"ማኔ ቴቄል ፋሬስ" በሚዛን ተመዘንህ ቀለህም ተገኘህ ። ት/ ዳንኤል 5:25
Godana Yacob
·
ይድረስ ለኤርሚያስ ለገሰ
-----------------//----------------
ይህንን ምላሽ ላንተ ባልሰጥ በወደድኩ ነበር ምክንያቱም በቀደመው ጽሁፌ ላይም እንዳልኩት I Can’t Stand Cowards! እራስህን ችለህ መናገር ሲገባህ በባለቤትህ ምላሽ ከመስጠት ያለፈ ውርደት የለም።
እሷን በአንተ ጉዳይ በቀጥታ address ማድረግ ለወንድነትህ፣ ለአባወራነትም ይሁን ለትልቅ ሰውነትህ የሚመጥን ስላልሆነ ይድረስ ላንተው ብዬ መፃፍን ወደድኩ። ለሌላ ጊዜ ግን የራስህን ትግል ታገል። ለራስህ መቆምና መታገል ሳትችል እንዴት ለሰው እና ለሀገር መታገል ትችላለህ።
እውነት ነው ኤርሚያስ ለገሰ በእስፒከር ላይ ስልክ ማውራቱ እቤት ውስጥ ካለው የነፃነት እጦትና እራስ ተገላብጦ በመሆኑ ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ሁሉም በዙሪያው ያለ ሰው የሚያውቀው ሀቅ ቢሆንም ያ የቤት ውስጥ ጉዳያችሁ እንጂ እኔ የሚመለከተኝ ጉዳይ አይደለም። ግን ያው የችግሩ ምንጭ አንዱ ኤርሚያስ እራሱን ችሎ መቆም አለመቻሉና ሁሌም ደጋፊ እሱን ወክሎ ተሟጋችን ተናጋሪ ስለሚፈልግ ነው። “እኔ ፈሪ ነኝ ልጅም ሆነን የሚጣላልኝ ወንድሜ ነበር!” በአደባባይ ማለቱ ለአድማጭ ትውስታ ትተነው እኔም ይህ ሰው ተፈጥሮ ፈሪ አድርጎ የፈጠረውና ለጥቃት ተጋላጭ ነው ብዬ በተቻለኝ መጠን ልከላከልለትና ከጥቃት ልታደገው ለአመታት ጥሬአለሁ። ይህም በቅርበት ሁለታችንንም የሚያውቁን ሁሉ የሚያውቁት ሀቅ ነው።
ምን ነበር የተፈጠረው?
በጦርነቱ ወቅት የነበረውን ውጥረትና የአቋም ልዩነት ሰው ያየው ፀሀይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው። ለረዥም ሰዓታት በሀሳብ ሳግዝህ፣ ፅሁፎች ሳነብልህ እና ተቋሙ በአቋም ልዩነት አደጋ ውስጥ እንዳይገባና እናንተም እንደማትለያዩ ሰርቻለሁ። ደክሚያለሁ።
ከEthio-360 ለመልቀቅና የራስህን ሚዲያ ለማቋቋም የነበረህን ፍላጎት የጦርነቱ ወቅት የፈጠረው የአቋም ልዩነት በፊትም ቢሆን የነበረህ፣ ያማከርከኝ፣ እናም አብረት እንስራ ያልከኝ ጉዳይ ነበረና በጦርነቱ ወቅት በተፈጠረው ውጥረት ማሳበብ አያስፈልግህም። የኔም ምላሽ የሚያውቁኝ ሰዎች ሁሉ የሚያውቁት ነው። እኔ የሚዲያ ሰው አይደለሁም!!! ብዙም የሚመስጠኝ አይደለም!!! ስለዚህም ከኔ ጋር የምትከፍተው ሚዲያ የለም። አይኖርምም። ብዬ ነግሬህ እንደነበር መቼት አትክደውም።
በነገራችን ላይ ሰው የራሴን ነገር ልክፈት ማለት ብቻ ይቻላል። የግድ ተጣልቼ፣ ተጠልቼ፣ ተገፍቼ ብሎ የሰቆቃ ሙሾ ማውረድ አስፈላጊ አይደለም። የሆነ ሆኖ ሚዲያ የሚከፋፈልበት ሳይሆን በአንድ ላይ ተሰባስቦ ሀገር እና ሕዝብ ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ ያስፈልጋልና አትውጣ! እኛ ከጎንህ አለን! ብዬ ከፕሮግራም በፊት እና በኃላ ምክርም ሀሳብም ድጋፍም እየሰጠሁን ያንን አስቸጋሪ ጊዜ በፅናት እንድንሻገረው እንደደከምኩ አንተም ከእስፒከሩ ጀርባ ሆና የምታዳምጠው ባለቤትህ ታውቁታላችሁ።
