Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15409
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የወደፊቱ የኢትዮጵያ ሥነ-መንግሥት ምን መሆን ይኖርበታል? ሀ) ፌደራል ( ልሙጥ-ጎሳ ፌደራል ያልሆነ)? ለ) ክፍለ-ሀገራዊ?ፕሬዚዳንት ወይስ ጠ/ሚንስተር ወይስ ንጉስ?

Post by Abere » 26 Jul 2023, 14:38

የወደፊቱ የኢትዮጵያ ሥነ-መንግሥት ምን መሆን ይኖርበታል? ሀ) ፌደራል ( ልሙጥ-ጎሳ ፌደራል ያልሆነ)? ለ) ክፍለ-ሀገራዊ?ፕሬዚዳንት ወይስ ጠ/ሚንስተር ወይስ ንጉስ?

ማሳሰቢያ፤

ሁሉም የስነ-መንግስት አወቃቀሮች በ21ኛው ክፍለ ዘመን በተለያዩ አገሮች የሚከናወኑ ናቸው - አሁን በኢትዮጵያ ካለው ልሙጥ-ጎሳ ፌደረሽን በስተቀር። ኋላ ቀር አስተዳደሮች አይደሉም አንዳንድ ጥራዝ ነጠቅ ካድሬዎች ለመስፈራርቾ እንደሚያወሩት አይደለም።

Abere
Senior Member
Posts: 15409
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የወደፊቱ የኢትዮጵያ ሥነ-መንግሥት ምን መሆን ይኖርበታል? ሀ) ፌደራል ( ልሙጥ-ጎሳ ፌደራል ያልሆነ)? ለ) ክፍለ-ሀገራዊ?ፕሬዚዳንት ወይስ ጠ/ሚንስተር ወይስ ንጉስ?

Post by Abere » 26 Jul 2023, 15:42

ኢትዮጵያ ተዘፍቃ ለምትገኝበት የፓለቲካ አሮንቋ እና የዕልቂት አዙሪት መቶ በመቶ ምንስዔው ልሙጥ-ጎሳ ፌደሬሽን አወቃቀር ይህን መሰረት አድርጎ አንድ ልሙጥ ጎሳ የሚወክል (ለዚያውም የልሙጥ ጎሳውን ሙሉ ድምጽ ሳያገኝ) ጠቅላይ ሚንስትር መሪ ማድረግ ነው። ይህ አደገኛ የሆነ የፓለቲካ አስተደደር ነው - እጅግ ያፈነገጠ ነው። ልሙጥ የጎሳ ፌደራል ሙሉ መብት እና ጥቅም የሚሰጠው ለአንድ ጎሳ ሲሆን ሌሎች በአንድ ል ኡላዊት አገር የሚኖሩ ግን የባዕደ አገር ሰው ተደርገው ይወሰዳሉ - መጤ ይባላሉ። ህግ አያውቃቸውም። የሚገርመው ደግሞ ይህ ሌሎች ከልሙጥ ጎሳው ፌደሬሽን ውጭ ያሉት ግን ከሌላ ጎሳ ፌደሬሽን የወጣ ጠቅላይ ሚንስትር መሪያቸው ይሆናል። ሊመራ የሚችለው ነገር ግን የለም - የእራሱን ጎሳ ጥቅም በሌሎች ላይ አስገድዶ ከመጣል በስተቀር።

Post Reply