Page 1 of 2
በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 25 Jul 2023, 22:53
by Horus
(1) ኢዛና
(2) አግአዚያ
(3) አክሱም
(4) ነጋሲ ግድር
እስከነ ትክክለኛ ትርጉማቸው እና ስረ ቃላቸው! ሆረስ ኃይለ ብርሃን አስፈላጊ ሲሆን ይገልጻቸዋል!
ሰላም ዋሉ !
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 26 Jul 2023, 16:56
by Horus
እንዴት ነው! እስቲ አዲስ ልብሰ ሲመት ከተሰጣቸው ውስጥ አንዳቸው ኢዛና ምን ማለት እንደ ሆነ ጀባ ቢሉን?

Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 28 Jul 2023, 03:43
by Horus
ከላይ ከጠቀስኳቸው 4 ታሪካዊ ቃላት የአክሱምን ትርጉም ለቅቄያለሁ ። ሶስት ተኩል ይቀራል ። ግማሹ ሹም ማለት ምን እንደ ሆነ የማን ቃል እንደ ሆነ ነው ።
ከዚህ በታች በዚህ ጉዳይ ላይ ትክክለኛ መረጃና እውቀት ለሚሹ በከፍተኛ ምርምር ላይ የተመሰረተው የ Jean Doresse (Director of Archaeological Research in Ethiopia) 1956 classic ልጠቁማችሁ ። (ETHIOPIA: Ancient Cities and Temples). እኔ የመጀምሪያው እትም ነው ያለኝ ። Published in 1956 as "Au Pays de la Reine de Saba L'ETHIOPIE Antique et Moderne"
In this book page 27 ላይ Gadarat, the ruler of Habashat and Negasi Geder, the king of Axum are mentioned. Only I Horus have the clue to the mystery of these personalities!
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 28 Jul 2023, 04:07
by Horus
I could not find a single 1956 copy! It is amazing. Here is the Google search!
https://www.google.com/search?q=Ethiopi ... s-wiz#ip=1
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 28 Jul 2023, 04:43
by Meleket
እየተዝናናን እንማማራ . . . “ኤርትራ ውስጥ ኣንድ ኣግኣዚያን( ነጻ ኣውጪዎች) የሚባል ትምህርት ቤት ውስጥ ይማር የነበረ፡ ኢዛና የምንለው ‘ጀሮው ትልቅ ስለሆነ ‘ኣዛን’ ብለን በቅጽል ስሙ የምንጠራው ( ‘እዝኒ’ ማለት ጀሮ ማለት ነው
) የነበረ፡ የአቶ ነጋሢ ልጅ፡ ሰፈራቸው እንኳ “ገጀረት” አካባቢ እንደነበር አስታውሳለሁ። ታድያ ኣንዴ ለሽርሽር አዱሊስና መጠራ ከስከሰና ቖሓይቶ ሄዶ እንደተመለሰ ያጫወተንን አስታወስከን። እነዚህ ስልጣኔዎች ቅድመ ክርስትና ቅድመ ኣዅሱምም ናቸው ብሎን ነበር። ኣዅሱም ማለት የውሃ ሹመኛ እንደማለት ነው የሚለው ትርክትና መላ ምት እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ‘ዅስሚ’ ማለት ታቦት ወይ የአንድ ኣካባቢ ደብር ማለት መሆኑም ሊዘነጋ ኣይገባም ብሎ ጠቆም ኣድርጐን ነበር። ለምሳሌ በትግርኛ “ዅስምኹም እንታይ ኢዩ” ከተባልክ “የቀያችሁ ደብር ወይ ቤተክርስትያን ታቦቱ ምንድን ነው” እንደማለት ነው ብሎ ነግሮን ነበር የገጀረቱ የአቦይ ነጋሲ ልጅ ኢዛና!