ትግሉን ከገቢ ምንጭነት አንፃር እንጂ ከእምነት እንደማታደርገው፣ ብቻህን ብትወጣም የተሻለ ገንዘብ እንደምትሰራ ስትነግረኝ “ቁርበት ስለ ቁርበት ነውና” ብቻ መስራት ያለውን ድካም እና የገቢ ማሽቆልቆል አንድ ሁለት ብዬ ነግሬህ እንጂ ለመቆየት ያሰብከው ካለቀቅኩ እያልክ እንደነበር በዙሪያህ ያለ ሰው ሁሉ የሚያውቀው ነው። እንዳልኩት እኔም የመውጣትና የራስህን ሚዲያ የማቋቋም ፍላጎት እንዳለህ ካወቁኝ አመታት አልፈውኛል። በግሌ ባልወደውም፣ ለትግሉ ይረዳል ብዬ ባላምንም ግን በማንኛውም ምክንያት መውጣት እና የራሴን ጎጆ መቀለስ እፈልጋለሁ ካለ መብቱ ነው ባይ ነኝ።
(1) ችግሬ የቆየና ከግንዘብና ከጥቅም ጋር የተያያዘን የራስ ጎጆ የመቀለስ ፍላጎት የብሔር ካባ አልብሶ ለማቅረፍ የሄደበት ወራዳ አካሄድ ነው። እውነት አይደለም።
ሀብታሙም በአማራነቱ አንተም በኦሮሞነትህ አይደለምና በብሔር ካባ ተደብቀህ ከጎን የነበረውን መላውን የEthio-360 አባላት አትካድ! ሳታማሀኝ ብላ!!! የሚል ነው። የብሔር ጨዋታ ልትጫወት እየዳዳህ እንደሆነ ስለገባኝም ነው እኔም ወደማልወደው የሚዲያ መድረግክ ብቅ ያልኩት። ዋቅጅራነትህን መነገጃ ልታደርገው ስለፈለግክ ነው ጎዳና የቦረናው ኦሮሞ ሆኜ ወደ መድረኩ የመጣሁት።
የአማራ ማኅበረሰብም ይሁን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለኤርሚያስ ለገሰ መልካም ሆኖ ሳለ በስተርጅና ለገንዘብ ለገንዘብ መሰብሰቢያነት ይረዳልና ኦሮሞነቴ ይጠቅመኛል ብሎ ከክፏም በደግም አብሮት የነበረና ሲደግፈው የኖረውን የአማራም፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ በገንዘብ ሲቀይረው በአደባባይ ልቃወመውና ላነውረው ይገባልና በአደባባይ ግልጽ ደብዳቤ ጽፌለታለሁ።
ለርካሽ ጥቅም በኦሮሞ ጉያ ውስጥ መወሸቅ አብይ አህመድም ሲያደርገው ነውር ነውና እቃወመዋለሁ!!! ኤርሚያስ ለገሰንም እቃወመዋለሁ!!!
ሰው መቼም ሰው ነውና እኔም ነገ ተነስቼ በኦሮሞ ግያ ውስጥ ተወስቄ ርካሽ ትርፍ ለማግኘት ከቃጣኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በአደባባይ እንደሚቃወመኝና እንደሚያነውረኝ ተስፋ አደርጋለሁ!!!
ካለምንም ምህረት በአደባባይ እንዲቃወሙኝና እንዲያነውሩኝ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከአሁኑ እለምናለሁ!!!
ብሔርተኛነት ጥንብ ናትና ነውርን ነውረኛ ስሆን ነውረኛነቴን እንዲነግሩኝ ያስፈልጋል!!! እንደ ኢትዮጵያዊያን የመዳን ተስፋ ካለን እውነት በመነጋገርና እና ነውረኛን ነውኛ በማለት ነው። ለመወሻሸት የሚሆን ጊዜ ላይ አይደለንም!!!
