Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15425
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የትግራይ ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ህወሓት ነው። ብርቱካን ሚደቅሳ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ትቀልዳለች - ህወሓት ተሰርዟል።

Post by Abere » 14 May 2023, 11:20

የትግራይ ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ህወሓት ነው። ብርቱካን ሚደቅሳ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ትቀልዳለች - ህወሓት ተሰርዟል። :lol: በእርግጥ ህወሓት በሰው ደራጃ ከ 3-5 የሚደርሱ መሪዎች ቀርተዋል - በሙሉ በጦርነት አልቀዋል። በስም ጠርቶ የቀሩትን ቁሞ አልቃሽ ወያኔዎች መዘርዘር ይቻላል - በአካል ጠፍቷል። ህወሓት ሙቷል። አቶ አብይ አህመድ ግን ህወሓት ሰዎቹ ቢያልቁ እንኳን አለች ብሎ ማስቀጠል ይፈልጋል። ታዲያ ወ/ሮ ብርቱካን ዋና የኦነግ ብልጽግና አባል ሁና ይህ ምስጢር በእውነት ጠፍቷት ነው ወይስ ትዕዛዝ ከእቶ አብይ ስላልደረሳት ይሆን? ጌታቸው ረዳ እና ታደሰ ወረደ የሰላም ሽልማት ተሸላሚ ሲሆኑ እኮ የብቁ እና ትጉህ ፓርቲ አባል ተብለው ነው።