አንዴም ጉራዕ የተባለ ቀዬ ደርሶ እንደተመለሰም ባደረገው ምርምር “ግዕዛችን ‘ከሰመ’ የሚለውን ቃል ሽኻል ሸኸለ፡ መትከል ተኸለ። ብሎታል እንግዲህ እንደ ሃውልቶቹ መትከልንም መቸከልንም ያሰማል ማለት ነው ልመራመር ላለ ሰው፡ ብሎ እሱ በገባው መሰረት የተፈላሰፈብን የገጀረቱ የአቦይ ነጋሲ ልጅ ኢዛና፡ እንደ ኣግኣዚያን ሃገሩንና ህዝቡን ነጻ ለማውጣት ወደ ትግል ሜዳ ተቀላቅሎ ነበር የሚሉ ኣካላት አሉ፡ ያኔ የተያየን እስከዛሬ ድረስ . . . " ሃሪፍ ትረካ ነው እንዳትሉ እንጂ!
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 28 Jul 2023, 13:17
by Horus
መለከት፣
በጣም ጥሩ ጅማሮ ነው !!
የኔ ትኩረት በጠቅስኳቸው 4 ቃላት ላይ ብቻ ይሆናል (ኢዛና፣ አክሱም፣ አጋዚ እና ግድር)።
(1) አጋዚያን ነጻ አውጪ ማለት ነው የሚለው ማንና እንዴት እንደ ተጀመረ ባላወቅም ስህተተ ነው ። ግእዝም ሆነ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ሴም ቋንቋዎች ነጻ፣ ነጻነት ለሚለው ጽንሰ ነገር የታወቁ ቃላት አሏቸው ። ነጻ፣ ንጹህ፣ ጽራይ፣ ጥራይ፣ ጥሩ ሃራ፣ አርነት፣ ወዘት ። ጋዝ እና አጋዝ ነጻ ማለት አይደለም ።
(2) ነጋሲ ንጉስ ማለት ስለሆነ ያ ክርክር ውስጥ የለም ። ነገር ግን ግድር ምን ማለት ነው? አንዱ የአክሱም ንጉስ ነጋሲ ድግር ይባል ስለነበር ።
(3) ኢዛና ጆር ትልልቅ ሰው የሚለው ፍጹም ፍጹም ስህተት ነው ። አው በትግርኛ እዝኒ ማለት ጆር ማለት ነው ። በጉራጌኛ እንዝን ይባላል። ቃሉ በአረብኛም እንዝ ነው ። አንድ ታላቅ ንጉስ ግ ን በፍጹም ጆሮ ትልልቅ ተብሎ አይጠራም ። ኢዛና አይደለም በሁሉም የሴም ቋንቋዎች በሳንስክሪት (ህንድ) ቋንቋ ውስጥ ሁሉ ያለ ትልቅ ቃል ነው ።
(4) አክሱም ባህረ ነጋሽ ማለት ነው የሚለው መላ ምት አይደለም ። በሊንጉስቲክ ኤቪደንስ ላይ የቆመ ድምዳሜ ነው ። አክሱም ታቦት ማለት የሚለው ስህተት ብቻ ሳይሆን ከታሪክ ይቃረናል። አክሱም ሲመሰረት ከርስትና አልነበረም፣ ስለዚህ ታቦት የሚለው ጽንሰ ነገር ሊኖር አይችልም ። ያ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ደብርህ የት ነው የሚለው አባባልና አክሱም የሚባለው ኪንግደም በህሳቤ እንኳን አይገናኙም ።
ካስማ እና ባላ! አያቴ ጸሎት ሲጀምር መሬት ያለ ካስማ የዘረጋህ ሰማይ ያለ ባላ ያቆምክ ፈጣሪ ተመስገን ይል ነበር ። አው ካስማ ችካል ነው ። ግ ን የአክሱም ከተማ ወይም ግዛት ከመቆሙ በፊት ስለመቃብሩ ቦታ ታስቦ በሃውልቶቹ መተከል ላይ ስም ወጣለት የሚለው እንዲሁ የተሳሳተ ግምት ነው ። በዚያን ግዜ ከነበሩት የግእዝ ፣ ሂሚራይቲክ፣ ግሪክ እና ሌላው ቀርቶ ላቲንም ፋርሲም ተናጋሪዎች በነበሩበት ከተማ ለሃውልትና ትክል ድንጋይ ካስማ የሚል ቃል ሊጠቀሙ አይችሉም ነበር።