(2) ከትግሉም ባሻገር፣ ከኢትዮጵያ የህልውና አደጋ ኤርሚያስን ለገሰ ከEthio-360 “ውጣ” ብዬ የዛኔም ያልመከርኩት አሁንም ወደ ቤትህ ተመለስ የምለው ለራሱ ለኤርሚያስ ለገሰ ስል ነው። ካንቺ ባርነት በሀሳብም በገንዘብም ነጻ እንዲወጣ ስለምፈልግ ነው።
ወንድ ልጅ ስልኩን ስፒከር ላይ ሳያደርግ ማውራት አለመቻል ከአዕምሮ በላይ የሆነ ጭቆና ነው። ከሰው ሁሉ ተነጥሎ ብቻውን መሆኑ የአዕምሮ መታወክ እንዳይፈጥርበት፣ ወደፊትም እራሱን ሌሎችንም እንዳይጎዳ፣ ብቻው ቀርቶ ያንቺ መጫወቻ እንዳይሆን ስለምሰጋ ነው።
የፈራሁት ደርሶ ከሚዲያው ለቆ ብቻውን ባንቺ ሙሉ ቁጥጥር ስር ስለወደቀ እጅግ አዝናለሁ። ኤርሚያስ ከሚዲያው ስለመልቀቁ በተናገርኩ ጊዜ «በወንድማማቾች ዘንድ ፀብን የሚጭሩ እና ድንጋይ የሚያቃብሉ የእብድ ገላጋዮች» ስል አንቺን እና አንቺን ብቻ ታሳቢ አድርጌ ነው።
ኤርሚያስ እራሱን ችሎ መቆም፣ በራሱ ማሰብ የማይችል ስለሆነ ወዳጅ አልባ ሆኖ በአንቺ እጅ እና ባንቺ ምህረት ውስጥ እንዳይወድቅ ነው ወደ ቤቱ ወደ Ethio360 እንዲመለስ የምፈልገው። ለዛም ነው የዛኔም እንዳይወጣን ቆፍጠን ብሎ የአቋም ልዩነቱን እንዲጋፈጠው አብሬው ቀን ከሌት የቆምኩት!!! የሰራሁት!!!
ለዚህም ነው ኤርሚያስ “ከዛሬ ምን አለ?” ሲወጣ እረፍ አድርጎ እስኪመለስ፣ ጥቅምና ጉዳቱን አስልቶ እስኪመለስ ፈረቃውን እንሸፍንለት ብለን ተረባርበን የመጣነው። ቦታው ለሱ ተጠብቆ ይቆይ። ግን ደግሞ ዛሬን በሀገር ላይ ሸፍጥ የሚሰራ፣ ዜጎችን ለሰቆቃ የሚዳርገው የአብይ አህመድ አገዛዝ አለና የሕዝብ ድምጽ የሆነ ሚዲያ አይስተጉጎል፣ ለሕዝብም መረጃ የማድረስ ስራ ይቀጥል። ግን ደግሞ የኤርሚያስ ቦታም ወደቤቱ እስኪመለስ ድረስ ይጠበቅ ብለን ብንመጣ ነው እንግዲህ «ፕሮግራሞች ተጨናነቁ፣ ሌሎች ሰዎች መጡ» ብሎ በሱ አለመኖር የተፈጠረን ክፍተት ለሞምላት የመጣን ሰዎችን ኤርሚያስ ለገሰ የሚከሰው።
ዳሩ ግን ኤርሚያስ እራሱን፣ የማሰብ አቅሙንም አጥቶ ነውና ያለው የሱን ጎዶሎ ለሞምላት የመጡትን ሰዎች ማመስገን ሲገባው መክሰስ እና መውቀስ የጀመረው በሱ የሚያቄም ሰው አይኖርም።
እግዚአብሔር በቶሎ ወደ ቀልቡ ይመልሰውና ከአንቺም ባርነት ወጥቶ አብሯቸው ስንት ጥሩም መጥፎም ጊዜ ወዳሳለፋቸው ወደ የስራ ባልደረባዎቹ፣ወደ ወዳጆቹ፣ ወደ ቤቱ፣ እና አብሮን ደፋ ቀና ወዳለው የአማራ ማኅበረሰብን እና ወደ ኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ይመልሰው። ባልሽን የምታከብሪ፣ አባወራነቱ የምታከብሪ፣ ወንድነቱ የምታከብሪ ሴት ብትሆኚ ኖሮ ይህ ደብዳቤ መፃፍ ካለበት እሱው እራሱ እንዲፅፈው ታደርጊ ነበር እንጂ በአደባባይ ይህንን ደብዳቤ ይዘሽ ባልወጣሽ ነበር። እሱም ከቀልቡ ቢሆን ኖሮ ሼር ባላደረገው ነበር።
