Page 1 of 1

ክልል ከክልል ያለው ግንኙነት በትብብር እና ህግን መሠረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡- ሰላም ሚኒስቴር

Posted: 18 Jun 2023, 09:52
by sarcasm
ክልል ከክልል ያለው ግንኙነት በትብብር እና ህግን መሠረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡- ሰላም ሚኒስቴር
***************************************

ክልል ከክልል ያለው ግንኙነት በትብብር እና ህግን መሠረት ያደረገ መሆን እንዳለበት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን ተናገሩ።
የሰላም ሚኒስቴር ከድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመተባበር የምሥራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች እና ከተማ አስተዳር የጋራ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ እና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብደላ በከር፣ ሰላማችንን ሁሌም ልንከባከበው ይገባል፤ ስለ ሰላም የምንሰራው ግጭት እና ብጥብጥ ውስጥ ከገባን በኋላ መሆን የለበትም ብለዋል።
ሁለንተናዊ እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የአጎራባች ክልሎች የእርስ በእርስ ግንኙነት እና መናበብ በእጅጉ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይ በፌዴራሊዝም፣ በመንግሥታት ግንኙነት ጽንስ ሀሳብ እና የመንግሥታት ግንኙነት ሥርዓት የተመለከቱ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን፣ ከመንግስታት ግንኙነት አዋጁ አንዱ የጎንዮሽ ግንኙነት መሆኑን ጠቅሰው፤ ክልል ከክልል ያለው ግንኙነት በትብብርና ህግን መሠረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

የፌዴራሊዝም ሥርዓት ያለ መንግስታት ግንኙነት ጠንካራ ሊሆን አይችልም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ የመንግሥታት ግንኙነት በደንብ ባለመጠንከሩ ምክንያት ትንንሽ ችግሮች እየሰፋ ብጥብጥ ሲፈጥር ይስተዋላል ብለዋል።

አክለውም፣ በክልሎች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችን ክልሎች ራሳቸው በሰከነ መንገድ የመፍታት ባህል ሊያጎለብቱ እንደሚገባ ጠቁመው፣ አንዳንድ ክልሎች በዚህ በኩል ብዙ ለውጥ እንዳመጡም መግለጻቸውን ከሰላም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
Please wait, video is loading...

Re: ክልል ከክልል ያለው ግንኙነት በትብብር እና ህግን መሠረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡- ሰላም ሚኒስቴር

Posted: 18 Jun 2023, 11:08
by Abere
ይህ በትክክል በተግባር ላይ ውሏል :lol: የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ ተገኝተው በአሜሪካ አደራዳሪነት በአፍሪካ ዩኒየን ሰብሳቢነት በትብብር እና በህግ ችግራቸውን በመፍታታቸው።በአንጻሩ የኦሮምያ ክልል ወይም የኦሮሞብልጽግና ሊቀመንበር በፕሪቶራiው ጉዳይ ላይ ጣልቃ አለመግባታቸው ይህን ያረጋግጣል።ወደየት አገር ሂደን እንሳቅ እባካችሁ። የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ይላሉ እንድህ አይነቱን የወያኔ እና ገልቱ ኦነግ የሞኝ ብልጥ።

በመጀመሪያ ትግራይ ክልል ለመሆን ሳይሆን አገር ለመሆን እያሽኮበኮበች ያለች ምስኪን ክፍለ ሀገር ናት - ፈረንጆች ኢትዮጵያን ለማጥመድ ትግራይን ከወጥመዱ አፍ ላይ እንደ ቀይ ሥጋ አስቀምጠው እያተጫወቱብት ያለ ህዝብ። ይህን አይነቱን ቀልድ ከኢትዮጵያ ውጭ ሂዳችሁ ተጫወቱ ከፈለጋችሁ ኡኡ ጆባይደን :mrgreen: ማለት ትችላላችሁ።

የሚያሳዝነው ግን ለምን ይሆን የትግራይን ህዝብ ጊዜ እና ዕድሜ በከንቱ የምታባክኑት። እናንተ 1 ሚልዮን ትግሬ አስጨርሳችሁ በመጨረሻ ሻንጣችሁን እየጎተታችሁ አሜሪካ ሰርቃችሁ ወደ ገዛችሁት ቤት ትመጣላችሁ። ምስኪን የትግሬ እናት ግን ጧሪ እና ቀባሪ ልጇን አጥታ በሀዘን እና በእርሃብ ትኮማተራለች።