Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Horus
Senior Member+
Posts: 42727
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by Horus » 10 Jul 2023, 01:57

ወዳጄነህ የፖዘቲቭ ሳይኮሎጂ አቀንቃኝ ነው። ለጥቂት አመታት በጣም የገነነ ፋድ ነበር positive psychology. አሁን ኮግኒቲቭ ሳይንስ፣ ኢቮሉሽነሪ ሳይኮሎጂና ኒውሮሳይንስ በጣም ስለመጠቁ ፖዘቲቨ ሳይኮሎጂ ከቢሄቨየር ሳይንስ ወደ ማይለይበት ደረጃ ደርሷል ። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ገና እያወቁት ስለሆነ ብዙ ሆሆታ ይደረግበታል ። የዴካርት I think therefore I am የሚለው የማይንድ የበላይነት ተሽሯል ። ይህን የማያውቁ ሰዎች ናቸው በዚያ ላይ ግዜ የሚያጠፉት ። ዛሬ ያለው ፓራዶግማ mind is embodied! በቃ! አቢይ አህመድ ይህን የምናብ የበላይነት ጠጥቶ ነው ይህና ያንን እየሰበከ የትም ፈቀቅ ማለት ያቃተው ። Reality is fact. ሃሳብ ባዶ ምስል ነው። በስሜት ያበደ ፖዘቲቭ ሃሳብ ሺ ግዜ ብናላምጠው ውስጡ ምንም የለውም ። ይህ ነው ያቢይና አማካሪዎቹ መሰረታዊ ውድቀት! በሌለ ነገር ነው የሚያምኑት! የሌለ ፈለግ እና ፋና ነው የሚከተሉት !

Axumezana
Senior Member
Posts: 19150
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by Axumezana » 10 Jul 2023, 02:39

The path for success ! Idea/vision/ plan + action = result!

Idea - vision- mission - goals-plan - action - monitoring - refine as required( Idea- vision-mission- goals -plan action) repeat the cycle in dynamic and continuous manner.

Selam/
Senior Member
Posts: 17831
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by Selam/ » 10 Jul 2023, 07:58

ወያኔ ወጣቱን በጫት ሱስ አንደንዝዛ ስታበቃ እራሷ ደንዝዛ ጓያ እንደሰበረው ሰው ተሽመደመደች።

አብይና ወዳጄነህ እየተለሳለሱ ፖስቲቭ ኤነርጂ (positive energy)፣ ኤምፕቲ ዩር ማይንድና (empty your mind) ቅብርጥሶ የሚሉት ወጣቱን በድጋሚ ለማነሁለልና ከስረ-እምነቱ ለመንቀል ነው። ኤምፕቲ ዩር ማይንድ የሰይጣን ስራ ነው። ክርስቲያን የሆነ ሰው በፆም በፀሎት አእምሮን በእግዚአብሄር መንፈስ ይሞላል እንጂ ባዶ ለመሆን ሜዲቴት አያደርግም። ፖሲቲቭ ኤነርጂም የሚባለው አእምሮን በባዕድ ሀይል (alternate sources of energy) ለመሙላት ታቅዶ የተቀረፀ የክርስትና ሃይማኖት ጠላት (anti-Christ) ነው። ይኸንን እውነታ የመንፈስ አባቶች ማስተማር አለባቸው።

Horus wrote:
10 Jul 2023, 01:57
ወዳጄነህ የፖዘቲቭ ሳይኮሎጂ አቀንቃኝ ነው። ለጥቂት አመታት በጣም የገነነ ፋድ ነበር positive psychology. አሁን ኮግኒቲቭ ሳይንስ፣ ኢቮሉሽነሪ ሳይኮሎጂና ኒውሮሳይንስ በጣም ስለመጠቁ ፖዘቲቨ ሳይኮሎጂ ከቢሄቨየር ሳይንስ ወደ ማይለይበት ደረጃ ደርሷል ። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ገና እያወቁት ስለሆነ ብዙ ሆሆታ ይደረግበታል ። የዴካርት I think therefore I am የሚለው የማይንድ የበላይነት ተሽሯል ። ይህን የማያውቁ ሰዎች ናቸው በዚያ ላይ ግዜ የሚያጠፉት ። ዛሬ ያለው ፓራዶግማ mind is embodied! በቃ! አቢይ አህመድ ይህን የምናብ የበላይነት ጠጥቶ ነው ይህና ያንን እየሰበከ የትም ፈቀቅ ማለት ያቃተው ። Reality is fact. ሃሳብ ባዶ ምስል ነው። በስሜት ያበደ ፖዘቲቭ ሃሳብ ሺ ግዜ ብናላምጠው ውስጡ ምንም የለውም ። ይህ ነው ያቢይና አማካሪዎቹ መሰረታዊ ውድቀት! በሌለ ነገር ነው የሚያምኑት! የሌለ ፈለግ እና ፋና ነው የሚከተሉት !