ሰላም
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 29 Jul 2023, 01:34
by Horus
መለከት፣
አጋዚያን ማለት ነጻ አውጪ ነው ብለህ ተቃውሜ ስለነበር አሁን ለምን የሚለውን ላብራራ ። የቃሉ ስረቃል (ኢቲሞሎጂ) እና ስነቃል (ፊሎሎጂ) ውስጥ ገብቼ አንባቢ አላሰለችም ። ቃሉ ከየተ እንደ መነጨ ማወቅ ለሚሹ ለማብራራት ፈቃደኛ ነኝ። ቃሉን ስራዬ ብሎ ለፈለገ በጉራጌኛ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የሴም ቋንቋዎች ውስጥ ሊገኝ ይችላል ብዬ አስባለሁ ። ነገር ግን በብችኝነት ጥቅም ላይ ያለው በጉራጌኛ ቋንቋ ውስጥ ነው ።
ጋስ ወይም ጋዝ ማለት ጦር፣ ዘመቻ፣ የጦር ኃይል ማለት ነው ። ለጦር የተሰለፉ ወታደሮች ጋሰኘ፣ ጋዘኘ (ጦረኛ) ይባላሉ ።
አጋስ፣ አጋዝ የሚለው አጠቃቀም እንደ ወረደ አዋጊ፣ ጦር አደራጅ የሚል ትርጉም ሲኖረው በሰሜኑ ክፍል ትርጉሙ ተለውጦ አጋዚያን የተባለው እሱ ነው ። ቃሉ እርባታውን ተከትሎ ከሄድ አጋዚያን ሳይሆን ጋዚያን፣ ጋዘኛ፣ ጋዘኘ መባል አለበት ።
አጋዝ የሚለው አጠቃቀም ትክክለኛ ቃል አባጋዝ፣ አበጋዝ፣ ባለጋዝ የሚሉት ሲሆን ያ የጦር አባት፣ የጦር ጌታ፣ የጦር አዛዥ፣ ጄኔራል ማለት ነው። ስለዚህ ተራ ተዋጊ ወታደር ጋዘኘ ሲሆን ጦረኛ ወይም ተዋጊ ማለት ነው ። የጦር መሪ አበጋዝ ይባላል ።
ጉራጌዎች ጦር፣ ዘመቻ፣ ዉጊያ፣ ወታደር፣ የጦር መሪ ፣ የጦር አለቃ ለማለት ሌላ ቃል የላቸውም ። ያላቸው አንድ ቃል ነው። ጋዝ ጦር፣ ሰራዊት ነው ። አበጋዝ የጦር ጌታ ነው ።
ስለሆነም አጋዚያ ነጻነት ጋር ቀጥታ የትርጉም ት ስስር የለውም ። ነገር ግን አንድ የጦር ዘመቻ (ጋዝ) የሚደረገው አገር ከወራሪ ነጻ ለማውጣት ከሆነ ያ በርግጥም የነጻነት ጋዝ ወይም የአርነት ጋዝ ይባላል ። በጉራጌኛ ቋንቋ ውስጥ ነጻነት አዲስ ቃል ነው ። በሰፊው ጥቅም ላይ ያለው አርነት የሚለው ቃል ነው ።
ባጭሩ የአጋዚያን ትክክለኛ ትርጉም ይህ ነው።
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 29 Jul 2023, 02:17
by Meleket
ግሩም ትንታኔና ምርምር ነው ወንድም Horus ቀጥልበት፦
‘ገረብ ዓረና ወያነ ትግራይ’ በተሰኘው መጸሓፉ ካሳ ሃይለማርያም ረዳ ካባቱ ከብላታ ሃይለማርያም ካሳ የተተረከለትን የመጀመርያው ወያኔ ታሪክ (1933-38) ለእትመት በ2010ዓ.ም ኣቅርቦ ነበር። “ጋዝ’ የሚለውን ቃል በአንተ ዓይነት ኣጠቃቀም ተጠቅሞበታል። ጹሑፉ በትግርኛ ነው፡ ዓፋሮችና የትግራይ ደገኞች እርስ በእርስ ጦር ይዛመቱ ነበርና፡ ይህ ሰዉየው የተሳተፉበት ውልና ስምምነት ይህን “ወራር ጋዝ” ያሉትን ለማስቀረት እንደወሰኑ ተርከዋል። ‘ኣቦ ጋዛት’ በማለትም ኣንተ “ኣበጋዝ” ያልከውን ትርጉም በተላበሰ መልኩ ተጠቅመውበታል። እንዲህ ሲሉ፦
