Assegid S. :
ዶ/ር ደሳለኝም ሆኑ ሌላው በህወሃት ላይ በተወሰደው እርምጃ ተሳታፊም ሆነ ደጋፊ የነበረ ኢትዮጵያዊ በወንጀል ተጠያቂ ወይንም ይቅርታ ጠያቂ የሚሆንበት ምንም ዓይነት የህግም ሆነ የሞራል አግባብ የለም።
እንደ እኔ እምነት ትክክለኛ አእምሮ ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ‘ጀግና ጀግና’ ‘ተጎጂና ይቅርታ ተጠያቂ’ የማስመሰል ጨዋታቸውን አቁመው፥ እጅግ በጣም ሳይረፍድ የተሰራውን በደል በመልካም ቃላትና ስሜት ለማለዘብ ቢሞክሩ የተሻለ ይመስለኛል።
አለበለዚያ ግን ህዝብ ግራና ቀኝ ተሰልፎ ኣንዱ በኣንዱ ላይ እየተንጠራራ በምርኮ በተያዙት የኢትዮጵያ ወታደሮች ፊት ላይ የተፋው ምራቅ ቢደርቅም ... ጭርቱ ግን ገና አለቀቀም።
የህወሃት ወታደር ድካምና ረሃብ ያደከመው ወገቧን በ’ከስክስ’ ጫማ ረቅጦ መራመድ እስኪያቅታት ድረስ አጥንቷን የሰበራት ኢትዮጵያዊት ሴት - ለእኔና ለሚሊዮኖች እህት ናት … ለሚሊዮን ኢትዮጵያዊ እናቶች ደግሞ ሴት ልጅ። ስለዚህ ማን ተጠያቂ፣ ማን ይቅርታ ጠያቂ መሆን እንዳለበት ማስተዋል ያስፈልጋል።
ይህ ጊዜ ለህወሃትና ለደጋፊዎቹ 'victim victim' መጫወቻ ሳይሆን እንዳውም Happy Hour ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ ኣመራር ትንሽ ሸርተት ያለ ጊዜ ... ልቡ የቆሰለ፣ ኣንጀቱ ያረረ ወጣት እስከ የት ድረስ ለመሄድ እንደሚችል ለመገመት አይከብድም።
-