ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ እኔ ትግሬ አይደለሁም የትግሬ ዘር የለብኝም ብሎ የተናገረው በቪድዮ የተቀረጸ አለ። እሱን ፈልጌ እስከማገኘው ይችን አንብቡ
https://ayunile.wordpress.com/2017/05/0 ... %E1%88%88/
“የሽብር ወንጀል አልፈፀምኩም፤ይህንን ለማድረግ ማንነቴም አይፈቅድም፣ የታሰርኩት ግን አማራ እንጅ ትግሬ አይደለሁም በማለቴ ነው” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
Posted on May 3, 2017 by አያሌው መንበር
#የሽብር_ወንጀል_አልፈፀምኩም፤ሀሳቡም የለኝም፤#ማንነቴም አይፈቅድም” “…የታሰርኩት #እኔ_ትግሬ #አይደለሁም #አማራነኝ በማለቴ ነው”..ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ትናንት ፍ/ቤት ቀርቦ የተናገረው
(((የኮሎኔል ደመቀ ጉዳይ ተጨማሪ ዝርዝር)))
በትናትናዉ ቀን ተቀጥሮ የነበረዉ የኮ/ል ደመቀ ቀጠሮ
በቀረበዉ የክስ መቃወሚያ ላይ እና ተከሰሳሽ በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ በቀረበዉ አቤቱታ ላይ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡
የቀረበዉን የክስ መቃወሚያ በተመለከተ በፍ/ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ዉድቅ ተደርጓል ፡፡
ተከሳሽም የእምነት ክህደት ቃሉን እንዲሰጥ የተደረገ ሲሆን ኮ/ል ደመቀም
ም“የሽብር ወንጀል አልፈፀምኩም ፤ የመፈፀም ሀሳብም አልነበረኝም፤ ከማንነቴ ጋርም የሚጋጭ ፤ የቀረበብኝ ክስ ሰዉ ሁሉ በህግ ፊት እኩል ነዉ በብሄሩ እና በማንነቱ ምክንያት አድልኦ ሊፈፀምበት አይገባም የሚለዉን ህገ_መንግስታዊ መብት ተገን በማድረግ ትግሬ አይደለሁም እኔ አማራነኝ በማለቴ ነዉ“ በማለት የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል ፡፡
ፍ/ቤቱ በሰብዓዊ መብት አያያዙ ዙሪያ ዛሬም ብይን አልሰጠም ።ይልቁንም ማረሚያ ቤቱ በድጋሚ አስተያየት እንዲሰጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል ፡፡ ጉዳዩ ለግንቦት 28 እና 29 የዓቃቢ ህግ ምስክሮች ሲቀርቡ ለመሰማት በሚል ተቀጥሯል ፡፡
የዛሬዉን ችሎት አቶየኔነህ ስመኝ (የክልሉ ጠ/ፍቤት ፕሬዚዳንት) በሰብሳቢነት ተሰይሞ ነበር።
በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ክስየ ተመሰረተባቸዉ እና በፌደራል ከ/ፍቤት ጉዳያቸዉ እየታየ የሚገኘዉ እነ #አታላይ ዛፊን ጉዳይ የያዘዉ ችሎት የምስክሮቹ ስም ዝርዝር ለተከሳሾች እንዲደርስ በማለት ብይን የሰጠ ሲሆን በተመሳሳይ ጉዳይ ተከሳሽ በሆነዉ ኮ/ል ደመቀ ክስ ላይ ብይን የሰጠዉ የአ.ብ.ክ.መ ጠ/ፍቤት የምስክሮቹ ዝርዝር ለተከሳሽ #ሊደርስ_አይገባም በማለት ብይን ሰጥቷል።