የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 25 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ ድጋፎችን ለትግራይ ክልል አስረከበ
Posted: 12 Jun 2023, 07:32
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 25 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ ድጋፎችን ለትግራይ ክልል አስረከበ
*******************************
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ 25 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ምርጥ ዘርና የምግብ እህል ድጋፎችን ለትግራይ ክልል አስረከበ።
ድጋፉን ያስረከቡት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋየ ማሞና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ አለባቸው ናቸው።
ድጋፉ 10 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብና 15 ሚልዮን ብር ግምት ያለው 2 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር፣ ዱቄትና ቦቆሎ መሆኑን የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ፀጋየ ማሞ ገልጸዋል።
የክልሉ ሕዝብና መንግስት ለትግራይ ክልል ያደረገው ድጋፍ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አለመሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይ ክልሉን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች የተረከቡትን ድጋፍ በፍጥነትና በፍትሃዊነት ለተጠቃሚው እንደሚያደርሱ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር እያሱ አብረሃ፣ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የተደረገው ድጋፍም የክልሉ ህዝብና መንግስት የትግራይ ህዝብ አለኝታ መሆኑን ያሳየበት እንደሆነም ገልጸዋል።

Please wait, video is loading...