ንኣብነት ምስኩሎም ኣቦ ጋዛት ርክብ ገይርና ዝዘተናን ብደረጃ ምርድዳእ ወራር ጋዝ ከይካየድ ዝገበናን ክረምቲ 1933 ዓ.ም. እዩ ነይሩ።
ኣግኣዚ የሚለውን ቃል እግዚእ፡ ጎይታ፡ ገዛኢ ከሚለው ጋር ያዛምዳሉ ኣንዳንድ ተመራማሪዎቻችን፡ ትክክለኛው ጌታችን ደግሞ ከኃጢኣትና ከባርነት ቀንበር ነጻ እውጪ መሆኑን መቼም ሁላችንም ኣንስተውም፡ እንስማማበታለን።
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 29 Jul 2023, 02:46
by Horus
መለከት፣
በትክክል! ልክ እንደ አቤ አብርሃም ነገር አዋቂ ነህ! አው ወራር ጋዝ አለ፤ አርነት (አረና) ጋዝ አለ ።
ቅድም ስጀምር ነገሩ እንዳይሰፋ ወደ ቃሉ ኢቴማና ፍሊሊያ አልገባም ያልኩት ልክ እንዳልከው አጋዚና አግዚኦ፣ እግዚአብሄርና ገዛኢ ገዢ፣ ግዛት ፣ ወዘተርፈ ውስጥ ላለመግባት ብዬ ነው ። በስረ ግንዳቸው ካንድ ኢቴማ ስለሚበቅሉ !
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 29 Jul 2023, 04:49
by Zelku
ምናምን ቀማምሳችሁ አትፈላሰፉ፡፡ የምን መቀባጠር ነው? ሆሆ ሰዉ እየለቀቀ ነው ጃል!
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 29 Jul 2023, 13:24
by Horus
አጼ ኢዛና ምን ማለት ነው? ክርስትና ሲቀበል ለምን ስሙን ወደ አጼ አብርሃም ለወጠ? ይቀጥላል።
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 29 Jul 2023, 15:09
by Horus
መለከት፣
ገጀረት ዛሬ በትክክል የት ነው ያለው? የኢዛና ልደት ቦታ ነው ወይ? Thanks. ለምን ካልክ? ቃሉ ጠቃሚ ትርጉም ስለያዘ።
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 01 Aug 2023, 03:14
by Horus
ነገ የኢዛና ትርጉም እለጥፋለሁ ። ዛሬ የነጋሲ ግድርን ጉዳይ ልዝጋው ። ነጋሲ ግድር ከኢዛና በፊት የገዛ ንጉስ ነው ። በትግሬ ወይም ኤርትራ ውስጥ ገጀረት እሚባል ቦታ ያለ ይመስለኛል ። የቃሉ ስር ግ ን ምን እንደ ሆነ የሚያውቁት አይመስለኝ ። በእኔ እምነት ገደራት (ገጀራት) ነጋሲ ግድር የተወለደባቸው ሕዝቦ ወይም ቦታ መሆን አለበት ።
ግድር የሚለው ህያው ሆኖ እስከ ዛሬ ያለው በጉራጌኛ በተለይም በክስታኔኛ ውስጥ ነው ። ግድር ማለት ታላቅ ማለት ነው ። ግድር ሰብ ዎበል ማለቅ፣ ታላቅ ሰው ማለት ነው። ድሮ ነጋሲ ትልቁ፣ ዳሪዩስ ትልቁ፣ አሌክሳንደር ትልቁ የማለት ባህል ነበር ። በዚያ መልክ ነው ይህ ቅድመ ኢዛና ያክሱም ንጉስ ነጋሲ ግድር የተባለው ። በዚያን ዘመን አባባል ገደራት ወይም ገጀራት ማለት ታላቆች፣ ነጋሲዎች እንደ ማለት የነበረ ይመስለኛል !! ማን ያርዳ የቀበረ ! ማን ይንገር የነበረ !!!!
