Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

"የእኛ ሰው በባህር ዳር"

Post by Wedi » 04 Jul 2023, 06:40

"የእኛ ሰው በባህር ዳር"

እነ ሽመልስ አብዲሳ "የእኛ ሰው በባህር ዳር" ብለው የሚጠሩት እና የሚተማመኑበት ሰማ ጥሩነህ!

ሰማ ጥሩነህ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መንግስት መዋቅር የተመለመለው ከ1997 ዓ.ም በፊት ነበር ይላሉ ምንጮች። በወቅቱ አዲስ አበባ ላይ የግርግሩ ትክክለኛ ምክንያት ባይታወስም ግርግር የነበረነት ወቅት ነበር።
ሰማ ጥሩነህ ያኔ ነው የተመለመለው። ምልመላውም የተከናወነው በአቶ በረከት ሰምዖን ነበር። ሰውየው የመንግስት መዋቅር ውስጥ ከመግባቱ በፊት በአዲስ አበባ ወዛደር/ጫኝ አውራጅ/ ነበር የሚሰራው። (ለስራው ትልቅ ክብር ያለኝ መሆኑ ይሰመርበት) ይለናል ምንጫችን።

በወቅቱ የተነሳውን ግር ግር ለማብረድና ወጣቶችን ለማሳሰር በወቅቱ በበረከት ሰምዖን አይን የገባው ሰማ ጥሩነህ ነበር። ሰማ በበረከት ሰምዖን ሲመለመል በስርዓት መጻፍም ሆነ ማንበብ አይችልም ነበር ብሎኛል የቅርብ ጓደኛው።

ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ ስልጠና ተስጥቶት ማንበብና መጻፍ ሲጀምር የስለላ ስልጠና/ደህንነት/ እየተከታተለ እዛው አዲስ አበባ ከቆየ በኋላ ወደ ሶማሌ ተልኮ እዛው ሶማሌ ሲሰራ ቆይቶ በኋላ ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲላክ ተደረገ።

ቤንሻንጉል እያለም እያንዳንዷ ግጭትና ጸረ አማራ ዘመቻ ይካሄድ የነበረው በዚሁ ሰውዬ አስተባባሪነት ነበረ ከዛም ከመተከል አምጥተው አዊ ዞን ተመድቦ እየሰራ በአማራና አገው መካከል ግጭት ፈጥሮ እንጅባራን የደም ማዕበል እንዲበላት በተለያየ ጊዜ ሞክሮ ሲከሽፍበት ከርሟል።

ይህን ማድረግ ባለመቻሉ በአለቃዎቹ ቂም የተያዘበት ሰማ ከአዊ ዞን ተነስቶ ወደ አሶሳ ተላከ ከዛ በኋላ በመተከልና ሌሎች አካባቢዎች ጸረ አማራ አስተምሮዎችን በሚገባ ፈጽሟል። የመተከል እልቂት የሰማ ጥሩነህ ስራ ውጤት ነውም ብለዋል።

ከዛ በኋላ ገዱ ለትህነግ ጀርባውን መስጠት ሲጀምር የአገው ሸንጎን እንዲያደራጅና ገዱን እንዲሰልል ወደ አማራ ክልል መለሱት። በሚገባ ስራውን ሲሰራላቸው ቆይቶ ለአገው ሸንጎ ጥንካሬ ሲባል ወደ አዊ ዞን እንዲመጣ ተደረገ።

ለትህነግ ያለው ፍቅር የትየለሌ ነው ያለው ምንጫችን አሁንም ቢሆን የአገው ሸንጎ ዋና አንቀሳቃሽና የኦህዴድ በተለይም የትህነግ ሰላይ በመሆን እያገለገለ የሚገኝ ባንዳ ነው። ታስታውሱ እንደሆነ አለን ምንጫችን "የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ እያለ እያንዳንዱን የጦርነት ዝግጅት በመግለጫ መልክ ነበረ ሚዲያ ላይ እንዲወጣ የሚያደርገው"

