የአቢይ አህመድ አሊ ወረሙማ መንግስት አማራን በመውረር ወታደራዊ አገዛዝ ባማራ ሕዝብ ላይ የጫነው ሕግ ማስከበር በሚለው ሽፋን ነው ። በኢትዮጵያ 120 ሚሊዮን ሕዝብ አለ፤ 85 ብሄረ ሰቦች አሉ ። ይህው ያማራ አመጽ አንድ ሳምንት ሊሞላው አንድ ቀን ፈሪ ነው ። በዚህ ድፍን ሳምንት ውስጥ ከአቢይ አህመድና አሽከሮቹ በተቀር አንድ ሕዝብ፣ አንድም ብሄረ ሰብ፣ አንድም ድርጅት ያማራ ሕዝብ ሕግ ጥሷልና አቢይ ሕግ የማስከበር ሃላፊነት አለበት ብሎ ባማራ አብዮት ላይ ተቃውሞ ያቀረበ የለም ። ይህ እጅግ እጅግ አስገራሚና የወረሙማ አገዛዝ ምን ያህል ከሕዝብ እንደ ተነጠለ የሚመሰክር ሃቅ ነው ።
እንደ ሚታወቀው ሕዝብ እንደ ንቃቱና እንደ ባለደንታነቱ በግልጽ የሚደግፍ አለ፣ በጸጥታ የሚደግፍ፣ በድብቅ የሚደግፍ አለ ። እንዲሁም በግልጽ የሚቃውም አለ፣ በዝምታ የሚቃወም አለ ። ለምሳሌ ጥቂት የማይባሉ ጥቅመኛ ተረኛ ወረሞች በዝምታ አቢይ የሚደግፉና አማራን የሚቃወሙ ሊኖሩ ይችላሉ ። እነሱ ዛሬ ሜዳ ላይ ለሚድረገው ትግል ብዙም ፋይዳ አይፈይዱም ።
ስለሆነም ባማራ የሚካሄደው ትግልና ባገሪቱ ያለው ጸጥታ አለምንም ጥርጥር ያማራ አመጽ በሕዝብ ዘንድ ፍትሃዊ ሆኖ መታየቱን ያረጋግጣል ። ያ ማለት ደሞ የዲክታተሩ ሽንፈት ማለት ነው ። ዘዴ ፈልጎ ከዚህ ቅሌት ባስቸኳይ ማፈግፈግና ወደ ሰላማዊ መፍትሄ ማጎንበስ አለበት ! ያ ካልሆነ ሕዝባዊ አመጽ አይደለም ባማራ በደቡብ ይፈነዳል !