የኢዛና ትርጉም ይቀትላል
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 01 Aug 2023, 05:08
by Meleket
ግሩም ምርምር ነው ወንድም Horus ግፋበት።
ኣባ ጋስፓሪኒን ጠቅሶ ኣንድ ጽሑፍ እንዲህ ኣስነብቦናል ኤርትራም የመንም ውስጥ ስለሚገኙ የቦታ ስያሜዎች።
ሰሓርታን = ሰሓርቲ፣ ባድዕ = ባጽዕ (ምጽዋዕ መሆኗ ነው)፣ ሰራት እና ሰርዋ የተሰኙ ሁለት አውራጃዎች ከሰራዬ ጋር፣ ሰንዓ ከሰንዓፈ ጋር (ሰንዓ- ፊ ማለት ሰንዓ ይህችውና ማለት ነው ይሉናል)። ዳብር (ዛና የተባለ ከሰንዓ ኣጠገብ የሚገኝ ስፍራ)፣ ጽልማ፣ ሊባን፡ ደምበሳን = ድንበዛን፣ ዓንሰባ፣ ምራራ፣ ግኒ-ሳባ፣ መሪብ= መረብ፣ ገደረት = ገጀረት እንዲሁም ሳዋ የሚባሉ ስፍራዎችና ከተሞች በደቡባዊ ዓረብ ማለትም በየመን እንዲሁም በምስራቅ ኣፍሪካ ማለትም በኤርትራም ይገኛሉ። ብሎ አስፍሯል።
በተመስሳይ መልኩ ተስፋዬ ገብረኣብ ነፍሱን ይማረውና፡ ስለ አንድ አስመራ ውስጥ ገጀረት አካባቢ ስለተወለደ “ዘግዱር” ስለተባለ ታሪከኛ ሰዉዬ በጻፈው የቅርብ ጽሑፍ፡ እሱም ኣባ ጋስፓሪኒን ጠቅሶ፡ ዘግዱር ወይም ገደረት የተባለ የአካባቢያችን ንጉስ ከኣዱሊስ በታንኳ ወደ የመን ተሻግሮ ጦርነት ስለማድረጉ፡ ሳንቲሞች ላይ ስሙ ተጽፎ ስለመገኘቱ ተርኮ፡ በ "“ገደረት” እና “በገጀረት” መካከል ስላለው ግንኙነት ግን ለማረጋገጥ አልቻልኩም” በማለት ጽፏል ቀዩ ዘመን በተሰኘው መጸሓፉ።
የአስመራ ገጀረት በልማድ ከሁለት ተከፍሎ "ገጀረት-ዓቢ" እና "ገጀረት-ንእሽቶ" ይባላል። እንግዲህ ገጀረት ማለት ገደረት ወይም Horus እንዳለው ከክስታኔው ግድር ጋር ግንኙነት አለው ብለን ካሰብን፡ “ገጀረት-ዓቢ” ማለት “ትልቁ ትልቅ” እንዲሁም “ገጀረት-ንእሽቶ” ማለት ደግሞ “ትልቁ ትንሽ ወይ ትንሹ ትልቅ” ሊሆን ነው ማለት ነውን? ቀያቸው ከአምበራ መጠቃ ሳይሆን ከኤርትራዋ ገጀረት ወይም ከየመኗ ገደረት የሆኑ ሰዎች ስለ ስያሜው ትርጉም ምን እንደሚሉ ብንሰማ ደግሞ መልካም ነበር። 
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 01 Aug 2023, 09:41
by Meleket
