Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7367
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ከነዉር ባህል እና ከክርስትና ሃይማኖት የቱ ይቀድማል?

Post by Naga Tuma » 26 Apr 2023, 20:08

ስለ ኢትዮጵያ ህዳሴ ወይም ግስጋሴ በርካታ ተብሏል። የዚህ ጥያቄ መልስ ይታወቃል? ማወቅ ይቻላል? በሌላ አነጋገር የነዉር ባህል ምንጭ ምንድነዉ? መቼ ነዉ የተጀመረዉ? ከእየሱስ ልደት በፊት ነዉ ወይስ በኋላ?

Naga Tuma
Member+
Posts: 7367
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ከነዉር ባህል እና ከክርስትና ሃይማኖት የቱ ይቀድማል?

Post by Naga Tuma » 21 Jul 2023, 16:59

የኢትዮጵያ የብርሃን ዘመን የጀመረዉ መቼ እንደሆነ በዉል ይታወቃል? በሌላ አነጋገር በዚህ ዘመን አብረሆት ከተባለ የኢትዮጵያ የብርሃን ዘመን መቼ ጀመረ?

የጥንቱ ካህን ፀሓይ ተኮር ብርሃን ካለበት ዘመን ነዉ?

ወይስ ከስደቱ በኋላ በእግዝኣብሔር የተመረጡ ሕዝብ ካለበት ዘመን ነዉ?

ወይስ ከንግስቷ ጉብኝት በኋለ ነዉ?

ወይስ ከኣዳኙ ስቅለት በኋላ ነዉ?

ለዚህ መሠረታዊ ጥያቄ በቂ መልስ ኣለ?

በባህል ነዉር ማለት ጥልቅ ትርጉም ኣለዉ። ሰፉም እንደዛዉ።

እነዚህ ፅንሰሀሳቦች በየትኛዉ ዘመን ይሆን ለመጀመርያ ግዜ የተስተዋሉት?

በእኔ አስተያየት እኛ ብዙ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊያን ቀላል ጥያቄን ኣሰላስሎ በትክክል መመለስን በሰፊዉ ኣልለመድንም። ጥያቄዉን በደንብ ሳናሰላልስል ለመመለስ ይምንጣደፍ ብዙ ነን። ጌታ ሲባል እንባ ቅርባቸዉ የሆነ ብዙ ናቸዉ። ይህ የምያመለክተዉ የስቅለት ዘመን የጀመረ ትምህርት ሰፊ ተፅዕኖ እንዳለዉ ነዉ።

ቢሆንም ምናልባት ባህል ዉስጥ በሰፊዉ የሚታወቁት እንደ ነዉር እና ሰፉ ያሉ ፅንሰሀሳቦች ከስቅለት ዘመን በፊት ጀምሮ የሚታወቁ ከሆነ የኣንድ ዘመን ክስተትን እና ከዛ በፊት የነበረን የባህል ጥልቀት ማጣጣም የሚቻለዉ እንዴት ነዉ? ብዙ የሳይንስ ፍሬዎች በዙሪያችን ሞልተዉ የሳይንስ ሃያልነትን ጥቅም በኣግባቡ ማስተማር እንጂ ማቆም ወይም ወደኋላ መመለስ ኣይቻልም።

ይህን ያምያስጠይቀኝ ኣንድ ምንም ሊገባኝ ያልቻለ ምሳሌ ኣለ። ሰን እና እኔ በኣብዛኛዉ ተቀራራቢ አስተያየት ያለን ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል። በአካል ባላዉቀዉም እዚህ ፎረም ላይ የሚጽፈዉን ሳይ ኣነባለሁ።

እኔ መጽሓፍ ቅዱስን በጥልቀት ኣዉቃለሁ ማለት የምችል ሰዉ ኣይዴለሁም። እሱ በደንብ ያላመጠዉ ይመስላኛል።

እዚህ ፎረም ላይ ቅናት የሚለዉን ቃል ብዙ ግዜ ጽፎ ሲከራከር ኣንብቤኣለሁ። ለእኔ የዚህ ቃል ፅንሰሀሳብ በጣም ሩቅ ነዉ። ለእኔ በጣም ቅርብ የሆነዉ ነምን ኡፍ ደንደኤ ነመ ደንደኤ የሚለዉ ኣስተሳሰብ ነዉ። ራሱን የቻለ ሰዉ ሰዉን ቻለ እንደማለት ነዉ።

