Page 1 of 1

ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 15 Jul 2023, 17:14
by Revelations
ከውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ጉራማይሌ ንግግር እንድያቆም ትመክራላችሁ ተብሎ ሲጠበቅ ጭራሹኑ እናንተ አገር ውስጥ ያላችሁት ተዘፈቃችሁበት ምነው?! ኧረ ተው! ባይሆን የውጩን ቋንቋ መጠቀም ካለባችሁ ሙሉውን ያንን ቋንቋ ተጠቀሙ::

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 15 Jul 2023, 17:19
by Revelations

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 15 Jul 2023, 17:30
by Revelations

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 15 Jul 2023, 18:22
by Revelations
ዓይኔን ሰው አማረው፤

የሰው ያለህ የሰው!
አያ ብር አለንጋው የሌጌዎን መሪ፣
ልጅ፤ እስከ ማእዜኑ ያስማንዲዮስ መሪ፤
አያ ደሙ በኔ የሳጥናኤል መሪ፣
የቀበሮ እንግዳ በቤቱ አሣዳሪ፣
ተበግ ተቀበሮ ቀበሮን አክባሪ፣
ቀበሮን ወደ ቤት በግን ገደል መሪ፣
የበግ ለምድ ለበሶ በጐችን አባራሪ፣
በቀበሮው አዋጅ አገሩን ወራሪ፣
በለሰለሰ እርሻ አሜኬላ ዘሪ፣
እጅግ ተጠንቅቆ አባቱን አፍቃሪ፣
አባቱን አፍቅሮ እናት አቃጣሪ፣
እናቱን አቃጥሮ አባት አሣሣሪ፣
አባት አሣሥሮ በናቱ መካሪ፣
በናቱ ላይ መክሮ አዋጅ አስነጋሪ፣
በግራ የቆመው ሲመለስ ወደ ቀኝ፣
እኔም በናታችሁ ጐዳናው ሳይርቀኝ፣
በዚያን ጊዜ እናንተን የሚያይ ሰው ናፈቀኝ።

ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 15 Jul 2023, 18:38
by Revelations
ጥንተ ሀገሬ ሆይ ጥንተ ተደንግሎ፤
ሕጻናቱ ታርደው ያንቺም ልብ ቆስሎ፤
ሕዝቡ ተሰደደ አንቺን ተከትሎ፤
የሕጻናቱን ደም አዘክሪ ኵሎ፡፡
አስጨነቀኝ ስደትሽ፤
እመቤቴ ተመለሽ፡፡

ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 15 Jul 2023, 18:54
by Revelations
ተቀምጬ

ተቀምጬ፣
የሐዘን የትካዜ ሙዚቃ ስሰማ፣
ጓደኛዬ ሁኖ የሲጋራው ጢስ፣
ጢሱ ቅታሬውን እየጎንጎን ክራሴ በላይ፣
የብቻ መሆኔ አዳኛ ሲሳይ፣
ጢሱና ሙዚቃው እየተባበረ፣
የስሜቴን ስሜት የልቤን የውስጡን እየበረበረ፣
ሲያወጣው ፈልቅቆ፣
እኔን እኔነቴን፣ ራሴን ከውስጡ፣ ከውስጤ ሰልቆ፣
ፈርፍሮ፣
ፈልፍሎ፣
ፈታ ፈታታና፣
ደም - ብረት፣ ሐሞት - መርዝ ሊያናግረው ሲል፣
ድንገት ድምጽ ሰማሁ፣
አንዲቱ መዝጊዬ ሰማሁ ስትንኳኳ፣
ገብቶ የነበረው ልቤን ሊያመሰኳ፣
የሙዚቃው ስልቱ፣ የጢሱ ውበቱ በደንገት ቀጥ አለ፣
የበሬም መንኳኳት በዚያው ልክ ቀጠለ፡፡


ዮሃንስ አድማሱ

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 15 Jul 2023, 19:38
by Revelations
ጎበና እና አሉላ

አጥንቱን ልልቀመው መቃብር ቆፍሬ ፤
ጎበናን ተሸዋ አሉላን ተትግሬ፤
ስመኝ አድሬያለሁ ትላንትና ዛሬ፤
ጎበናን ለአሞራ አሉላን ለጭሬ፡
ተሰባሰቡና ተማማሉ ማላ ፤
ጎበና ከሸዋ ተትግሬም አሉላ
ጎበና ሴት ልጁን ሊያስተምር ፈረስ
አሉላ ሴት ልጁን ጥይት ሊያስተኩስ
አገሬ ተባብራ ካልረገጠች እርካብ
ነገራችን ሁሉ የእምቧይ ካብ የእምቧይ ካብ።

ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 15 Jul 2023, 21:12
by Horus
ወይ ካላካበቱ ወይም ካላምታቱ
ማን ለማ ይሰጣል ከዚያ ከሱረቱ


መንግስቱ ለማ
እስረኞቹ ግጥሞቼ

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 16 Jul 2023, 00:58
by Revelations
እገበያ መሀል ፈስ እያንዛረጡ
አውራ ጎዳና ላይ ዳቦ እየገመጡ
ቤተክስያን ገብቶ ትምባሆ እየጠጡ
እንዲህ ነው ወይ ጣሊያን አልጋ ላይ ሲወጡ?

ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 16 Jul 2023, 01:36
by Revelations
በሳህን ሲሆ ነው የሚያምረው ወጥህ
ድንች አትላክልኝ ከመሬት ነቅለህ

ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 16 Jul 2023, 02:17
by Horus
Revelations,
እነዚህን ሁለት ነገሮች ስለ መንግስቱ ለማ ታውቅ ኖሮዋልን?

አንድ፣ ጣሊያን ተባሮ የሃይለ ስላሴ መንግስት እንደ ገና ሲደራጅ ማጆሪቲው የዙፋን መኳንንቶች የኢትዮጵያ አንደኛ ብሄራዊ ቋንቋ እንግሊዝኛ እንዲሆን ሲከራከሩ መንግስቱ ለማ ገና ሁለተኛ ደረጃ ሳይጨርስ ዙፋን ቀርቦ አማርኛ ቋንቋ እንዴት የማንነታችን መገለጫ እንደ ሆነ ኃይለ ስላሴን ያሳመነ ምሁር መሆኑን!!!

የዚህ ድንቅ ሊቅ አባት የታወቁ አለቃ ባለቅኔ ሲሆኑ እናታቸው ጉራጌ እንደ ሆኑ! ልክ የታላቁ ምኒልክ ትህትና ከጉራጌ እናቱ እንደ ወረሰ ሁሉ መንግስቱ ለማም ትሁትነትና ሚዛናዊነት የወረሰው ከጉራጌ እናቱ ነበር!!

Re: ጉራማይሌው ቢቀር

Posted: 16 Jul 2023, 08:07
by Revelations