የኢሳያስ አፈወርቂ ጥበብ ምን ላይ ነው?
እንደ ሜታፎር ሁለት ልጃገረዶችን እንውሰድ። አንዷ ልጃገረድ እጅግ ቆንጆ ብዙ ጎረምሶች የሚመኟት ሴት ነች ። ሌላኛዋ ልጃገረድ የእኔ ብጤ መደበኛ ሴት ነች ። ታዲያ ያቺ ቆንጆ ሴት ይህን ያንን ጎረምሳ ስትይዝና ስትለቅ አንድም ወንድ ከልብ ሳይወዳት ቀረና እሷም ባል አልባ ሆና ኖረች ። ሌላኛዋ ሴት አንድ የተጠጋትን ጎረምሳ በትክክል በመያዝ እሱም ባል አድርጓት እሷም ደጋፊና ጠባቂ ወንድ አግኝታ ኖረች ይባላል።
የአቢይና ኢሳያስ አሁናዊ የጂኦፖለቲካ ፉክክር የላይኛው ሜታፎር ይመስላል ። ኤርትራን እንደ ሁልተኛዋ ልጃገረድ ብናያት አንድ ጥያቄ አንጎላችን ውስጥ ይነሳል ።
ለምንድን ነው ላለፈው 30 አመት በሩሲያና ኤርትራ መሃል ዛሬ የተፈጠረው አይነት መተሳሰር ያልነበረው? ዛሬ ምን ስለሆነ ኢሳያስም ሙሉ በሙሉ ወደ ሩሲያ፣ ሩሲያም ሙሉ በሙሉ ወደ ኤርትራ ያዘነበሉት? እንደ እኔ ግምት ይህ ነገር የወረሞው ቡድን የሰራው ግዙፍ ስህተት ወይም ክህደት ውጤት ነው ።
ሩሲያ ለኢትዮጵያ ያላት ክብር፣ ወዳጅነትና ፍላጎ ጥንታዊ፣ ታሪካዊና እና ጠንካራ ስለሆነ ለብዙ ዘመን ሩስኪዎች ኢትዮጵያን አስቀይመው ከሌላ የቀጠናው መንግስት ጋር እስፔሻል አሊያንስ መፍጠር አልፈለጉም ። ይህም ስለሆነ አሜሪካና አውሮፓ ኢትዮጵያን በሚሊታሪ እስከ መያዝ ድረስ ባለፈው 4 አመት ሲሰሩ በሩሲያ ጥብቅ ድጋፍ ነበር አቢይ አህመድ እራሱ በስልጣን ሊቆይ የቻለው ።
አቢይና አላዋቂው የወረሙማ ክሊክ ልክ እንደ ቆንጆዋ ጂል ልጃገረድ የራሱንም ሕዝብ፣ ቻይናን፣ ሩሲያን ፣ ራሷ አሜሪካን ሌሎችንም አንዴ ትግሬን ፣ አንዴ አማራን፣ አንዴ ጉራጌን፣ አንዴ ሱማሌን፣ እያስቀየመ አንድም የልብ ወዳጅ ሳይፈጥር ባክኖ ባል አልባ ሴት፣ ሚስት አልባ ወንድ ሆኖ የቀረ የጂሎች ስብስብ ነው።
ዛሬ ላይ ሩሲያ አቢይ አህመድ ማለት ምን አይነት አቋም አልባ ደካማ ነገር እንደ ሆነ አውቀውታል ።
በሌላ በኩል ኢሳያስ አንድ ሁሉም የሚያውቀውና የሚያምነው ጉልበት (ዉበት) አለው፤ ጂኦግራፊ፣ ባህር፣ ጂኦግራፊ ፣ ባህር ። እስከዛሬ አሜሪካኖችም ኤርትራ ጋራ በማበር ኢትዮጵያን እንዳያጡ፣ ሩሲኪዎችም ከኤርትራ ጋር በማበር ኢትዮጵያን እንዳያጡ ለ30 አመት ደፍረው ያልገቡትን የቀይ ባህር ሽኩቻ ዛሬ ሩሲያ በግልጽ ወስዳዋለች ።
ይህም የሆነው ኢትዮጵያ መሪነት የሌላት አገር፣ ዲፕሎማሲ የሌላት አገር ፣ በውስጥ ዶሜስቲክ ፖሊሲዋ ባዶ የሆነች፣ የራሷን 120 ሚሊዮን ግዙፍ ኃይል በመደዴዎች ዱላ በታትና ስርዓት አልባ መረን የሆነች እና በአለም ላይ እከሌ የሚባል ውክልናና ድምጽ የሌላት በጥቂት እረኛ አላዋቂዎች ባክና የወደቀች አገር ስለሆነች ነው።
ኢሳያስ ዛሬ ላይ ያሳየው ዊዝደም አስደናቂ ነው ። መንገድ የጠፋቸው የትግሬና የወረሞ ወጠጤዎች አንድ ምሽት ሰክረው በጦዙ ቁጥር ሌላ አንድ ጦርነት ከኤርትራ ጋር በሚለፋደዱበት የጨቅላዎች ፖለቲካ ኢሳያስ ቁርጥ አድርጎ ከሩሲያ ጋር በማበር በዋናነት ኤርትራ ምንም አይነት የሚሊታሪ ጥቃት ከማንም ወላ ትግሬ፣ ወላ ወረሞ፣ ወላ ጂቡቲ፣ ወላ ሱዳን ሆነ ግብጽ እንዳሞከርበት እያደረገ ነው ።
ሙሉ እድሜውን የለፋላት ኤርትራን ህልውናዋን ሳያረጋግጥ መሞት አለመፈልጉ ትልቅ ዊዝደሙ ነው። አሁን ትግሬዎችና ወረሞች ካሜሪካ ጋር ሊግማሙ ይችላሉ ። የአሜሪካ አሽከር መሆን ከመጣ ደሞ ኬኒያን የሚያሸንፍ የለም ። አቢይ አህመድ ከኪኒያ ቀትሎ ጁኒየር አሽከር መሆን ብቻ ነው የሚችለው ።
የቀድሞ አቤ ጉበኛው ‘የከብት እረኛ የሕዝብ መሪ ይሆን ዘንድ ከቶም አይችልም ‘ እንዳለው!
ሆረስ ኃይለ ብርሃን
የአቢይ አህመድ አሊ ወረሙማ ክሊክ ለምን በአፍሪካ ቀንድ ጂኦፖለቲካ ተሸነፈ?
Last edited by Horus on 30 Jul 2023, 16:05, edited 1 time in total.