ስለዚህ የዚህ አይነት የአስተሳሰብ ልዩነት ምንጭ ምንድነዉ ብዬ ለረጅም ግዜ እራሴን ጠይቄኣለሁ።

የእኔ አስተሳሰብ የተለየ ነዉ እንዳይባል ለምሳሌ ያህል ከፕሬዝዳንቱ በላይ በፍጥነት ያረጀ የሚመስለዉ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ቲቪ ላይ ኣንድ ግዜ ስለ ፅንሰሀሳቡ ተመሳሳይ አመለካከት እንዳለዉ ሰምቼ ደንቆኛል። ጥልቅ ዕዉቀት እና ኣስፈላጊ የስራ ልምድ በሌለዉ መታዘዝ ያስረጃል። ሙሉ በሙሉ ባላስታዉስም የተናገረዉ አስተሳሰቡ ስለ ቅናት ሳይሆን ጎረቤት ስያድግ ሰፈር ኣብሮ ይበለጽጋል ኣይነት ነዉ። እሱን ቲቪ ላይ ነዉ ያየሁት። ስለ ፅንሰሀሳቡ ያለን አስተሳሰብ ተመሳሳይነት ገርሞኝ ዝም ኣልኩኝ።

ምናልባትም ኣንዳንድ ሰዎች መጽሓፍ ቅዱስ ፍጹም ቅዱስ ነዉ ብለዉ ተምረዉ የምያስተምሩ ከሆነ እንደ ነዉር እና ሰፉ ያሉ ጥልቅ የባህል ህሴቶችን የት እናድርጋቸዉ?

መጽሓፍ ቅዱስ ምናልባትም የተፈጥሮ ሃብት ያነሰበት አከባቢ ሳይሆን የተትረፈረፈበት አከባቢዎች፣ ለምሳሌ ለሚቷ ኮንጎ ወይም መንገደኛ ዉሃ ጠማኝ ሲል ወተት ይሰጥበት የነበረ ባሌ፣ ተፅፎ የነበረ ቢሆን መጽሓፍ ቅዱስ ያዉ ይሆን ነበር ወይስ ለየት ይል ነበር። ለምሳሌ ስለቅናት ተመሳሳይ አስተሳሰብ ተፅፎ ማስተማር ይጀመር ነበር?

ስለዚህ የኢትዮጵያ የብርሃን ዘመን የጀመረዉ መቼ ነዉ?
Last edited by Naga Tuma on 22 Jul 2023, 00:19, edited 1 time in total.

Abere
Senior Member
Posts: 15409
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ከነዉር ባህል እና ከክርስትና ሃይማኖት የቱ ይቀድማል?

Post by Abere » 21 Jul 2023, 17:54

መልካም ማህበራዊ የመስተጋብር ልማድ እና ወግ ጥሰቶችን ወይም አፈንጋጭ ድርጊቶችን በተለያየ ደረጃ መመዘን ያስፈልጋል።

ነውር፤ሃጥያት፤ወንጀል በማለት ጥንካሪያቸውን (የጎጅ እና የነቀፌታ ምልሾችን መመለከት)።
ደግሞ ክርስቲያን ያልሆነ ማህበርሰብ ሁሉ ነውር፤ ወንጅል ፤ ሃጥያትም የሚለካበት መንገድ አለው።

