Welayeta’s demand to be a killil and Election board
Posted: 25 Jun 2023, 01:39
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የወላይታን ህዝበ ውሳኔ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ አደረገ
Play Video3:26 min
24.06.2023
የወላይታ ህዝበ ውሳኔ ግዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ ሆነ
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ሰኞ የተካሄደውን የወላይታ የድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ የጊዜያዊ ውጤት ዛሬ ይፋ አደረገ ፡፡ ቦርዱ በጊዜያዊ የድምፅ ቆጠራ ውጤት ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን በመደገፍ የተሰጠው ድምፅ አብላጫ ቁጥር ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን ለውጤቱ ዕውቅና አይሰጡም
የዎላይታ ህዝበ ውሳኔ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ሆነ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ሰኞ የተካሄደውን የወላይታ የድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ የጊዜያዊ ውጤት ዛሬ ይፋ አደረገ ፡፡ ቦርዱ በጊዜያዊ የድምፅ ቆጠራ ውጤት ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን በመደገፍ የተሰጠው ድምፅ አብላጫ ቁጥር ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ ቦርዱ ህዝበ ውሳኔውን ያካሄደው ሁለት ዋነኛ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሂደቱም ሆነ ለውጤቱ ዕውቅና እንደማይሠጡ እየገለፁ ባሉበት ወቅት ነው ፡፡
የዎላይታ ህዝብ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች በጋራ ያዋቅሩታል የተባለው ክልል አካል ለመሆን ወይም ላለመሆን ያስችላል የተባለው የድጋሚ ህዝበ ውሳኔ ባለፈው ሰኞ ነበር የተካሄደው ፡፡ በህዝበ ውሳኔው የዞኖች እና የልዩ ወረዳዎቹን በጋራ መደራጀት “ አደግፋለሁ “ የሚለው በእርግብ ፤ “ አልደግፍም “ የሚለው ደግሞ በጎጆ ምልክት በተወከሉበት በዚሁ ህዝበ ውሳኔ ከ849 ሺህ በላይ መራጮች ድምፃቸውን ሰጥተውበታል ፡፡የዎላይታ ሕዝበ ዉሳኔ ቅድመ ዉጤትና የምርጫ ቦርድ ግምገማ
ሂደቱን እያስፈጸመ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ይፋ ባደረገው ጊዚያዊ ውጤት በጋራ ክልል መደራጀትን የሚደግፈው ድምፅ አብላጫ ቁጥር ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ ቦርዱ እንዳለው በቆጠራው ውጤት መሠረት 760 ሺህ ያህል ድምፅ ሰጪዎች የጋራ አደራጃጀቱን ደግፈው ድምፅ ሰጥተዋል። ቀሪዎቹ 42 ሺህ ድምፅ ሰጪዎች ደግሞ ሳይደግፉ መቅረታቸውን ነው ቦርዱ በመግለጫው የጠቀሰው፡፡
የዎላይታ ህዝበ ውሳኔ የተካሄደው የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ እና የዎላይታ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር የተባሉ ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ለህዝበ ውሳኔው እውቅና እንዳማይሰጡ እየገለፁ ባሉበት ወቅት ነው፡፡ ዶቼ ቬለ DW ቦርዱ ዛሬ ይፋ ባደረገው ጊዚያዊ የድምፅ ቆጠራን ውጤት የዎላይታ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር ዕውቅና የነፈገበትን ምክንያት የግንባሩን ሊቀ መንበር አቶ ጎበዜ ጎአን ጠይቋል ፡፡ የዎላይታ ህዝብ ለአራት ዓመታት ሲጠየቅ የነበረው የክልል አደረጃጀት ጥያቄ በህዝበ ውሳኔው ውስጥ በአማራጭነት መካተት ሲገባው አልተካተተም የሚሉት አቶ ጉበዜ “ ይልቁንም የህዝቡ ጥያቄ በገዢው ፓርቲ ውሳኔ እንዲቀለበስ ነው የተደረገው ፡፡ በመሆኑም ቦርዱ ጊዜያዊ ውጤት በሚል የገለጸውን ፓርቲያችን አይቀበለውም ፤ ዕውቅናም አይሰጥም “ ብለዋል፡፡የወላይታ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ቅሬታ
የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ የሆኑት እና የደቡብ ክልልን በመወከል የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን ያገለገሉት አቶ ዳያሞ ዳሌ የህዝበ ውሳኔው ውጤት በአመዛኙ የጋራ አደረጃጀት አማራጭን ይሁንታ ሊያገኝ እንደሚችል የሚጠበቅ ነበር ብለዋል፡፡ ምርጫው ነባሩ እና አዲሱ ክልል በሚል የቀረበ ነው ያሉት አቶ ዳያሞ “ ከእውነታ አንጻር ነባሩ ክልል እንደማይቀጥል የታወቀ ነው ፡፡ ለምርጫው የወጣው ህዝብ ያንኑ አማራጭ ሊጠቀም እንደሚችል ይገመት ነበር ፡፡ ምክንያቱም ወላይታ ህዝበ ውሳኔ በሰጠበት ክልል እና በማዕከላዊ ክልል ኮሚቴ ተቋቁሞ ከወዲሁ ረቂቅ ህገ መንግሥት እየተዘጋጀ ያለበት ሁኔታ አለ ፡፡ ይህ ማለት ነባሩ እንደማይቀጥል ግልፅ ነበር “ ብለዋል ፡፡
Äthiopien Wolaita Opposition
በህዝበ ውሳኔው መሠረት የጋራ ክልል ይመሠርታሉ ተብለው የሚጠበቁት የዎላይታ ፣ የጋሞ ፣ የጎፋ ፤ የኮንሶ ፣ የደቡብ ኦሞ ፣ የጌዲኦ ዞኖችና አንዲሁም የአማሮ ፣ ቡርጂ ፣ ደራሼ ፣ አሌ እና ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች ናቸው ፡፡ዛሬ ይፋ የተደረገው የቦርዱ ጊዚያዊ ውጤት ከጸና ስድስቱ ዞኖች እና አምስቱ ልዩ