ወደ መሠረታችን ወደ ግዕዝ ካተኮርን ደግሞ ጌዶር የሚለውን ቃል ወታደር ሠራዊት ብሎ ይተረጉመዋል የነ ውልፍ ሌስላው 1987 የግዕዝ መዝገበ ቃላት። ታዲያ 'ጌዶር' የሚለው ቃል እንደ የክስታኔው ቃል 'ግድር' ብዙም ከገደረትና ከገጀረት ኣይርቅም። በተጨማሪም ጌዳር የሚለው የግዕዝ ቃልም ዘላን ተብሎ ተተርጉሟል።
የጌዶርና የጌዳርን ትርጓሜ ያካፈልናችሁ እንዲያው የምርምር አድማሳችንን ለማስፋት ያህል ነው፤ የገጀረትና የገደረትን የስም ትርጓሜ የሚገልጹልን እስኪገኙ።
እርግጥ ነው "ጌዶር" የሚለው ቃል ትርጉም፡ ከአዱሊስ ወደ የመን በታንኳ ተመሙ ከተባሉት ጦረኞቹ ቅመአያቶቻችን ታሪክ ጋር የሆነ አንዳች ግንኙነት ይኖረው ይሆናል፡ ተመራማሪዎች ቀስ ብለው ይነግሩናል ብለን እናስባለን፡ እኛ ኤርትራውያኑ የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 01 Aug 2023, 14:06
by Horus
መለከት፣
ትክክል። እያንዳንዱ ቃል አጠቃቀም ከቦታ ቦታና ከግዜ ግዜ እንዴት ኢቮልቭ እንዳደረገ ቢመረመር ሁሉም ካንድ ስረ ቃል እንደ ተነሱ ይገኛል ። በጣም ጥሩ አድርገው የእኔን ሊንጉስቲክ ወይም ኢቲሞሎጂካል ግኝት ደግፈሃወሃል ። ዘግዱር የሚለው ነው ቃሉ ፤ ዘ ግድር ማለት በግዕዙ ።
ልብ በል እኔ አሁን ስለዘረዘርካቸው የኤርትራና የመን ቦታዎችና ሰዎች አንብቤ ወይም አውቄ አይደለም፤ ዠን ዶሮሴ ሳንብ ነጋሲ ግድር ሲል ነው በምናገረው ቋንቋ ውስጥ መኖሩን የተገነዘብኩት ።
አንተ ልክ እንደ አቤ አብርሃም! አረብኛ የምታውቅ ስለሚመስለኝ ይህን ልንገርህ ። ግድር ወይም ዘግዱር (ታላቅ፣ ግሬት) የሚለው ቃል አረቦች ከዲር ወይም ያ ከዲር የሚሉት ነው ። ትርጉሙም ያው ታላቅ፣ ሃያል፣ ማለት ነው ።
ገጀረት የሚለው ጋር ት ስስር አለው የምለው በዶሮሴ መጽሃፍ ገጽ 27 ጋዳራት (ገደረት) የሃበሻት ንጉስ ሆኖ የሚጠቀሰው ። ከየመን ወደ ኢትዮጵያ የተሻገረ ይለዋል። ነጋሲ ግድር ያክሱም ንጉስ ሆኖ ነው የሚጠቀሰው ።በእኔ እምነት የአንድ ነጋሲ ቤተሰብ ስም ይመስለኛል ። ጋዳራት የሃበሻዎች ንጉስና ነጋሲ ግድር ያክሱም ንጉስ አንድ ሰውና ባንድ ዘመን የኖሩ ላይሆኑ ይችላል። ግ ን የቃሉ አጠቃቀምና ትርጉም አንድ ነው ። አረቦቹ ዛሬም ከዲር ካዲር የሚሉትን ማለት ነው።
ነገ ደሞ ኢዛናን እንመለከታለን
