Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Assegid S. » 05 Jul 2023, 15:03

https://www.eaglewingss.com/

የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

ለማንበብም ሆነ ለመስማት ስልችት ያለኝ ነገር ቢኖር “የፕሪቶሪያው ስምምነት” የሚለው ሐረግ ነው። ለትንሹም ለትልቁም - ለወፍራሙም ለቀጭኑም ጉዳይ “የ Pretoria agreement” እያሉ ማላዘን። ምርጫ ቦርድ፦ ‘ህወሃትን ዳግም በፖለቲካ ፓርቲነት አልመዘግብም’ ሲል ... ”የፕሪቶሪያው ስምምነት!”  ብሎ መጮኽ። ትምህርት ሚንስትር፦ ‘ወልቃይትና ራያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔት በኣማራ ክልል አስተዳደር ስር ናቸው’ የሚል  assessement report ሲያወጣ ... ”የፕሪቶሪያው ስምምነት!” ብሎ ኡ! ኡ! ማለት። ይህ ጉዳይ በዚህ ከቀጠለ ... ነገ ... በዚያ መንደር በትዳር ፍቺ ላይም የፕሪቶሪያው ስምምነት ሳይጠቀስ የሚቀር አይመስለኝም።

ህወሃት፦ በኢትዮጵያና በህዝቦቿ ላይ መከራ ሲያዘንብ ሁለት ትውልድ ማምከኑ ሳያንስ ዛሬም እንደ ስለት ልጅ ሸምናችሁ አልብሱኝ፣ ሸምታችሁ አጉርሱኝ ሲል በረባ ባልረባው ያለቅሳል። ለነገሩ ... “የማይገርፉት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል“ አይደል የሚባለው። ይህ የመርገምት ቋት ኣራት ኪሎ ከመግባቱ በፊትና ከገባ ቦኃላ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያኖች ላይ ያወረደውን በላ ወደ ጎን ትተን፤ ከኣራት ኪሎ ከወጣ እና የሰሜኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ቦኃላ ያሉትን ጥቂት ዓመታት ወደኋላ መለስ ብለን ብንመለከት እንኳ፥ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ላይ ያደረሰው አካላዊ፣ ስነለቦናዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደ ቀላል በእርቅ የሚታለፍ አልነበረም። ግን ምን ዋጋ አለው ... ልፍስፍስ መሪ ከእራሱ አልፎ ሀገር ያልፈሰፍሳል።  

ከሁሉ ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ “የሌባ ዓይነ-ደረቅ ..." እንዲሉ ገድለው - ተገዳይ፣ ዘርፈው - ተዘራፊ፣ በድለው - ተበዳይ ሆነው ‘የተለየ ጥቅምና አገልግሎት ይሰጠን!’ እያሉ መጮሃቸው ነው።  

ይህንን ደም አፋሳሽ ጦርነት በቅጥረኝነት ቀስቅሰው የሀገሪቷን ሰዋዊና ቁሳዊ ቅሪት ዶግ አመድ በማድረግ ሀገርና ህዝብን በኣሥርት ዓመታት ወደኋላ በመመለሳቸው ካሳ መክፈል ሲገባቸው፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ዜጋ ነፍስ በከንቱ እንዲጠፋና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሲቪሊያን ከቅዬያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት በመሆናቸው በሕግም ሆነ በታሪክ በወንጀለኛነት መጠየቅ ሲኖርባቸው ... ጭራሽ እነርሱ ተበዳይ፣ እነርሱ ተጎጂ፣ እነርሱ ከሳሽ ሆነው ከሀገር ሀብት ላይ “ከባንኮች የተበደርነው እዳ ይሰረዝ፣ መሽገን የተታኮስንባቸው ቤተክሪስቲያኖች፣ ትምህርት ቤቶችና የኢንዱስትሪ ተቋማት በአስቸኳይ ይጠገኑ፣ ተፈናቃዮች  በቀናት እድሜ ወደ ‘ቅዬያቸው’ ይመልሱ" እያሉ የሰው ጩኸት በመቀማት “የፕሪቶሪያው ስምምነት ተጣሰ!” ሲሉ ላንቃቸውን ይቀዳሉ። ይህ በየትኛውም መመዘኛ ብልግና እንጂ ብልጠት፣ ወያኔነት እንጂ ወኔያምነት አይሆንም።