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by Wedi » 10 Jul 2023, 08:11

Selam/ wrote:
10 Jul 2023, 00:41
ይህ ሰው ከዳዊት ድሪም እና ከሆነች ሴት ጋር በመሆነ በጋላ አብይ አህመድ በሚመራው ብልጽግ ና ከፍተኛ በጀት ተበጅቶለት "The New Age movment" የሚባል የኢሊሙኒቲ ሴክት በኢስትዮጵያ እያስፋፋ ነው ያለው!!

እጅግ አሳፍሪ እና አረመኔ የሆነ ስራ ነው እየሰሩት ያለው፡፡

ስለነዚህ ሰዎች ለመረዳት ይህም ማዳመጥ ጥሩ ግንዛቤ ይሰጣል!!

:!:

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by Wedi » 10 Jul 2023, 08:17

:!:
The "Law of Attraction" is capitalism rendered into "spirituality." It is the religion of greed and self-interest.
:!:
Please wait, video is loading...

Selam/
Senior Member
Posts: 17831
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by Selam/ » 10 Jul 2023, 20:06

ትክክል - ዝሙትና ገንዘብ ላይ ያነጣጠረ ማማለያ የኑሮ አቅጣጫ ነው።
Wedi wrote:
10 Jul 2023, 08:17
:!:
The "Law of Attraction" is capitalism rendered into "spirituality." It is the religion of greed and self-interest.
:!:
Please wait, video is loading...

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by sun » 10 Jul 2023, 21:48

Horus wrote:
10 Jul 2023, 01:57
ወዳጄነህ የፖዘቲቭ ሳይኮሎጂ አቀንቃኝ ነው። ለጥቂት አመታት በጣም የገነነ ፋድ ነበር positive psychology. አሁን ኮግኒቲቭ ሳይንስ፣ ኢቮሉሽነሪ ሳይኮሎጂና ኒውሮሳይንስ በጣም ስለመጠቁ ፖዘቲቨ ሳይኮሎጂ ከቢሄቨየር ሳይንስ ወደ ማይለይበት ደረጃ ደርሷል ። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ገና እያወቁት ስለሆነ ብዙ ሆሆታ ይደረግበታል ። የዴካርት I think therefore I am የሚለው የማይንድ የበላይነት ተሽሯል ። ይህን የማያውቁ ሰዎች ናቸው በዚያ ላይ ግዜ የሚያጠፉት ። ዛሬ ያለው ፓራዶግማ mind is embodied! በቃ! አቢይ አህመድ ይህን የምናብ የበላይነት ጠጥቶ ነው ይህና ያንን እየሰበከ የትም ፈቀቅ ማለት ያቃተው ። Reality is fact. ሃሳብ ባዶ ምስል ነው። በስሜት ያበደ ፖዘቲቭ ሃሳብ ሺ ግዜ ብናላምጠው ውስጡ ምንም የለውም ። ይህ ነው ያቢይና አማካሪዎቹ መሰረታዊ ውድቀት! በሌለ ነገር ነው የሚያምኑት! የሌለ ፈለግ እና ፋና ነው የሚከተሉት !
Really wushetam neh! :P

Horus
Senior Member+
Posts: 42727
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by Horus » 10 Jul 2023, 22:23

Abere & Wedi,
This new comers will get nowhere with Prosperity Bible and Positive Psychology. I jut pulled out both volumes from my library.

The Prosperity Bible (a massive collection of think rich and get rich movement that began with Ben Franklin and taken to its heights by Napoleon Hill. This collection of 1272 pages by 19 authors published in 2007. I will post its link.

Hand Book of Positive Psychology (ed.) by Snyder and Lopez -828 pages of complete collection the basic writing of the entire field of this new age ideology published in 2005. Both schools of poplar psychology are not considered worthy of serious scientific import. Those who believe in them follow these preaching just as they would believe in the Scripture. These are ideas taken up by lazy and intellectually weak people; people who are unable to tackle the scientific ideas of cognitive science, behavioral economics, evolutionary psychology or the neurology of human behavior.

In the world of science thinking is a physical activity, ideas are metaphors, images that appear in our mind to represent or signify reality. We call them forms, they are copies of reality. so, all talk about mind over matter, all talk about willing a non existent reality into being is mental illusion, waste of mind if not a mental disorder.

