የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቅኝ ግዛት ያስገባ የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ፈቃድ ታገደ | "ቤተ ክርስትያናችን ከቅኝ ተገዢነት ትውጣ!" ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ
Posted: 21 May 2023, 11:11
"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቅኝ ገዢዎች ተይዛለች! ቤተ ክርስትያናችን ከቅኝ ተገዢነት ትውጣ!" ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ
የማህበረ ቅዱሳን ብሮድክስቲንግ አገልግሎት ቴሌቪዥን ፈቃድ በጊዜያዊነት ታገደ - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን
******************************************
የማህበረ ቅዱሳን ብሮድክስቲንግ አገልግሎት ቴሌቪዥን ፈቃድ በጊዜያዊነት መታገዱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታወቀ።
በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር አንቀፅ 70 ከተጠቀሱት ውስጥ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን በሐይማኖት ተከታዮች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት ማነሳሳት ወይም በሐይማኖት ተከታዮች መካከል አለመቻቻል እንዲፈጠር መቀስቀስ የሌለባቸው መሆኑ መደንገጉን ባለስልጣኑ ገልጿል።
ይሁንና ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ሰበር ዜና በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሚና ውጪ በሆነ አግባብ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያካሄደውን ስብሰባ የሚያውክና ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት ማሰራጨቱ ተረጋግጧል ብሏል።
ይህም የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን የሚተላለፍና በሀገር ሁለንተናዊ ሰላም ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል እንደሆነም አብራርቷል።
በመሆኑም ከጉዳዩ አጣዳፊነትና ሊያስከትለው ከሚችለው ጉዳት አንፃር በቀጣይ በባለሥልጣኑ ቦርድ ታይቶ ዘላቂ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ የጣቢያው ፈቃድ በጊዜያዊነት የታገደ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታውቋል።

Please wait, video is loading...