በአንድ ባህል ውስጥ በአብዛኛው ህዝብ የሚጠላውን ነገር የሚያደርግ ነውር ፈጸመ ይባላል፤ ጠንከር ያለ ከሆነም ወንጀል ይሆናል።

ሰው በእግዚአብሄር አምሳያ የተፈጠረ ነው። መጥፎ እና በጎ ለይቶ የሚያውቅበት ህሌና ሰጠው - ለሌሎች ያልሰውጠ ነው። አዳም እና ሄዋን የመጀመሪያውን ነውር ብቻ ሳይሆን ትዕዛዝ ጣሱ ከዚያም ለቅጣታቸው ከገነት ተባረሩ። ከገነት ስደት በኋ የሰው ልጅ ሁሉ በምን ላይ እንደ ተሰማራ ከትውልድ ትውልድ እያየው ነው። ህግ ካለ ወንጀል አለ። ባህል ህግጋቶች አሉት። መለኮታዊ ህግ መጠበቅ ልስጋ ለባሽ እጅግ ከባድ ነው - ግን ክርስቶስን መከተል ያድናል።ቁም ነገሩ አገራችን የሃይማኖት ተቋምን ከጥቃት እንደት እንከላከል? መንግስት እራሱ እያጠቃት ይገኛል። ከብርሃን ወደ ጨለማ እየመራት ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ከነዉር ባህል እና ከክርስትና ሃይማኖት የቱ ይቀድማል?

Post by Horus » 21 Jul 2023, 22:39

ይህ ሲጀመር የተሳሳተ ጥያቄ ነው? ናጋ ቱማ እንደ ሁልግዜው ጥልቅ ሃሳብ ያቀረበ እየመሰለው ጭለማ ውስጥ ለማየት ይሞክራል ። አንደኛ ክርስትና ምን እንደ ሆነ መጀምሪያ ማወቅ አለብሕ ሁለተኛ ነውር የሚለው ቃል ምን እንደ ሆነ መግለጽ አለብህ ። ዘመነ ብርሃን ማለት እራሱ ምን እንደ ሆነ በውል አልገባውም ። ነውር የሚለው ቃል በጣም ተራ የአንድ ባህል ስነ ምግባር ነው።

በከፍተኛ ደርጃ ያሉት የሰው ልጅ መገዣ ስርዓታትና ሕግጋት ከክርስትና ብዙ ብዙ ሺ ዘመን ቀድመው ነበሩ ማለትም የሰው ልጅ በአንድ ፈጣሪ (ያ ፈጣሪ መንፈስም ሆነ ፀኃይ) ከማመኑ በፊት ። ትልቁ እድገትና ልዩነት ማህበራዊ ሕግጋትና ስነ ምግባራት ምንጭ ከምድራዊ ገዦች ሳይሆን የሚመነጨው ከመለኮታዊ፣ ከሰው በላይ ከሆነ ፈጣሪ ነው የሚለው ነው ።

ኢትዮጵያዊያን በሕገ ኦሪትና ሕገ ልቡና ሲያምኑ እና በሕገ ኦሪት ዚገዙ ብዙ ሺ ዘመናት ሆነዋል ። ዘመነ ብርሃና ክርስትናን ማያያዝ ድንቁርና ነው ። ኦሪት ማለት እራሱ ብርሃን ማለት ነው ። ቃል ማለት እራሱ ብርሃን ማለት ነው ። ሁለቱም በአንድ ፈጣሪ ማመን ከተጀመረ በኋላ የኖሩ ናቸው። ኢትዮጵያዊያን ከክርስትና በፊት በብርሃናን ሕገ ኦሪት ያማኑ ሕዝቦች ናቸው ።

ዛሬ ከክርስትና በኋላ በህገ ኦሪትም በህገ ወንጌልም ያምናሉ ።

ነወር ከህገ ኦሪትና ሕገ ወንጌል አንጻር እጅግ እግጅ ኢምንት የሆነ ስነ ምግባር ነው ። ሌላው ቀርቶ ሕገ ሙሴን እንኳን አያክልም ። ዛሬ ላይ የህጎች ሁሉ ምንጭ መለኮታዊ ግንዛቤ ነው ። ነገስታት ሕግ የማውጣት መብትና ኃይል የሚሰጣቸው ከፈጣሪ ነው ። ሰዎች ዜጋዎች ሕገ መንግስት የማውጣት መብትና ኃይል የሚሰጣቸው በአምሳሉ ከፈጠራቸ ፈጣሪ ወይም እግዚአብሄር ነው ።