ሰውየው ቀጥታ የሚገናኘው ከእነ አብይ/ ሽመልስ/ ብርሃኑ ጁላ አሁን ደግሞ ከእነ ደብረፂዮን ጋር ነው የሚሉት ምንጮች በአማራ ክልል የተከፈተውን ጦርነት በበላይነት እያስተባበረ እና መረጃ እየሰጠ ያለው እሱ ነውም ብለዋል። ያው የእነ ይልቃል ከፋለ የድውይ ስብስቦች የሚሰሩት አድርባይነት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።

በመከላከያም ይሁን በክልሉ ፀጥታ መዋቅር እንዲሁም ከአመራሩ ለህዝብ ውግንና ያላቸውን መረጃ በመሰብሰብ እንዲመቱ ወይም እንዲሸማቀቁ አለያም እንዲባረሩ እና ከቦታው እንዲቀየሩ ይሰራል።

በስብሰባም ላይ እና ለአንዳንዶቹም ስልክ እየደወለ " ውሎ አዳራችሁ፤ ውይይታችሁ ከፋኖ ጋር ነው፤ እንወያይ እያላችሁ ፋኖን ልቡን ታሳብጣላችሁ" እያለ ለማሸማቀቅ ሙከራ ሁሉ አድርጓል።

ሌላው የዚህ ሰውዬ አደገኛነት አማራውን እረፍት ለመንሳት እና አጀንዳውን ለማሳት ጎንደር አካባቢ በደረቅ ወንጀል የሚፈለጉትን የቅማንት ታጣቂ እያደራጀ እና በውይይት፤ በእርቅ የተዘጋን ፋይል ለመቀስቀስ ጥረት እያደረገ መሆኑ ነው።

ለዚህ ደግሞ በከተማችን በወንጀል የሚጠረጠሩ አንዳንድ አመራሮችን: በህዝብ የተነጠሉ እና የማይፈለጉ አመራሮችን: በዘመድ አዝማድ ተደራጅተው ከህዝቡ ላይ ተጣብቀው ጎንደርን ከሚግጧት ጋር ተናበው ነው እየሰሩ ያሉት።

ለአብነት ያህል ወደፊት በዝርዝር እመጣለሁ (ብሏል ምንጫችን) ለአሁኑ የአዘዞ እና አካባቢው ፖሊስ አዛዥን ኮማንደር ብርሃኑን መጥቀስ እችላለሁ። ከዚህ ሰውዬ ጋር በመገናኘት ጎንደር ውስጥ ደም አፋሳሽ ነገር ለመፍጠር ሰሞኑን ሞክሮ ከሽፏል። ይህንንም እመጣበታለሁ። ሌላው ሰማ ጥሩነህ በቋራ መተማ ሱዳን አዋሳኝ ያለውን የሰዎች እገታና ዘረፋ ታጣቂዎችን አደራጅቶ የሚመራው ፤ ከመተከል አማራ እንዲፀዳ እየሰራ ያለው እሱ ነው።

"ክልል ብሎ ለማዋለድ ከጎንደር ቋራ ጀምሮ ቤኒሻንጉልን በከፊል እነ ሽመልስ አብዲሳ የቀረውን በመያዝ ተጎራባች ክልል ለመሆን ያቀደ ነው። ያው ቅዠት ቢሆንም ቅሉ!

በምስሉ ላይ ከሰማ ጋር አብሮ የሚታየው ኮማንደር ብርሃኑ ይባላል በጎንደር የአዘዞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ሲሆን ከሰማ ጥሩነህ ጋር በጎንደር ደባ እየፈጸመ ያለ ባንዳ ነው በማለት መረጃውን ከምስሎቹ ጋር አያይዞ አድርሶናል ምንጫችን

:!:
Please wait, video is loading...