Page 1 of 1

ቤተ-አማራ ----> የክርስትና መዲና፤ የሓዲስ ኪዳን መንበር። አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል. ግሸን - አምባሰል

Posted: 13 Jul 2023, 11:02
by Abere
ቤተ-አማራ ----> የክርስትና መዲና፤ የሓዲስ ኪዳን መንበር። አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል. ግሸን - አምባሰል

በኢትዮጵያ ጥንታዊ የእምነት መንበር ማለትም በኦሪት ዘመን መስዋዕት የቀረበበት በሀዲስ ኪዳን ደግሞ መስቀሉ የከበረበት እና መሰረተ ክርስትና የተጣለባቸው ቦታዎች በአማራ ክፍለ ሀገር ይገኛል። በኦሪት ዘመን መስዋዕት የቀረበባቸው ቦታዎች አንደኛው ጣና ገዳም ሲሆን በዚህ ገዳም ጽላት ዘሙሴ ከእስራዔል መጥቶ ለሺ አመት የተቀመጠበት ( ወደ ትግራይ በዘመኑ ንጉስ በትዕዛዝ እስከ ሄደበት ) እና ካህናት መስዋዕት የተደረገበት ነው። ሁልተኛው የኦሪት (ብሉይ) ዘመን ቦታ አማራ ሳይንት ተድባበ ጽዮን ማርያም ነው።
በሀዲስ ዘመን የድህነት ምልክት የሆነው ክርስቶስ የተሰቀለበት በመሰቀሉም ሞትን ድል አድርጎ የሰውን ልጅ ያዳነበት መስቀል ነው። ይህ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ያረፈው በተመረጠው ቅዱስ መስቀለኛ ቦታ በቤተ-አማራ አምባሰል ጊሸን ነው። ጊሸን ለበርካታ አመታት የኢትዮጵያ ቤተ-መንግስት ነበር እስከ ግራኝ አህመድ ወረራ ድረስ።

የሀዲስ ኪዳን እና የክርስትና መዲና የሆነችው አምባሰል ተገቢው ልማት ከተደረገ የመንፈሳዊ ህይወት ፈላጊዎች የስበት ከተማ እና ክልሉም ተጠቃሚ ይሆናል።