በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ካሏት "ብርቅና ዕንቍ ዜጐች" መካከል ጥቀሱ ቢባል
Posted: 17 May 2023, 05:23
በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ካሏት ብርቅ ዜጐች መካከል ጥቀሱ ቢባል
“በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ኤርምያስ ጠቅል ኣመልጋንና ልደቱ ኣያሌውን ማፍራቷ እጅግ እድለኛ ሃገር ያደርጋታል።
ምክንያቱም ሁለቱም በሃሳብ ልዕልናና በሰላም መንፈስ ሃሳባቸውን ሲገልጹ እንጂ፡ ከቶውንም በጡንቻቸው ሲያስቡና የጥላቻ ንግግር ሆነ ድርጊት ሲከውኑ በበኩላችን ኣላየናቸውም።
ኤርምያስ ጠቅል ኣመልጋ፦ ኢትዮጵያ ውስጥ በኢኮኖሚው ረገድ ብዙ ነገር ለማዘመን የጣረ የልማት ፊተውራሪና ኣርበኛ፡ እልፍ ኣእላፍ መስናክሎችን እያለፈ በቅንነት ሲታትር አስተውለነዋል።
ልደቱ ኣያሌው፦ የቦለቲካ አስተሳሰቡ ምንም ይሁን ምን፡ ያመነበትን ጉዳይ በቃላት ቁልጭ አድርጐ በመግለጥ፡ ሁሌም በሰላማዊ ትግል በማመን፡ ኣሸባሪነትን እየተጠዬፈ፡ ለሃገሩ ያለውን ፖለቲካዊ ራእዪ ሲገልጥ አስተውለነዋል።
በመሆኑም “ኤርምያስን የመሰለ የልማት ኣርበኛና ልደቱ ኣያሌውን የመሰለ በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ ዜጐችን ከፈጣሪ መቸር፡ ለአንድ ህዝብ መታደል ነው! “ ብንል፡ ስንቱ ነውጠኛ ይነጫነጭ ይሆናል!
እርግጥ ነው ሁሉም ሰው ፍጹም ኣይደለምና፡ እነዚህ ዜጐች ስህተቶች ሊኖሯቸው ይችላሉ፤ ቢሆንም ግን ቅሉ ዓላማቸው ላይ ለመድረስ በሰላም ጐዳና የሚያደርጉት በጨዋነት የተሞላ ሰላማዊ ትግል ያስደንቃቸዋል።
ይህን ስንል ሁለቱም ኢትዮጵያውያን ዜጐች፡ በኤርትራ ልዑላዊነትና በኤርትራና ኢትዮጵያ የድንበር ብዪን ምልከታ ያምናሉ፤ በሁለቱ ጐረቤት ሃገሮች ፍቅርና ሰላማዊ የብልጽግና ጉዞም የማይናወጥ ኣወንታዊ ኣቋም ኣላቸው በሚል እሳቤ ነው!
እስቲ በዚህ “ቤተ ሙከራችን” እነማን እንደሚንጨረጨሩ እንዪ? ኣንዳንድ የጦርነት ጥቅመኞች (ጦ.ጥ.) ላይ ሆምጠጥ ያለ ‘ኬሚካል’ በመውጋት ‘ኤክስበርመን’ ለማድረግ ያክል ነው!