በነገራችን ላይ ሟቹ ማርቲን በርናል ጥቁር አቲና በሚለው ግዙፍ ምርምሩ (Martin Bernal, Black Athena, vol.3) የጉራጌኛ ሴም ቋንቋዎች ብዙም ያልተለወቱ ኮንሰርቫቲች ስለሆኑ ሴሚትክ ቋንቋ ከትንታዊ ግብጽ ጋር ያለውን ትስስር ለማሳየት ጠቃሚ ብሎ ብዙ ብዙ ነገር ጽፏል ። የግሪክ ስልጣኔ ከግብጽ ስለመወሰዱ ሊንጉስቲክ ኤቪደንስ በሚለው 3ኛ ቮልዩም በሰፊው የተጠቀመው ኢትዮሴሚቲክ ጉራጌኛን ነው ።
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 12 Aug 2023, 00:41
by Horus
ይቅርታ አድርጉልኝ፤ የኢዛና ትርጉምና ስረ ቃል ነገ ፖስት አደርጋለሁ።
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 12 Aug 2023, 01:05
by union
ጭሱን አረጋጊው ነብሴ ፣ የነቀልሽው አንቺ ነሽ ሆረስ አይደለም
Zelku wrote: ↑29 Jul 2023, 04:49
ምናምን ቀማምሳችሁ አትፈላሰፉ፡፡ የምን መቀባጠር ነው? ሆሆ ሰዉ እየለቀቀ ነው ጃል!
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 12 Aug 2023, 01:38
by Horus
ኢዛና ምን ማለት ነው?
ምንም ቴክኒካል ሃተታ ሳላበዛ በጥሬ ትርጉሙ ማለት ንጉስ፣ መስፍን አለት ነው ። የቃሉ ብልት ሁላችሁም የምታውቁት ‘ጃ’ (ዣ) የሚለው ነው ። ኃያል፣ ታላቅ ማለት ሲሆን ዣን፣ ዣን ሆይ፣ ዣን አሞራ የምንለው ነው።
ቃሉ የተወለደው በጥንታዊት ግብጽ ሲሆን እነሱ ካህ ወይም ቻህ ያሉት ይመስለኛ ። ከዚህ ብዙ ሳይርቅ ይዘውት ያሉት ኢራናዊያን ሲሆኑ እነሱ ‘ሻ’ (ሻህ) ይሉታል። ሻ (ሻህ) ንጉስ ማለት ሲሆን ሻሃንሻ ንጉሰ ነገስት ማለት ነው ።
በኢትዮጵያ ያለው አጠቃቀም ከፊቱ ቅጽል ተቀጥሎበት ንጉስ (ንኩሽ)፣ ነካሺ (ነጋስሂ) ማለትም ካህ በሚለው የግብት ስሩ ነው።
ከዚህ በታች እንደ ኤቪደንስ ልዩ ቃላትና አግባቦን አቀባለሁ ።
(1) በአቢይ ጾም ግማሽ የምናከብረው ሆሳዕና (ሆሻና፣ ሆሳና) የንጉሱ መግባት በዓል ነው ። ሆሳን ወይም ሆሻና ንጉስ ማለት ነው ።
(2) በህንዶች ቅዱስ ቋንቋ (የህንዶች ግእዝ) ሳንስክሪት ሆሻን ፣ ሾሻን መስፍን ማለት ነው።
(3) ካልተሳስትኩ በእብራስጥ ሹሻን ልዕልት ፣ ንግስት እንደ ማለት ነው፣ የሴት ስም ነው