ህወሃት፦ በብዙ ቢሊዮን ዶላር ሊገመቱ የሚችሉ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሀብት የሆኑ ወታደራዊ መሳሪያዎችንና ተሽከርካሪዎችን በምርኮና በውርስ ድንበር አልፈው እንዲወሰዱ ምክንያት ሆኗል።  ባለፉት ጥቂት ዓመታት፦ በድርድርና በሰበብ አስባቡ መቀሌ እያረፉ በሚነሱት አይሮፕላኖች በርካታ የወርቅና የውጭ ምንዛሪ ሻንጣዎችን በኣደራና በስጦታ ከሀገርና ከህዝብ ሰርቆ አሽሽቷል። እነዚህ ኣይሮፕላኖች መሬት ለቀው ሊበሩ የቻሉት በኣምላክ ሚስጢር እንጂ እንደተጫኑት የሀገርና የህዝብ ንብረት ክብደት ቢሆን ኑሮ ከመቀሌ እስከ ጅቡቲና ናይሮቢ በረው ሳይሆን እንደ ባቡር ምድር ለምድር ተስበው በደረሱ ነበር። የመንግስታቱ ድርጅት አለቃ "ትግራይ እንዳልሄድ ተከለከልኩ” ሲሉ ያኮረፉት፥ መቀሌ ውስጥ ዓይኑን ለማየት የናፈቁት ቤተሰብ ኖሯቸው ሳይሆን ሊጨብጡት ያሰቡት ወርቅና ዶላር አጓጉቷቸው ነው።

ይህ ሁሉ ወንጀልና ክህደት በሀገርና በዜጎች ሀብት ላይ ተፈፅሞ እያለ፥ ህወሃትና ደጋፊዎቹ ጩኸታችንን በመቀማት የሚያለቅሱት ስላማረኩብን ስፍር ቁጥር የሌለው ተተኳሽ፣ ስላስወረሱን surface to air missiles፣ ስላሸሹት ወርቅና የውጭ ምንዛሪ ሳይሆን ስለ ማንኪያና ሹካ፣ ስለ ባዶ የወሃ ጄሪካን ነው።

እውነት ለመናገር፦ በፕሪቶሪያው ስምምነትም ሆነ በፕራዮሪቲ (priority) መርሕ … ህወሃት “ጠያቂ” ሳይሆን “ተጠያቂ” መሆን የሚገባው ሀገርና ህዝብን ያደኸየ ቅጥረኛ አካል ነበር። ግን ምን ያደርጋል፦  “አንቺ ምን አደረግሽ ሰው ነው ያጠፋሽ … ተኚ ተኚ እያሉ ሳያንቀላፋሽ” ነው ያለው ዘፋኙ? በእኔ እምነት የፕሪቶሪያው agreement ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያኖች “ስምምነት” ሳይሆን ዳግም የመከራ ሰንሰለት ነው።

*Original feature image credited for unknown artist

Fed_Up
Senior Member+
Posts: 23850
Joined: 15 Apr 2009, 10:50

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Fed_Up » 05 Jul 2023, 15:40

^^^ only in Ethiopia.

