አንድ መንግሥት በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ እንደ ሰሜን ዕዝ ያለ የክህደት በፈጸመ ላይ 1ኛ) የሰራዊቱን ሞራል ለመጠበቅ 2ኛ) ሰለባ ለሆኑት ካሳ ይሁን የወንጀል ክሥ መመስረት የለበትም ወይ?
Posted: 07 Jul 2023, 10:19
የአንድ አገር መንግሥት በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ በትግራይ እንደ ሰሜን ዕዝ ያለ የክህደት ጥቃት በፈጸመ ላይ በህግ አግባብ 1ኛ) የሰራዊቱን ሞራል ለመጠበቅ 2ኛ) የግፉ ሰለባ የሆኑትን በማሰብ የካሳ ይሁን የወንጀል ክሥ መመስረት የለበትም ወይ? - ሆረስ
የአንድ ልዑላዊት አገር የመከላከያ ሰራዊት አባል ህይወት ሌጣ የወረቀት ቼክ ተደርጎ እንደት ሊወሰድ ይችላል? በመጀመሪያ በአለም ላይ ታይቶ እና ተሰምቶ በማያውቅ ዘግናኝ መልኩ ክህደት ለተፈጸመበት ሰራዊት ጥቃቱ አንደ አገር ቀጥሎም በሰራዊቱ እና በቤተሰቡ ላይ የደረሰ ግፍ በመሆኑ ማንኛውም ውይይት ይሁን ድርድር ለዚህ ወንጀል ተጠያቂ ማግኘት እና ለጥቃቱ ሰለባዎች ደግሞ የካሳ ክፍያ ሊያስፈልግ አይችልም ወይ? ይህን አይነት ግፍ ከፈጸመ ሀይል ባለበት እንደት የአንድ ልዑላዊ አገር መከላከያ ህግ እና ደንብ ሊያስከብር ይችላል? የዚህ አይነት ክህደት በሚፈጸምበት ህዝብ ዘንድ እንደት ደጀን እና ወገን ሊባል ይችላል? ለመሆኑ የሰሜን ዕዝ ጥቃት የፈጸመው ማን ነው? ወያኔ ነው ወይስ ብልጽግና ኦነግ? ምክንያቱም ለዚህ ለህሌና እና ሞራል ዘግናኝ ግፍ እና ወንጀል ጠያቂ የማይፈልግ ተጠያቂውንም የማይወንጀል ለተጠቃው ሰራዊት የሞራል እና የህግ ካሳ የማይጠይቅ እራሱ ወንጀለኛ ነው። የአብይ አህመድ መንግስት ዝናብ እንደ መታው የጭቃ አክንባሎ የፈራረሰ ስለመሆኑ ይህ ብቻ በቂ ነው። የሰራዊቱን ጠላቶች ሸሪክ ሰራዊቱን ግን ጠላት ያደረገ ቢኖር በታሪክ እና በአለም ይህ ሰው ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ህይወት እና ሞት እንደ ውሻ ተቆጥሯል - ሰራዊቱ በዚህ ሳብያ ከህዝብ ክብር አጥቷል። በየጢሻው እንደ ውሻ ሙቶ ወይም እየተማረከ ነው። ውሃ ሲጠማው እንኳን ውሃ የሚያጠጣው የለም - የእራሱን ደም ያላስመለሰ ደሙን የወያኔ ውሻ ልሶት የቀረ ስለሆነ። እንደ ኢትዮጵያ መከላከያ ከመሆን ያስጠላ ስራ የለም።
The most respected profession is now the least respected profession in Ethiopia. ዛሬ ህዝብ የመከላከያ ሰራዊት ብሎ ሳይሆን የሚጠራው ሸኔ እያለ ነው።