ይህ ክስተት ብቻውን ኤርሚያስ ለገሰ ያለበት የአደጋ መጠን እና ለምን ወደ ቤቱ መመለስ እንዳለበት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። እራስ የተገላበጠበት ቤት ውስጥ መኖሩ ሳያንስ እንዴት አደባባይ ገበናሽን ይዘች ኤርሚያስ ለገሰን የመሰል ትልቅ ባለ አዕምሮ፣ የኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ አምድ የሆነን ሰው ልታዋርጂ አደባባይ መውጣት እንዳስፈለገሽ አላውቅም። ነገር ግን ወዳጅነቴ ለኤርሚያስ ነውና ያንቺን ሱሪ መልበስ የማየው ኤርሚያስ ላይ ከሚደቅነው አደጋ አንፃር ብቻ ነው።
ኤርሚያስንም ዘልፈንም ወቅሰንም ወደ ቤቱ እንዲመለስ ማድረግ የሚያስፈልገውና ከስፍራዬ ወርጄ ያለመደብኝን እንዲህ አይነቱን ውረድ እንውረድ የተያያዝኩት ከኤርሚያስ ደህንነት የኔ ክብር ስለማይበልጥ ነው። ሕይወት ይቀድማል ብዬ ነው!!! ደኅንነት ይቀድማል ብዬ ነው!!! ስለምራራለት ነው!! እሱ እየዞረ በሀሜት ጅራፍ ቢገርፈኝም አሁንም እንደ ወዳጄ ስለምቆጥረው ነው!!!
(3) « በወቅቱ እኔ ብሆን ኖሮ» ላልሽው በአደባባይ እኮ ነው ከEthio360 ጋር የማይታረቅ ልዩነት ውስጥ ስለገባሁ ወደ ሚዲያው አልቀርብም ያልኩት። እኔ ወደ የትኛውም ሚዲያ ስቀርብ ከነሙሉ ክብሬና ከነሙሉ ጥቅሜ ነው። ጎዳናን ሆኜ ነው!!! ጎዳናን ደግሞ እጅግ የማከብረውና በማንም፣ በምንም የማለውጠው ሰው ነው!!! ስለዚህ ሆኖ መገኘትን እንጂ «እኔ ብሆን!» ብሎ ዛቻ አይቃጣኝም። በኔ እምነት ዛቻ የሚያበዙ ሰዎች ሆኖ መገኘት የሚቸግራቸው ናቸው።
ከኤርሚያስ ለገሰ ጋር በሁለንተናዊ እይታ በቋሚነት ስናደርጋቸው የነበሩትን ውይይቶች ሰርዤ ከሚዲያው የተለያየሁት አንቺ በስፒከር ላይ ሆነሽ በምታዳምጪው ስልክ ነው። ከኤርሚያስ ለገሰ ጋርም መጨረሻ በስልክም ያወራሁት የፍርድ ቤት ጉዳይ እልባት ባገኘበት እና ከፍርድ ቤት ውሎው በኃላ በዛሬ ምን አለ? ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። የዛን ወቅት ነው ደግሞ «ኤርትራዊያን በምንኖርበት ኮንዶ ውስጥ እየተበራከቱና ነውና እንዳይገድሉኝ ስጋት ውስጥ ነኝ » ሲል Ethio360 ድጋፍ ጠይቅ እነሱም የሚያስፈልግህን ሁሉ ድጋፍ ይሰጡኸል » ብዬ እርግጠኛ ሆኜ ምክር የሰጠኃችሁ። እኔ በዚያን ወቅት ከሀብታሙ ጋር ጥርስ የምሳበርበት ወቅት በሆነበት ሰዓት እንኳን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚሰጦችሁ እርግጠኛ ሆኜ ያማከርኳችሁ።
የሆነውም ደግሞ እንዳልኩት ነው!!! ከማንም በላይ ሀብታሙ አያሌው ነው ተሯሩጦ ወዲያው አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንድታገኙ የበኩሉን ጥረት ያደረገው። ጭቡ መጥፎ ነው። እውነት ደግሞ እውነት ናት!!! የጎዳናን ድጋፍ ወይም ተቃውሞ ሳትፈልግ በራሷ መቆም የምትችል ናት እውነት!!! ለዚህ ነው እውነትን መሸቀጫ የማላደርጋት!!!