Abere
Senior Member
Posts: 15418
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Abere » 05 Jul 2023, 16:56

Assegid,

ቁም ነገሩን በሚገባ ነው ያስቀመጥከው። ይህ የፕሪቶሪያ ጉዳይ የወያኔ እና የኦነጎ የግል ጉዳይ እንጅ የማንም ጣጣ አይደለም። ወያኔዎች ሲያስነጥሳቸው ይሁን ሲያመልጣቸው "ፕሪቶሪያ!" እያሉ ያላዝናሉ - ለእኛ ደግሞ ምንም ምንም እንደማይመስለን ማን በነገራቸው። ነገሩ በተለያዩ ጥሩ ምሳሌያዊ አነጋገር ገልጸኸዋል። ለመጨመር ያህል "አያት ያሳደገው ሰባራ አህያ አይመልስም" ይባላል። ኡ!ኡ! ጆባይዴናቸው ሞግዚት አድርገው አፋቸው ወደዚያ መክፈታቸው ነው። እኛ ደግሞ ምን ጉዳያችን - ፕሪቶሪያ የእኛ አይደል። ከፈለጉ ሌላ ፕሪቶሪያ የመልስ ግጥምያ ይደረግላቸዋል - የመሀል እና የመስመር ዳኛ በአግባቡ ተመርጦ።

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by sarcasm » 05 Jul 2023, 17:59

Brother Assegid, I enjoyed reading your timely articel. At the risk of boring you more, I want to bring a law professor's view on the agreement. The Pretoria Agreement will continue to be referenced very frequently for the next couple years until Tigrayans determine their destiny in a referendum because it is the only political / legal thread that is holding Tigray and Ethiopia together.

CONSTITUTIONALLY SPEAKING... The Tigray-Ethiopia relation is governed mainly by the Pretoria Agreement
============

By Dr Tsegaye Ararsa, Constitutional Lawyer - former professor of Law at Addis Ababa University

The Tigray-Ethiopia relation is governed mainly by the Pretoria Agreement, and only secondarily by the Constitution.

The constitution, conceived as a framework within which disagreements between the two are to be resolved, is cast as an annex to the agreement.

As far as Tigray is concerned, the constitution has been blatantly violated since 2018, but especially after the 2020 election.

The constitution, implicated as it was in the atrocious crimes of the genocidal war, did not have a meaningful existence as far as Tigray was concerned.

It is this imposed "constitutional void" that made defensive war the only mode of ensuring the survival of Tigray as a nation and the Tegaru as a people.

Their heroic resistance has eventually yielded the Pretoria peace deal. That is why, Pretoria, as much as it marks the end of armed hostilities, also marks a new legal beginning for the Ethio-Tigray relation.

Yes, the Pretoria Peace deal (if one can call it that), is the new constitution between Tigray and Ethiopia. As inadequate as it is as a constitutional document, it is the only binding thread that exists between them (other than the now muzzled/neutralized military flex). This has to sink in to the mind of the leaders, especially of Tigray (because the other side has nothing one can call a leader, much less one with a sane mind).

Abiy's flaunting of the terms of the Pretoria agreement is an ominous sign of irresponsibility as these terms are the only thread that bind Tigray to Ethiopia. Ignore them, and Tigray is gone.
Pretoria, you see, is intended not only to stop and avert conflict but also to serves as a bridge between the two. At least until Tigray negotiates a new term of (re)entering the constitutional union, possibility via a new comprehensive referendum.

But in order to get there, Abiy (or whoever rules Ethiopia) must honor the terms of the Pretoria agreement--and for several reasons. For Peace. For humanitarian purposes. For purposes of preserving the union. For keeping Tigray in the union (albeit tentatively).

The issue of compliance therefore is a serious issue. A crucially decisive one at that.
Adhere to the terms, you will give chance to peace, humanity, and unity. Ignore them, and you will lose all. The stakes are that high.

That is also precisely why the guarantors must exert a maximum effort to enforce the agreement.
#Comply_or_perish!

"Shared rule አክትሟል" ዶ/ር ፀጋዬ አራርሳ | በኢትዮጵያ ያልተወከለ ሕዝብ . . .