(4) ከአረሜይክ ቋንቋ ጀምሮ በሁሉም የሴም ቋንቋዎች ኧዣ፣ እዣ፣ አዚዝ፣ አዣዥ፣ ገዢ፣ ነጋሲ፣ ንግስት፣ ንጉስ፣ ማለት ባለስልጣን ፣ ገዥ። ሩለር ማለት ነው ።
(5) በጉራጌ አንዱ የጉራጌ አገርና ጎሳ እዣ ይባላል
(6) እንዲሁ በጉራጌኛ ሰነ (ሸነ) ኃይል ማለት ሲሆን ስልጣን፣ ስልጤ ለሚሉት ቃላት ስር ነው
(7) እንዲሁ በጉራጌ ሰነቻ የሚዳኙ ሽማግሎች ናቸው
(8) በአረብኛ ሃሳን፣ ሃሰን፣ ሁሴን ማለት ኃያል ፣ ታላስ ማለት ነው ። መስፍን እንደ ማለት ነው
(9) ሰነ ኃይል ማለት ነው ብዬ ነበር ፤ ጸና፣ ጽኑ፣ ጽናት ኃይል፣ ትንካሬ ማለት ነው
(10) በጎደር ዘመን የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ የነበሩት ራስ ዘ ስላሴ የጉራጌ ሕዝብ አስተዳደር አጉራ ጠነ ይባላል ብለዋል ። አጉራ ጠነ ማለት ራስ ገዝ አገር ማለት ነው ። ጠነ (ሰነ) ከላይ እንዳልኩት ገዝ (ገዠ፣ ኧዠ) ማለት ነው።
በአጭሩ ኢዛና ማለት ኧዣኛ፣ ኧዠኛ ... ባለ ኃይል፣ ገዢ፣ ንጉስ ማለት ነው ። ንጉስ ኢዛና ንጉሰ ነገስት የሚል ማረግ መያዙን አላቅም ። አድርጎ ቢሆን ኢዛነዛ ወይም ኢዛነዣ ይባል ነበር ። ንጉሰ ነግስት በሚለው አግባቡ ማለት ነው ።
እነዚህ ለግዜው እማስታውሳቸውን ብቻ ነው ። ሌሎቻችሁ ሻ፣ እሻ፣ እዛ፣ ኢዛ፣ ትዛዝ ቀመስ ቃላት አክሉበት ።
Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
Posted: 14 Aug 2023, 11:53
by Meleket
Horus wrote: ↑12 Aug 2023, 01:38

ግሩም ፍልስፍና ነው ወንድም Horus ምርምሩን ቀጥልበት፡ ግፋበት!
ኤርትራችን ውስጥ እንግዲህ ከኤዛና ሆነ ኢዛና ጋር የሚመሳሰሉ አንዳንድ ቃላትን እንጨምርልህ። ዓዜን፡ ኳዜን፡ ቢዘን፣ ላህዜን፡ ምድሪ ዜን፡ የሚባሉ የቀዬ ስሞች ኣሉ። በተጨማሪም መስፍንቶ የተባለች እጅግ ታሪካዊ ቀዬም ኣለችን . . . መረብን ስትሻገር ደግሞ ሓውዜን የሚለው ቃል ይጠብቅሃል ማለት ነው።
ሽመዛና (ሽመጃና) የሚባል ታሪካዊ ስፍራም ኣለን።
እስቲ በነዚህ ቃላትም ተፈላሰፍባቸው የሴም ይሁኑ የኩሽ ቃላቶቹ ኤርትራ ውስጥ ቁልጭ ብለው እስከዛሬ ድረስ ኣሉ። የምርምር ውጤትህን እዚህ ለብዙሃን ማጋርትህንም እጅግ አድንቀንልሃል፡ በርታ ብለናል እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።