ለዚህም ነው እውነትን ስትሸቅጡባት እጄን አጣጥፌ ቁጭ ብዬ የማላያችሁ!!!
ለዚህም ነው ጉዳዩን የብሔር ልታደርጉት ስትጥሩ በዝምታ ማለፍ አልቻልኩት!!!
ከሀብታሙ ጋር ኤርሚያስ የነበረው ፀብ የብሔር ሳይሆን የአቋም እንደሆነ ደግሞ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ማንኛውም ሰው የሚያውቀው ሀቅ ነው!!!
ኤርሚያስ ለገሰ ደግሞ የራሱን ሚዲያ የማቋቋም ፍላጎት እንዳለው የነገረኛ አብረን እንድንሰራ የጠየቀኝ ከጦርነቱ በፊት ነው!!! የአቋም ልዩነት ከመፈጠሩ በፊት ነው!!! ይህን ሀቅ ደግሞ ኤርሚያስ ብዙ ሰዎች የሚያውቁት እውነት ስለሆነ እዚህ ላይ የማጠፋው ጊዜ አይኖርም።
አሁንም ለኤርሚያስ ለገሰ የምለው ነገር ቢኖር የብሔር ጭቆና የሚል እንቶፈንቶህን ትተህ ተገለህ ብቻህን በመቅረትህ የምትጎዳው እናም እየተጎዳህ ያለኸው አንተና አንተ ብቻ ናችሁና ለማንም ብለህ ሳይሆን ለራስህ የአዕምሮ ድህንነት ስትል ወደ ቤትህ ተመለስ። እኔንም ያንተን ፈረቃ በመሸፈን በየሳምንቱ ሚዲያ ላይ ከመቅረብ ታደገኝ!!! በኦሮሞ ጉያ ውስጥ ተድብቀህ «በኦሮሞነቴ» የምትለው የቅጥፈት ጫወታ የከሸፈችው ጎዳና የሚባል ኦሮሞ ያውም ቦረና አንተን ወንበር ለማስጠበቅ ብቅ ሲል ከሽፏል። ያን ያደረግኩት ደግሞ እንዴት እንደምታስብ እና ምን ለማድረገ እንደምትችል ጠንቅቄ ስላወቅኩት ነው። የብሔር ጨዋታዋ አንተ አዘውትረህ እንደምትለው « የተበላች እቁብ » ሆናለች።
ዛሬ እማወራህ ወጥታ ለመውጣት ያሰብከውና እሷም ውጣ ስትልህ የነበረው ከአመታት በፊት እንደሆነ ስትናገር « የፕሮግራም መጣበብ፤ ትላንት ለመጣ አዲስ ሰው ብዙ ቀናት ሰጥተው እኔን ገፏኝ» የምትላት የሰቆቃ ክስ ውሸት እንደነበረ ለአድማጭ ቁልጭ አድርጋ አሳይታለች። ኢትዮ360 ከተቋቋመ ጀምሮ መጨረሻ ለጸብህ እንዲመችህ፣ ለአቤቱታ እንዲሆንህ ከሰራኸው ፕሮግራም ውጭ ማክሰኞ ማክሰኞ ፕሮግራም ሰርተህ እንደማታውቅ ሁሉም ወደኃላ መለስ ብሎ ሊያየው እና ሊታዘብ የሚችለው ሀቅ ነውና ሕዝብ አትናቅ። እንኳን ማክሰኞን ይቅርና ለአመታት በሞኖፖል የያዝከውንም አርብን በሙላት ተጠቅመህበት እንደማታውቅ ሕዝብ ወደኃላ መለስ ብሎ ሊያየው የሚችለው ሀቅ ነውና ሕዝብን አትናቅ።
በምናላቸው መመለስ አንተ የተገፋህ ለማስመሰል የሄድክበትን እርቀት አፈር ከድሜ የሚያስገባ የቆየ ፍላጎት መኖሩን ስለተናገርሽ ላመሰግንሽ እወዳለሁ። ግፍ እና ቅጥፈትን አብይ አህመድ ሲያደርገው ብቻ ሳይሆን ማንም ያድርገው ማንም በአደባባይ እቃወማለሁ። ሀብታሙ ትክክል አይደለም ባልኩባቸው ጉዳዮች ላይ በአደባባይ እና በግልጽ በስሙ ጠርቼ ተቃውሜዋለሁ!! ኤርሚያስም እንደዚህ አይነት ቅጥፈት ውስጥ ሲገባ በግልጽ እየተቃወምኩት እገኛለሉ። ምክንያት ቢባል ህግ እና መርህ ወይ ለሁሉ ይሰራል!!! ወይ ለማንም አይሰራምና ነው!!! ይዤ የምዞረው ሁለት መስፈሪያ የለኝምና ነው!!!