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Assegid S. » 07 Jul 2023, 09:02

Fed_Up wrote:
05 Jul 2023, 15:40
^^^ only in Ethiopia.
Do you think so? :|

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Assegid S. » 07 Jul 2023, 09:09

Abere wrote:
05 Jul 2023, 16:56
Assegid,

ቁም ነገሩን በሚገባ ነው ያስቀመጥከው። ይህ የፕሪቶሪያ ጉዳይ የወያኔ እና የኦነጎ የግል ጉዳይ እንጅ የማንም ጣጣ አይደለም። ወያኔዎች ሲያስነጥሳቸው ይሁን ሲያመልጣቸው "ፕሪቶሪያ!" እያሉ ያላዝናሉ - ለእኛ ደግሞ ምንም ምንም እንደማይመስለን ማን በነገራቸው። ነገሩ በተለያዩ ጥሩ ምሳሌያዊ አነጋገር ገልጸኸዋል። ለመጨመር ያህል "አያት ያሳደገው ሰባራ አህያ አይመልስም" ይባላል። ኡ!ኡ! ጆባይዴናቸው ሞግዚት አድርገው አፋቸው ወደዚያ መክፈታቸው ነው። እኛ ደግሞ ምን ጉዳያችን - ፕሪቶሪያ የእኛ አይደል። ከፈለጉ ሌላ ፕሪቶሪያ የመልስ ግጥምያ ይደረግላቸዋል - የመሀል እና የመስመር ዳኛ በአግባቡ ተመርጦ።
ሰላም ወንድም አበረ

ለሰጠኸኝ አስተያየት በጣም አመሰግናለሁ 8) በዛ ያሉ የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎችን አውቃለሁ ብዬ አስብ ነበር፤ ነገር ግን አንተ በተደጋጋሚ የምትናገራቸውን (የመትፅፋቸውን) ምሳሌዎች ስመለከት (ሳነብ) … ፍፁም ሰምቻቸው የማላውቃቸው ናቸው። እናም ... የአማርኛ ምሳሌ እውቀቴን ቁጥር ከብዙ ወደ ጥቂት ማውረድ ግድ ይለኛል። በዚህም ይሁን በሌላ thread ላይ ላካፈልከን ኣዳዲስ አስተማሪ ምሳሌዎችህ በድጋሚ አመሰግናለሁ!

መልካም ሰንበት ይሁንልህ - ወንድም አበረ

Abere
Senior Member
Posts: 15418
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Abere » 07 Jul 2023, 09:19

sarcasm wrote:
05 Jul 2023, 17:59

Post by Assegid S. » 07 Jul 2023, 09:21

sarcasm wrote:
05 Jul 2023, 17:59
Brother Assegid, I enjoyed reading your timely articel. At the risk of boring you more, I want to bring a law professor's view on the agreement. The Pretoria Agreement will continue to be referenced very frequently for the next couple years until Tigrayans determine their destiny in a referendum because it is the only political / legal thread that is holding Tigray and Ethiopia together.
Hello Brother Sarcasm

thanks a lot for the comment 8) Honestly, in my eyes and judgment, your comment bears greater polemical value to convince me to live with my boredom than the article written by "the law professor." ወንድም ሳርካዝም፦ መቼም የተማረ ሁሉ ኣዋቂ ነው የሚል አመለካከት እንደሌለህ አምናለሁ። ለእኔ ... ኣንዳንዶች በትምህርት ቤት ቆይታ ከያዙት የዶክተርና የፕሮፌሰር መዓረግ ይልቅ ኣንድ የእንደርታ ትግራዋይ ኣዛውንት ወይንም ደግሞ የወልቃይት ኣማራ ኣባወራ በእድሜ ቆይታ ያገኙት ኣይተ ወይንም አቶ የሚለው የስም ማዕረግ የበለጠ ክብርና ጥበብ አለው። እናም ... ተግባብተናል ብዬ አምናለሁ 8)

መልካም ሰንበት ይሁንልህ ወንድም ሳርካዝም

Abere
Senior Member
Posts: 15418
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Abere » 07 Jul 2023, 09:23

አጫውችኝ እንጅ በአማርኛ የምን ትግርኛ!!