So I wouldn't worry too much about the impact of these light weight worshipers of think rich and grow rich preachers. It is a fad!

https://www.abebooks.com/servlet/BookDe ... 8kQAvD_BwE

https://www.abebooks.com/servlet/BookDe ... YgQAvD_BwE

Horus
Senior Member+
Posts: 42727
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by Horus » 11 Jul 2023, 00:51

ሰውዬው እዚም እዛም ዞሮ ዞሮ ዞሮበታል! የሱ ስራ ሳይቲስት መሆን ነው ። ከዚያ ባለፈ ኮምፓራቲቭ ሪሊጅን እና ፍልስፍናና እና ሳይንሳዊ ፍልስፍና ማደባለቅ የለበትም ። አንድ ሊቅ ፊሎሶፈር የሚባለው እና ፊሎሶፊ ኦፍ ሳይንስ የተባለ መስክ የተፈጠረው እምነትና ሃቅ፣ ፋክትና ቫልዩ ወይም ስነ ምግባር የተለያዩ ስለሆነ ነው። ፊሎሶፊ የአንድን ነገር መስኤ ያጠናል ፣ አንድ ነገር የሚሆነው ለምንድን ነው ? ይህ ነገር ህያው የሆነው በምን ምክንያት ነው ብሎ አመክንዮን ይፈልጋል ። ይህ ሳይንስ ነው ማለትም እውነተኛ እውቀት ነው ። ሳይንስ ማለት እውቀት ማለት ነው።

እምነት እውቀትን አይሻልም። አንድ ሰው በአንድ ኃይል ለማመን ማወቅ የለበትም፣ ማመን ምቀበል ብቻ ነው ያለበት ። ሃኪሙ አሁን ከእውቀት ወደ እምነት እየሄደ ነው ። በዚህም ምክኛት ነው አይምሮአችሁን ባዶ አድርጉ፣ ሃሳብ ከአንጎላችሁ አውጡና ጣሉ፣ ባዶ ሁኑ የሚለው ከእውቀት ወደ እመንት ስለሄደ ነው ። የሰው ልጅ ሃሳብ ካንጎሉም ሆነ ከይምሮው ሊያወጣ አይችልም ። ሰው የሆነው ስላሰበ ነው። ተመልሶ የማያስብ ፣ ህሊና አልባ ድንዳይ፣ ዛፍ ወይም እንሽላሊት ሊሆን አይችልም ፣ አንጎል ስላለው ። ሃሳብ የህይወታችን የህያውነታችን መገለጫ ነው ። ሃሳብ የሌለው ሰው አልዛይመር የመታው፣ ሜሞሪው የጠፋ ሰው ማለት ነው።
90% በውስጣችን ያለው ሃሳብ አንኮንሸስ ስለሆነ እኛ እራሳችን እንኳ ምን እንደ ሆነ አናውቀውም እንኳንስ በትዕዛዝ ፍቀን ልናጠፋው ። ይህ ሃኪም ይህን መሰል ግዙፍ ስህተት የሚሰራው ከህክምና ወደ ኒውሮሳይንስና ኮግ ኒቲቭ ሳይንስ መሄድ ስላልቻለ ነው። 90% of our thoughts are buried below our consciousness. We don't even know that we have them let alone willingly manipulate them .

ስለዚህ ሰውዬው እንዳለ ገልብጦ ሰበከው እንጂ ትንሽ ቢያስብብበት እንዴት አብሰርድ እንደ ሆነ ይገባው ነበር። እምነት፣ ዊዝደም፣ ፍልስፍና ወዘተ ለያይተን ካላየን ጫካው ውስጥ እንጠፋለን ። የሰው ትርጉም ምንድን ነው? ሰው ለምን ይኖራል (ፐርፐዝ) እና ሰው ሲሞት ምን ይሆናል? ነፍስ የት ይሄዳል? እራሱ ነፍስ ምንድን ነው? ለሚባሉት ጥያቄዎችን መልስ ለመስጠት ነው ባለም ያሉ እምነቶችና ፍልስፍናዎች የተፈበረኩት! ሁሉም የሰው ልጅ የፈጠራቸው መልሶች ናቸው።

ዛሬ ሃኪሙ እንደ አዲስ ያን ሊያስተምር ለምን ግዜውን ያባክናል? ስንኖር ኢትዮጵያዊ ሰው ስንሞት ኢትዮጵያ አፈር ነው የምንሆነው!!! ነፍስ ነፋስ ነው! ስንሞት ነፍሳችን ከነፋስት ጋር ይዋሃዳል! በቃ ታሪክ ቢበዛ ባህያ አይጫንም!!!