ይህን እጅግ ትልቅና የእውቀት መጀምሪያ ምን እንደ ሆነ የማያውቁ እረኞች ናቸው ከኢትዮጵያ ክርስትና እምነት ጋር በመጋጋጥ አላዋቂነቻውን እያጋለጡ ያሉት ።

ከዚያ በተረፈ በሰለጠኑ እና ስብዕና ኖርም በሆነባቸው ሕዝቦች መሃል የኤቲክስ ወይም የሰነ ምግባር ፍልስፍና ወይም ሞራል ፊሎሶፊ የሚባል እጅግ ግዙፍ እውቀት ስላላቸው እነሱ ዛሬ መጽሃፍ ቅዱስ ወይም ቁርዓን በመጥቀስ አይደለም የሰዎችን ባህሪ የሚዳኙት ። ነገር ግን የአለም ሕግጋት ሁሉ ሄዶ ሄዶ ከዲቫይን ሕግጋት ወይም መርሆች እንደ ሚመነጭ ያምናሉ ። ሆኖም ዲቫይን እና ሴኩላር ሕግጋትን ይለያሉ። ማለትም መንግስትን ቤተ እምነት ስለተለዩ!

የኢትዮጵያ ጎሳ ደናቁርት እረኞች ለዚህ የበቁ አይደሉም! የትግሬና ወረሞ ደንቆሮ እረኞች የአማራን ሕዝብ ስለጠሉ ብቻ የኦርቶዶክስ ሃይማኖንትን በፖለቲካ አሸማቀው የሚያጠፉት ይመስላቸዋል ። የነሱ ሞራል ዝቅጠትና መንገድ አልባነት፣ የመንፈስና የሳይኮሎጂ ቀውስ ይህን መሰረታዊ የዘመናት ዊዝደም መማር ስለማይችሉ ነው ።

ሰው በአንድ ፈጣሪ አምሳል የተፈጥረ ስለሆነ ክቡርና የማይደፈር ፍጡር ነው የሚለው የስልጣኔዎች ሁሉ መቆሚያ ምሰሶና በአረመኔዎና በስልጡኖች መሃል ያለውን ልዩነት መግለጫ ነው! !!

Naga Tuma
Member+
Posts: 7367
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ከነዉር ባህል እና ከክርስትና ሃይማኖት የቱ ይቀድማል?

Post by Naga Tuma » 22 Jul 2023, 04:57

Horus wrote:
21 Jul 2023, 22:39

ለጠየኩኝ አጭር ጥያቄ በቂ መልሶች እነዚህ ናቸዉ።

1. “በከፍተኛ ደርጃ ያሉት የሰው ልጅ መገዣ ስርዓታትና ሕግጋት ከክርስትና ብዙ ብዙ ሺ ዘመን ቀድመው ነበሩ”

2. “ኢትዮጵያዊያን በሕገ ኦሪትና ሕገ ልቡና ሲያምኑ እና በሕገ ኦሪት ዚገዙ ብዙ ሺ ዘመናት ሆነዋል ።”

ቀጥሎ መምጣት ያለበት ይህን በትክክል በሰፊዉ ማስተማር ነዉ።

ምናልባትም እያሱስ እና ነብዩ መሓመድ የመሰከሩት ይሀን ይመለከት ይሆናል።

በተረፈ ይህን ሌክቸርህን የፈልክበት ወይም የለመድክበት መዉሰድ ትችላለህ። ኣወኩ ኣወኩ፣ ሁሉንም ኣዉቃለሁ ማለትህን እዚህ ፎረም ላይ የምትጽፋቸዉን ማንበብ ስጀምር ነዉ ያስተዋልኩኝ። እዛዉ እምቦጭ እምቦጭ እንጂ ፈቀቅ የምትል ኣይመስልም። ፈቀቅ ማለት ብትችል ምኞቴ ቢሆንም።

የኢትቶጵያ እረኛ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከዚህ ዘመን ያልተቋረጠ የእዉቀት መዝገብ ሆኖ በኣንተ ሁሉን ኣወኩ ባይነት የማይነቀፍ ሊሆን ይችላል።