Meleket
Member+
Posts: 5069
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Meleket » 07 Jul 2023, 10:20

Assegid S. wrote:
07 Jul 2023, 09:09
Abere wrote:
05 Jul 2023, 16:56
Assegid,

ቁም ነገሩን በሚገባ ነው ያስቀመጥከው። ይህ የፕሪቶሪያ ጉዳይ የወያኔ እና የኦነጎ የግል ጉዳይ እንጅ የማንም ጣጣ አይደለም። ወያኔዎች ሲያስነጥሳቸው ይሁን ሲያመልጣቸው "ፕሪቶሪያ!" እያሉ ያላዝናሉ - ለእኛ ደግሞ ምንም ምንም እንደማይመስለን ማን በነገራቸው። ነገሩ በተለያዩ ጥሩ ምሳሌያዊ አነጋገር ገልጸኸዋል። ለመጨመር ያህል "አያት ያሳደገው ሰባራ አህያ አይመልስም" ይባላል። ኡ!ኡ! ጆባይዴናቸው ሞግዚት አድርገው አፋቸው ወደዚያ መክፈታቸው ነው። እኛ ደግሞ ምን ጉዳያችን - ፕሪቶሪያ የእኛ አይደል። ከፈለጉ ሌላ ፕሪቶሪያ የመልስ ግጥምያ ይደረግላቸዋል - የመሀል እና የመስመር ዳኛ በአግባቡ ተመርጦ።
ሰላም ወንድም አበረ

ለሰጠኸኝ አስተያየት በጣም አመሰግናለሁ 8) በዛ ያሉ የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎችን አውቃለሁ ብዬ አስብ ነበር፤ ነገር ግን አንተ በተደጋጋሚ የምትናገራቸውን (የመትፅፋቸውን) ምሳሌዎች ስመለከት (ሳነብ) … ፍፁም ሰምቻቸው የማላውቃቸው ናቸው። እናም ... የአማርኛ ምሳሌ እውቀቴን ቁጥር ከብዙ ወደ ጥቂት ማውረድ ግድ ይለኛል። በዚህም ይሁን በሌላ thread ላይ ላካፈልከን ኣዳዲስ አስተማሪ ምሳሌዎችህ በድጋሚ አመሰግናለሁ!

መልካም ሰንበት ይሁንልህ - ወንድም አበረ

ከወንድም Assegid ምልከታ ጋር በሰፊው እንስማማለን። ወንድም ኣበረ ብዙ ተረቶችን እያስተማርከን ነውና ሞቅ ያለው ምስጋናችን ይድረስህ። ሁለታችሁም በጨዋ መልክ ለምታቀርቡት ትምህርታዊ ይዘት ላለው ምልከታችሁ አድናቆትና ክብር ይገባችኋል እንላለን፡ ከኛ ከኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች

እንደኛ እንደ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እይታ፡ ወንድማችን Abere እዚህ ላይ የዶልከው ተረት፡ ሚዛናዊነት አለው ለማለት አንደፍርም። ምክንያቱም ተረቱ ሁሉንም ‘አያቶች’ ባንድ ቁና ውስጥ የከተተ በመሆኑ። አንዳንዱ ‘ኣያት’ የልጅ ልጁን ማባበልና ማቆላመጥ እንጂ መቆጣትና መቆንጠጥ የማይመርጥ አለ፤ ኣንዳንዱ ደግሞ ደህና ኣድርጐ ቀጥቶ ቆፍጣና ኣድርጐ ለቁምነገር የሚያደርስ ኣለ። ሰባራ ኣህያ መመለስ ብቻ ሳይሆን፡ ሃገር መመለስ እንደሚችል አድርገው የሚያሳድጉ አያቶችም ነበሩ ኣሉም። ሁነኛ ኣብነት ያገራችን ብረዚደት የሴት ኣያት (እሚታ) ናቸው “ወ/ሮ መድህን በራድ” በመባል ዬሚታወቁት ያቶ ኢሳያስ ኣያት፡ 'ልጅ ኢሳይያስን በማሳደግ ረገድ ያንበሳው ድርሻ እንደነበራቸው ይነገራል'። ታዲያ ታጋይ ኢሳያስ ከትግል አጋሮቻቸው ጋር በመሆን “በሃይል የተደፈጠጠ የኤርትራን ልኡላዊነት ለመመለስ ከቻሉ አያት-አደጎች አንዱ ናቸው ለማለት ነው። :mrgreen:

በተረፈ ስለ አስተማሪው ጽሑፋችሁ ከልብ ምስጋናችን ለሁላችሁ ይድረሳችሁ ብለናል፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Abere
Senior Member
Posts: 15418
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Abere » 07 Jul 2023, 12:14

ወንድም አሰግድ፥

እንድሁ በገሃድ የምናያቸው ጣርያ የዘለቁ ውሸት፤ ተንኮል እና የግፍ ዶፍ ህሌናችን እራሱ ከጓዳ አፈላልጎ ምሳሌያዊ አነጋገር ያጎናጽፋቸዋል እንጅ በእውነት የመጠቀ ደረጃውን የጠበቀ እና አገረ-ሰብ ወግ የተላበሰ አገላለጽ ማን እንደ አንተ!

ወንድም መለከት:-

በቅድሚያ አመሰግናለሁ። እንደዚህ አይነቶቹ መድረኮች እርስ በእርስ መማሪያ ቢሆኑ እንደት ጥሩ ነበር። ግን ብዙ ይህን ኢንተርኔት ህዝብ ስለተለማመደው እንቶ ፋንቶ እና ክብረ-ነክ ስድብ መወራወሪያ ሁኗል። በምሳሌያዊ አነጋገር ይህን መሰሉ ምግባር ሲያስረዱ በጠላ (ወይን) ይገልጹታል። ጠላ ለጨዋ መጫዎችቻ፤ ለባለጌ መመቻቻ። ለምሳሌ መሸታ ቤት ጠላ ከጠጡ በሗላ፤ ጋጠወጦች ዱላ ይማዘዛሉ። ግን እንደ ወንድማማቾች ማህበር ቤት ግን ቁም ነገር ይጫወቱበታል፤ ስብሃተ ውዳሴ ለአምላካቸው ጽሎትም ለማህበራቸው ፥ለአገራቸው እና ቃያቸው ያደርጉበታል።

ወደ አነሳኸው ቁም ነገር ልመለስ። አንድ ህዝብን ያማከለ (population based) አባባል ቅቡልነት ለመመዘን በአብላጫው እና ማዕከላዊ ( average or normal distribution curve) የሆነውን መያዝ ነው። ማንም በህጻንነቱ ወደ አያቶቹ ቤት ሲላክ ደስ የማይለው የለም - ቢውል ቢያድር ደስታው ወሰን የለውም። ለምን? የአያት ልጅ ቅምጥል ነው። ይህ ማለት ሁሉም እንድህ ነው ማለት አይደለም። There could be grand parents that could fall on either side of the extremities, skewed to the most spoiled or otherwise.

