ብዙ የነገሱ ሴቶች ታሪክ አለ ። ከቃቄ ወርድወት (ወለተ ቃቄ ማለት ነው) ጀምሮ ይህው ዛሬ ጉራጌ ሴቶቹን እና እናቶቹን ከፍ አድግርጎ የሚያነግስ ባህል ማቆሙ በጅጉ ያኮራኛል !!! ጉራጌ ቤት ሲሰራ ያን ግዙፍ ጣራ የሚሸከመው ምሰሶ ችባን ወይም እችባ ይባላል ። እንከን የለሹን የጉራጌ ቤተሰብና ማህበረሰብ እንደ ችባን የምታቆመው የጉራጌ ሴት ነች፣ የጉራጌ እናት ነች! እኮራበታለሁ !!!