Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የጦርነቱ ባለቤት ማን ነበር!??? By Moges Zewdu Teshome

Post by sarcasm » 10 Jul 2023, 07:43

የጦርነቱ ባለቤት ማን ነበር!???


በወቅቱ ጦርነቱ የብል[ፅ]ግና እና ህወሓት የስልጣን ሽኩቻ ነው ብላ በግልፅ የፃፈችና ዋጋ የከፈለችው ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ ብቻ ናት። እንዴት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ይረሳል? እናንተ ብትረሱት እንኳን ሌላው ኮማ ውስጥ ስላልነበር ያስታውሳል።

የጦርነቱ መዋቅራዊ መነሻ ምክንያቶች የኢህአዴግ መፍረስና የብል[ፅ]ግና እና ህወሓት ሽኩቻ፣ የኤርትራ መንግሥት ቂም፣ የአማራ ብሄርተኞች ርስት እና ማንነት ማስመለስ ያደረ ፍላጎት፣ የኢትዮጵያኒስት ጎራ ጊዚያዊ ስካር( myopic) እና የውክልና ጦርነት ናቸው። በዚህ ውስጥ የአማራ ብሄርተኛ የነበረው ኃይል(በተለያየ መልክ የተደራጀው) የጦርነቱ ደጋፊ ብቻ ሳይሆን ዋና ባለቤትም ነበር!

የህወሓት ቡድን ይጥፋ እንጂ ሌላው እዳው ገብስ ነው ያለው ማን ነበር? ህወሓት የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ናት ብሎ የዘመተው ማን ይሆን? የኢትዮጵያ እና አማራ ትንሣኤ የሚረጋገጠው በህወሃት መቃብር ላይ ነው ያለችው ሱዳን ነበረች? ኢትዮጵያን ሲኦል ገብተንም ቢሆን እናፈርሳታለን ብሏል የህወሓት አመራር ያለው ፑቲን ነበር(በርግጥ ሰውዬው አላለም)? መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከአማራ ህልውና ጎን ሆኖ ወራሪ ኃይሉን ይደምስስ ያለው የማይታወቅ መንፈስ ነበር!?

ተዉ እንጂ ጎበዝ እያንዳንዱ ነገር በቪዲዮ እና ፅሁፍ ተሰንዶ ተቀምጧል እኮ። የጦርነቱን ሂሳብ እናወራርድ ካልን እያንዳንዳችን ድርሻ ነበረን( መጠኑ ቢለያይም)። በባህላችን ማፈር የሚባል እሴት ነበር እኮ።

ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ምን ተፈጠረ? ያው "ሌባ ሲሰርቅ ሳይሆን ሲካፈል ነው የሚጣላው" የሚለው ብሂል መልስ ይሆናል። እኩል የጦርነቱ ባለቤት ሆነው ሳለ የጦርነቱ ውጤት (spoils of war) ላይ ተጣሉ። ሌላ ተአምር የለውም።


እኔ በበኩሌ ቢያንስ ገና አመት እንኳን ያልሞላውን ኹነት አልረሳም። I am sorry to disappoint you, but I do not suffer from dementia ( short memory) yet. ይሄው ነው!
Please wait, video is loading...