ሌላው ሁሉ ባህርይ ደግሞ ከአያት አይወረስም፤ ከመልካም ወይም ከክፉ ባልጀራ ሊወረስም ይችላል። ባልንጀራህን ንገረኝ እና ስለአነተ ማንነት እነግርሃልሁ ይባላል።

Meleket wrote:
07 Jul 2023, 10:20
Assegid S. wrote:
07 Jul 2023, 09:09
Abere wrote:
05 Jul 2023, 16:56
Assegid,

ቁም ነገሩን በሚገባ ነው ያስቀመጥከው። ይህ የፕሪቶሪያ ጉዳይ የወያኔ እና የኦነጎ የግል ጉዳይ እንጅ የማንም ጣጣ አይደለም። ወያኔዎች ሲያስነጥሳቸው ይሁን ሲያመልጣቸው "ፕሪቶሪያ!" እያሉ ያላዝናሉ - ለእኛ ደግሞ ምንም ምንም እንደማይመስለን ማን በነገራቸው። ነገሩ በተለያዩ ጥሩ ምሳሌያዊ አነጋገር ገልጸኸዋል። ለመጨመር ያህል "አያት ያሳደገው ሰባራ አህያ አይመልስም" ይባላል። ኡ!ኡ! ጆባይዴናቸው ሞግዚት አድርገው አፋቸው ወደዚያ መክፈታቸው ነው። እኛ ደግሞ ምን ጉዳያችን - ፕሪቶሪያ የእኛ አይደል። ከፈለጉ ሌላ ፕሪቶሪያ የመልስ ግጥምያ ይደረግላቸዋል - የመሀል እና የመስመር ዳኛ በአግባቡ ተመርጦ።
ሰላም ወንድም አበረ

ለሰጠኸኝ አስተያየት በጣም አመሰግናለሁ 8) በዛ ያሉ የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎችን አውቃለሁ ብዬ አስብ ነበር፤ ነገር ግን አንተ በተደጋጋሚ የምትናገራቸውን (የመትፅፋቸውን) ምሳሌዎች ስመለከት (ሳነብ) … ፍፁም ሰምቻቸው የማላውቃቸው ናቸው። እናም ... የአማርኛ ምሳሌ እውቀቴን ቁጥር ከብዙ ወደ ጥቂት ማውረድ ግድ ይለኛል። በዚህም ይሁን በሌላ thread ላይ ላካፈልከን ኣዳዲስ አስተማሪ ምሳሌዎችህ በድጋሚ አመሰግናለሁ!

መልካም ሰንበት ይሁንልህ - ወንድም አበረ

ከወንድም Assegid ምልከታ ጋር በሰፊው እንስማማለን። ወንድም ኣበረ ብዙ ተረቶችን እያስተማርከን ነውና ሞቅ ያለው ምስጋናችን ይድረስህ። ሁለታችሁም በጨዋ መልክ ለምታቀርቡት ትምህርታዊ ይዘት ላለው ምልከታችሁ አድናቆትና ክብር ይገባችኋል እንላለን፡ ከኛ ከኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች

እንደኛ እንደ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እይታ፡ ወንድማችን Abere እዚህ ላይ የዶልከው ተረት፡ ሚዛናዊነት አለው ለማለት አንደፍርም። ምክንያቱም ተረቱ ሁሉንም ‘አያቶች’ ባንድ ቁና ውስጥ የከተተ በመሆኑ። አንዳንዱ ‘ኣያት’ የልጅ ልጁን ማባበልና ማቆላመጥ እንጂ መቆጣትና መቆንጠጥ የማይመርጥ አለ፤ ኣንዳንዱ ደግሞ ደህና ኣድርጐ ቀጥቶ ቆፍጣና ኣድርጐ ለቁምነገር የሚያደርስ ኣለ። ሰባራ ኣህያ መመለስ ብቻ ሳይሆን፡ ሃገር መመለስ እንደሚችል አድርገው የሚያሳድጉ አያቶችም ነበሩ ኣሉም። ሁነኛ ኣብነት ያገራችን ብረዚደት የሴት ኣያት (እሚታ) ናቸው “ወ/ሮ መድህን በራድ” በመባል ዬሚታወቁት ያቶ ኢሳያስ ኣያት፡ 'ልጅ ኢሳይያስን በማሳደግ ረገድ ያንበሳው ድርሻ እንደነበራቸው ይነገራል'። ታዲያ ታጋይ ኢሳያስ ከትግል አጋሮቻቸው ጋር በመሆን “በሃይል የተደፈጠጠ የኤርትራን ልኡላዊነት ለመመለስ ከቻሉ አያት-አደጎች አንዱ ናቸው ለማለት ነው። :mrgreen:

በተረፈ ስለ አስተማሪው ጽሑፋችሁ ከልብ ምስጋናችን ለሁላችሁ ይድረሳችሁ ብለናል፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Assegid S. » 08 Jul 2023, 09:54

Meleket wrote:
07 Jul 2023, 10:20

ከወንድም Assegid ምልከታ ጋር በሰፊው እንስማማለን። ወንድም ኣበረ ብዙ ተረቶችን እያስተማርከን ነውና ሞቅ ያለው ምስጋናችን ይድረስህ። ሁለታችሁም በጨዋ መልክ ለምታቀርቡት ትምህርታዊ ይዘት ላለው ምልከታችሁ አድናቆትና ክብር ይገባችኋል እንላለን፡ ከኛ ከኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች

ወንድም መለከት, good to see you (read from you) 8) ለመልካም አስተያየትህ ደግሞ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ

መልካም ሰንበት ይሁንልህ, Brother Meleket

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by Assegid S. » 08 Jul 2023, 09:59

Abere wrote:
07 Jul 2023, 12:14

ወንድም አሰግድ፥

እንድሁ በገሃድ የምናያቸው ጣርያ የዘለቁ ውሸት፤ ተንኮል እና የግፍ ዶፍ ህሌናችን እራሱ ከጓዳ አፈላልጎ ምሳሌያዊ አነጋገር ያጎናጽፋቸዋል እንጅ በእውነት የመጠቀ ደረጃውን የጠበቀ እና አገረ-ሰብ ወግ የተላበሰ አገላለጽ ማን እንደ አንተ!
ወንድም አበረ, ለአበረታች አስተያየትህ ምስጋናዬ እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው። መልካም ሰንበት እንዲሆንልህ ከልቤ እመኛለሁ, Brother Abere 8)

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የፕሪቶሪያው ሰንሰለት

Post by sarcasm » 10 Jul 2023, 08:13

Abere wrote:
07 Jul 2023, 09:23
አጫውችኝ እንጅ በአማርኛ የምን ትግርኛ!!

የድምፃዊ አበበ ካሴን መርህ የለሽነት - ሟችንም ገዳይንም እንዴት እኩል ማሞገስ ይቻላል?

ድምጻዊው ግን አድርጎታል።ከሰሞኑ ተወዳጅ ከሆኑ የባህል ሙዚቃዎች አንዱ ተብሎ የድምፃዊ አበበ ካሴን እናት አለም ዳንሻ የተባለ ዜማ አንድ ወዳጄ ልኮልኝ አየሁት።የግጥም ድርሰቱ የራሱ በሆነዉ በዚህ ስራ ውስጥ የወልቃይት አካባቢን ባህል፣ዉበት ጀግንነት እና የትግል ታሪክ ይዘረዝራል።

በጣም በሚገርም ሁኔታ ድምፃዊ አበበ ካሴ በዚህ አዲስ ስራው ዉበቱን ባህሉን ጀግንነቱን እና ታሪኩን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ተግቶ የታገለዉንና እየታገለ ያለዉን ጨካኙን የህወሓት ቡድን እያሞገሰ ያዜመ ቀደምት ድምፃዊ ነዉ።

ሰዉ እንዴት በዚህ መጠን ሟችንም ገዳይንም እኩል ማወደስ ይችላል?ጓድ ፕሬዝዳንት እንዲህ አይነት ትግል ነዉ የገጠመን ነበር ያሉት?

ሁለቱም ሙዚቃዎች ተያይዘዋል
Please wait, video is loading...

Unprincipledness

Post Reply