Page 1 of 1

ኢትዮጵያ ትልቅ ያጣችው ቅርስ 1) የሽማግሌ ባህል ወግ መጥፋቱ ተአማኒነት ማጣቱ 2) የፍርድ ቤት እና ፓሊስ ተቋም መጥፋቱ (የፍትህ ስርዐት መደምሰሱ)

Posted: 28 Apr 2023, 11:47
by Abere
ኢትዮጵያ ትልቅ ያጣችው ቅርስ 1) የሽማግሌ ባህል ወግ መጥፋቱ ተአማኒነት ማጣቱ 2) የፍርድ ቤት እና ፓሊስ ተቋም መጥፋቱ (የፍትህ ስርዐት መደምሰሱ)

1ኛ) የሽማግልና ባህል የሚሰራው አቻ የማህበረሰቡ አስተሳሰብ እና ዕውቀት ባለበት ዘመን ነው። በአሁኗ ኢትዮጵያ ዕድሜ ጠገብ የተማሩ ምሁሮች ሽማግሌ እንዳይሆኑ እራሳቸው የየስርዐቱ ውታፍ ነቃይ ካድሬዎች ናቸው። ከሽማግሌነት ሚና ተወግደዋል - የሚሸመገሉ እንጅ የሚሸምግሉ አይደሉም። ሌሎች ዕድሜ ጠገባ ያልተማሩ ወይም በትምህርት ብዙ ያልገፉት ቄስ፤ ቃልቻ ወይም የሰፈር ሽማግሌዎች ናቸው። እነኝህ ከሰለጠነ የፓለቲካ መሰሪ ጋር ዕርቅ ለማስቀመጥ አይችሉም። ወይም እራሳቸው በቀላሉ በጥቅም ይሸወዳሉ ሌሎችን ያሸውዳሉ። በእነርሱ ቤት ንጉስ አይከሰስ አይነት እምነት ነው ያለው።

2ኛ) የፍትህ ስርዐቱ ሙሉ በሙሉ ይሉኝታ በማጣት ፈራርሷል። ቱባ ቱባ ወንጀለኞች በር ከፍቶ እየለቀቀ፡ ምንም ወንጀል የሌለባቸውን አብይን ወይም ኦሮሙማን ይቃወማሉ በማለት ብቻ የሚስር የሚያሰቃይ የወንበደ መጠቀምያ ነው። ይህ የማፍያ ድርጅት ለምን የህዝብ የግብር ገንዘብ እየተከፈለው እንደሚኖር ይገርመኛል። መዘጋት ያለበት የማፈያ ተቋም ነው። ይህ እነ ስብሃት ነጋ ወዘተ ነፍሰ በላ የለቀቀ ግን መርካቶ 5 ብር ሰረቀ ወይም አረንጓደ ብጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ ልብስህ ወይም ለምን አዲስ አበባ አልክ ፊንፊን አትልም ወይ ብሎ አስሮ የሚያኖር የሚደበድብ የማፍያ ድርጅት ራዕይ የሌለው የዱርየ ነው። ፍትህ ተቋም በኢትዮጵያ የለም።