Selam/
Senior Member
Posts: 17831
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by Selam/ » 11 Jul 2023, 08:24

ወዳጄነህ ዛሬ እንደዳዊት የሚደግመውን የኤካርት ቶሌ eckhart tolle ዘ ኒው ኧርዝ the new earth እና ዘ ፓወር ኦፍ ናው the power of now በመጀመሪያ ሳነብ ልክ እሱ እንደ ሚሰብከው አይነት ስሜት ተሰምቶኛል። ፀሃፊው ግልፅ ባለና እጥር ምጥን ባለ ቋንቋ እያለሳለሰ የሰዎችንና የማኅበረሰብን አስተሳሰብና ባህርይ እየፈተፈተ ችግሩንም መፍትሄውንም ሲመግብህ አቀራረቡን ላለመቀበል ምንም ምክንያት አይኖርህም።

መሰረቱን በእስያ ያደረገው የቶሌ ፍልስፍና የቅዱስ መፅሀፍትንም ጠቅልሎ ስለያዘ የሆሊውድን የተመሳቀለ የዕብደት ኑሮ የሚያክም ፍቱህ መድሃኂት ሆኖ ነበር የተገኘው፣ በተለይም ኦፕራ ዌንፍሬ ካስተዋወቀችው በኋላ ቤስት ሴለር ሆኖ ነበር። መፅሃፉ ከተፃፈ ወደ ሃያ አመት ሊሆነው ነው፣ ሆሊውድ ግን አሁንም በዕፅ፣ በዝሙት፣ በፍቺ፣ በራስን ማጥፋት፣ በስግብግብነት እንደታመሰ ነው። ዊል ስሚዝ የቶሌ ዋና አቀንቃኝ ነው ግን አሁንም ፌዝን እንኳን መቋቋም የማይችል ሱሰኛና ጋጠወጥ bully ነው። ቶሌ እንደሚለውም አዲስ አስተሳሰብ new consciousness በምድር ላይ አልተፈጠረም። እንዲያውም ‘ቃሉ’ እንዲፈፀም ዘንድ ፣ የሰው ልጅ ክፋቱ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው፣ ከድሮ በከፋ መልኩ እየተጣላ፣ እየተከፋፈለና እየተጫረሰ ነው።

በመሰረቱ ከክርስትና አስተምርሆት ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው። ግን የሰው ልጆችና የምድራችን ሁሉ ችግሮች መፍትሄ ያለው በእያንዳንዳችን አእምሮ ውስጥ ብቻ ነው ብሎ ስለሚያስተምርና መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስን ከህክምናውና ከህይወታችን ውስጥ ስለሚቀንሰው በማር የተለወሰ አንታይ ክራይስት anti-Christ ነው። ጌታ ሁሉን ትተህ እኔን ተከተለኝ፣ ካለእኔ ምንም መዳን የለም ሲል፣ ቶሌ አእምሮህን ፍፁም ነፃ አድርገህ ስለአሁኗ ቅጽበት ብቻ አስብ፣ ኩነቶችን እንዳመጣጣቸው ተቀበላቸው ይላል።

ብዙ ፍልስፍናውን አምንበታለሁ እኖርበታለሁም ግን ለእኔ እንደሚመቸኝ
ተርጉሜ በክርስቶስ ስር ደፍቄዋለሁ I.e. like a Bible appendix።
ፍጋ ቢለው ነው እንጂ፣ ያለ ክርስቶስ መዳን የለም!

Selam/
Senior Member
Posts: 17831
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ይኸ ሰውዬ ወጣቱ ቤተ-እምነቱን ትቶ ግልብ ወደሆነው የሆሊውድ “የመንፈሳዊነት” አስተሳሰብ እንዲያመራ ነው እንዴ የሚሰብከው?

Post by Selam/ » 11 Jul 2023, 19:04

ከኤካርት ቶሌ ድንቅ አባባል ውስጥ ኮሌክቲፍ ፔይን (collective pain) የሚለው በጣም ይገርመኛል። በግል የታመመ ስነ-ልቦና (pain body) እናዳለን ሁሉ፣ የኅብረተሰብ ተወራራሽ በሽታም አለ ባይ ነው።

እንደ እርሱ አባባል ከሆነ የትግራይ ልሂቃንና ካድሬዎች ክፋት፣ ሌብነትና የመንከባለል ባህል የተወረሰና ለማከም ዘመናት የሚፈልግ የጋራ በሽታ ነው። በተመሳሳይም የኦሮሞ ካድሬዎች ጭካኔና አናሳ አስተሳሰብ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ስር የሰደደ የመንጋ ደዌ ነው ማለት ነው።

Post Reply