Page 1 of 1

የወረሙማ አንድ ጎሳ ገነንነት ለማሳካት 2 ፓርቲዎች አያስፈልጉም! ብልጽግና በቂ ነው! የኢዜማ መፍረስ የሶሺያ ቢሄቪየር ሕግ ነው!

Posted: 30 May 2023, 23:55
by Horus
በቢዝነስ ማነጅመንት አንድ ማክሲም አለ ። ለአንድ ስራ ሁለት ሰው ተቀጥሮ ከሆነ አንዱን አሰናብት ይባላል ። ወረሙማን ለመስራት 2 ፓርቲዎች ምን ያደርጋሉ? አንዱ በቂ ነው! ኢዜማ መሰናበቱ ማለት መበተኑ የዚያ ሎጂክ ውጤት ነው ። EZEMA has no reason to exist; it has no purpose to serve; it has no value to add to Ethiopia. Hence, its demise is logical. Ditto.


Re: የወረሙማ አንድ ጎሳ ገነንነት ለማሳካት 2 ፓርቲዎች አያስፈልጉም! ብልጽግና በቂ ነው! የኢዜማ መፍረስ የሶሺያ ቢሄቪየር ሕግ ነው!

Posted: 31 May 2023, 01:54
by TGAA
Horus wrote:
30 May 2023, 23:55
በቢዝነስ ማነጅመንት አንድ ማክሲም አለ ። ለአንድ ስራ ሁለት ሰው ተቀጥሮ ከሆነ አንዱን አሰናብት ይባላል ። ወረሙምን ለመስራት 2 ፓርቲዎች ምን ያደርጋሉ? አንዱ በቂ ነው! ኢዜማ መሰናበቱ ማለት መበተኑ የዚያ ሎጂክ ውጤት ነው ። EZEMA has no reason to exist; it has no purpose to serve; it has no value to add to Ethiopia. Hence, its demise is logical. Ditto.

እኔ የጠበኩት ኢዜማና ብልጽግና አብረው ይከስማሉ ብዬ ነበር ፤ የኢዜማ እራሱን ከአመራሩ በመለየት መፈረካከስ እንደ ጥሩ ነገር አይቼዋለሁ ፤ ኢዜማ የኦሮሙማ ሎሌ ሆኖ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንዳሰናከለ ሁሉ በውስጡ የኢትዮጵያዊነትን አርማ አንሰተው መጓዝ የሚችሉ ሰዎች አሉት ብዬ ስለምገምት ነው፤ ግራ የገባኝ ግን እንደዚህ በብዛት እራሳችውን ይዘው መውጣት ከቻሉ ለምን አዲስ ፓርቲ ወጥተው አልመሰረቱም ፤ ወይም ደግሞ ብርሃኑን ጨምሮ በውስጥ ያሉትን የብልጽግና ሎሎዎች no confidence vote ስጥተው አላስወገዱቸውም ፤ የአብይ መንግስት ያዋክባቸው ነበር ግን ወዲያውኑ በሌላ የፖለቲካ ፓርቲ ስም እራሳቸውን ቢያደራጁ የህዝብ ድጋፍ ማግኘት ይችሉ ነበር ፡፡ በኔ ግምት ፡፡

Re: የወረሙማ አንድ ጎሳ ገነንነት ለማሳካት 2 ፓርቲዎች አያስፈልጉም! ብልጽግና በቂ ነው! የኢዜማ መፍረስ የሶሺያ ቢሄቪየር ሕግ ነው!

Posted: 31 May 2023, 03:16
by Horus
TGAA
በእኔ እምነት ኢዜማ እይሆነ ያለው ልክ እንደ ኢትዮጵያ መከላከያ ነው ። አባላቱ ከተለያየ ጎሳ የመጡ ናቸው፣ በመሰረቱ አማራ፣ ጉራጌና ደቡብ ናቸው። ከደቡብም ጋሞ፣ ወላይታና ከምባታ ። ብርሃኑ ነጋና ኢዜማ በጣም ግዙፍ ድጋፍ ያገኙበት ሕዝብ በመከራው ሰዓት አንድ ተጽኖ ፈጣሪ ፓርቲ ድጋፍ በሚሹበት ሰዓት ብርሃኑ እጅግ አጥንት በሚሰብር መልኩ ክልልነት አይገባችሁም አለ። ጉራጌ በነቂስ ኢዜማ ትቶ ጎጎት ፓርቲ አቆመ ። ምን ያክል ጉራጌ በኢዜማ ውስጥ እንደ ነበር ታውቃለህ ።

ሌላው አማራ ነው ። ብርሃኑ ካማራ ጋር ያለው ችግር እስከ ቅንጅት፣ ቀስተ ደመና፣ ግ7 እና አርበኞች ግምባር ይሄዳል ። ከዘመነ ካሴ፣ ከባልደራስ ጋር.. ስለዚህ ዛሬ ላይ ያማራ መልቀቅ አያስደንቀኝም ። በእኔ ጥርጣሬ ይህ ረጅም ችግር (ብርሃኑና አማራ አክቲቪስቶች) እራሱ ብርሃኑን ወደ ኦሮሞቹ ጉያ ሳይገፋው አልቀረም ። እነሱ ጉያ ስለገባ ነው የራሱን ሕዝብ የካደው ።

አሁን ኢዜማ ልክ ኢ ህ አ ፓ እንደ ነበረው ነው ። አባላቱ ምናልባት ሌላ ፓርቲ ውስጥ ህይወት ማባከት ከንቱ ነው የሚል መደምደሚያ ሊደርሱ ይችላሉ ። ባይሆን ምኞቴ ነው! እኔ ኢዜማ ሆኜ ስለማላውቅ ውስጣቸው ያለው የሞራል ደረጃ ልገምት አልችልም !

ግን እንዳትረሳ የኢዜማ መፍረስ አቢይንም አይጠቅመውም! የጎሳ ፓርቲዎች በያሉበት ከጠነከሩ ያ ለወረሙማም አይመችም !