ኢትዮጵያዊያን በኦሪት ሕግ ለብዙ ሺህ ዐመታት ስያምኑ ኖረዉ ነዉ ከወጣትነት እድሜህ ጀምረህ ኣዉቀዋለሁ ያልከዉ የማሩ ልጅ በላቲኑ ካቶሊክ ልጅ የተማረከዉ። ኣሁን የኢትዮጵያ ተዋህዶ ዋና ተሟጋች ለማለት ትዳዳለህ። እስቲ ኣዉቃለሁ ከማልት ጋር ማፈርንም ተማር።

Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ከነዉር ባህል እና ከክርስትና ሃይማኖት የቱ ይቀድማል?

Post by Horus » 22 Jul 2023, 13:30

ነጊሻ ምነው ስንተዋወቅ?! መጀምሪያ ቁላ መስለብ የአረመኔ አይደለም ሃይማኖት አልባ እምነት አልባ ካልቸር፣ አይደለም ነውር ታሪካዊ ወንጀል እንደ ሆነ አንድ ቀን እንኳ ስትናገር እንስማ! ሲቀጥል ዛሬ በ21 ዘመነ ስልጣኔ ሰውን አግቶ መዝረፍ ገድሎ መስቀል የአረመኔነ ጥግ መሆኑን ኮንነህ ስትትናገር አንድ ቀን እንስማ! ከዚያ ባለፈ ስምክን በለመለዋወጥ ሰው መሳይ በሽንጎ እዚህ አይሰራም! የሚሉሽ ባልሰማሽ ገበያ ባለወጣሽ ይላሉ እናትቻችን !!!

Naga Tuma
Member+
Posts: 7367
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ከነዉር ባህል እና ከክርስትና ሃይማኖት የቱ ይቀድማል?

Post by Naga Tuma » 22 Jul 2023, 15:31

Horus wrote:
22 Jul 2023, 13:30
ነጊሻ ምነው ስንተዋወቅ?! መጀምሪያ ቁላ መስለብ የአረመኔ አይደለም ሃይማኖት አልባ እምነት አልባ ካልቸር፣ አይደለም ነውር ታሪካዊ ወንጀል እንደ ሆነ አንድ ቀን እንኳ ስትናገር እንስማ! ሲቀጥል ዛሬ በ21 ዘመነ ስልጣኔ ሰውን አግቶ መዝረፍ ገድሎ መስቀል የአረመኔነ ጥግ መሆኑን ኮንነህ ስትትናገር አንድ ቀን እንስማ! ከዚያ ባለፈ ስምክን በለመለዋወጥ ሰው መሳይ በሽንጎ እዚህ አይሰራም! የሚሉሽ ባልሰማሽ ገበያ ባለወጣሽ ይላሉ እናትቻችን !!!
ጊዜ እንደምያንህ እገምታለሁ። ለጥያቄህ መልስ ከኣሁን በፊት የጻፍኩትን ፈልጌ እለጥፍልሃለሁ። ስለዚህ ዝም ብለህ ኣትዘባቅ።

ለኣሁን ማለት የፈለኩኝ ይሄ ነዉ፥

የኢትዮጵያ እረኛ ኣዲስ ትምህርት ቤት ደርሶ ግራ የተጋባ ሳይሆን ኖሩ፣ ንበሩን ጠንቅቆ የምያዉቅ ጨዋ ነዉ። ካልተሳሳትኩ የኢትዮጵያ እረኞች ብዙ የኢትዮጵያ ኣርበኞችን ኣፍርተዋል።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7367
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ከነዉር ባህል እና ከክርስትና ሃይማኖት የቱ ይቀድማል?

Post by Naga Tuma » 23 Jul 2023, 04:57

ሆረስ፣ ጽፌ ነበር ያልኩህ ይሀዉ፥ What happened last year, according to Ethiopian calendar, in the land wherein no one is wronged?

ለተጨማሪ ግዜ እንዳገኘሁ ጥያቄህን እመለስበታለሁ።

Post Reply