ለማንኛው ኤርሚያስ በቃ መውጣት ስለፈለግኩ፣ የራሴን ነገር ማቋቋም ስለፈለግኩ እየወጣሁ ነውና መርቃችሁ ሸኙኝ ማለት ማንን ገደለ?! ከተቋሙ የለቀቀ ብቸኛ ሰው አይደለህም እኮ? እስቲ ምንአላቸውን እየው? ተቦርነንና ርዕዮትን እያቸው? «ከጨዋ ጸብ ከፍቅር አንድ ነውና» በጨዋ ደንብ ወጥተው የራሳቸው ስራ ይሰራሉ። በሚፈልጉት መንገድ ይጎዛሉ። ምንአላቸው ያለውን መልካም ግንኙነት ሳያደፈርስ ባመነ ሰዓት ወጣ፣ አንድ ላይ መሆኑ ይጠቅማል ሲል ተመለሰ።
ምን አለበት አንተም የግንኙነት ድልድዮችን ሁሉ ሳትቆራርጥ እና ነገ እግዚአብሔር ሰውን እንዴት መልሶ እንደሚያገናኝ ሳትዘነጋ በጨዋ ደንብ ስራህን አርፈህ ብትሰራ? የሀሳብ መድረክ እከፍታለሁ ብለህ ቃል የገባኸው ጠብቀህ የሀሜት ገበታ ባታደርገው? እራስህ ቻል!!! ስራህን ስራ!!! ኑሮህን ኑር!!!
እግዚአብሔር የተሻለ ቀን እሲኪያመጣ የራስህን ሩጫ እሩጥ እንጂ የሀሜት ሱሰኛ፣ የሀሜት ግዞተኛ አትሁን!!!
እኔ በግሌ ያ ቀን እስኪመጣ ድረስ ላንተና አንተን በተመለከተ የመጨረሻ አስተያየቴ ናት!!! ሰው ከእኩያው ጋር ነው ክፏ ደግ የሚነጋገረው እና አሁን ላይ ባለህበት ዝቅጠት ከአቅም በታች ነህና እንደ እኩያዬ ላወራህ አልችልም ፈጣሪ ምህረቱን እስኪያመጣልህ እና አንተም ቀልብ እስከምትገዛ ድረስ ካንተ ጋር መመላለስ መውረድ ነውና ሰላም ሁን!!! ለማኅበረሰቡ ያለውን እውነት በጥልቀት የማውቀውን እውነት አሳውቂያለሁ። Unlearn ማድረግ ከቻል ኖረህበት በማታውቀው ኦሮሞነት ለመደበቅ የምትሄድበት እርቀት እና አማራ ጨቆነኝ የሚለው ለቅሶህ ከእውነት የተፋታ የGoFundMe አጀንዳ እንዳልሆ ማሳየት ነበር አላማዬ ያን ጨርሼ ብእሬን በቅያለሁ::
እግዚአብሔር የተሻለ ቀን አምጥቶ በቸር ይግጠመን!!!
Please wait, video is loading...