Page 1 of 1
Eid Mubarak
Posted: 20 Apr 2023, 14:16
by Somaliman
Re: Eid Mubarak
Posted: 20 Apr 2023, 15:33
by kerenite
Eid mubarak to you too brother somaliman, to your family and to all muslims worldwide.
Kullu Am weantum bikheir. Or kullu sena weantum tayiboon as the Egyptians say.
Re: Eid Mubarak
Posted: 21 Apr 2023, 14:32
by Abe Abraham
-
Re: Eid Mubarak
Posted: 21 Apr 2023, 14:51
by Horus
አቤ፣
ኢድ ሙባረክ!
ብሩክ ማዕድ!
በነገራችን ላይ 'ኢድ' የሚለው ቃል በግዕዝ፣ በሂታይት፣ በሴም፣ አረብኛ፣ በሳንስክሪት፣ በላቲን፣ በግሪክ፣ በእንግሊዝኛ 'ኢት' ፣ ወዘተ ... ሁሉም 'መብላት' 'ምግብ' ማለት ነው ። ማዕድ በማዕድ ቤት ይቀመጣል እንዲሉ !!!!
Re: Eid Mubarak
Posted: 21 Apr 2023, 17:44
by Zack
Eid Mubarak to all the Muslims in here in all four counties of the horn Ethiopians Eritreans Djiboutians Somalis
Have a great eid all of u and may we reach next year ramadan inshalla
Dr Zackovich
Re: Eid Mubarak
Posted: 21 Apr 2023, 17:46
by Naga Tuma
Horus wrote: ↑21 Apr 2023, 14:51
አቤ፣
ኢድ ሙባረክ!
ብሩክ ማዕድ!
በነገራችን ላይ 'ኢድ' የሚለው ቃል በግዕዝ፣ በሂታይት፣ በሴም፣ አረብኛ፣ በሳንስክሪት፣ በላቲን፣ በግሪክ፣ በእንግሊዝኛ 'ኢት' ፣ ወዘተ ... ሁሉም 'መብላት' 'ምግብ' ማለት ነው ። ማዕድ በማዕድ ቤት ይቀመጣል እንዲሉ !!!!
ሆረስ፥
ሁለት ቃላትን ልጨምር፣ ከቦረና ቋንቋ። የአፋን ኦሮሞ መሠረት ነዉ።
1) ማዲ፣ ማዕድ ማለት ነዉ።
2) ቡዴን (ቡዴነ፣) ምግብ ማለት ነዉ። ከእንግሊዘኛዉ ፉድ ጋር የሚመሳሰል።
ከዓመታት በፊት ያየሁኝ የፉድ ኦሪጅን ይሀዉ፥ Food, fode (Middle English,) fōda (Old English,) fēdan (also Old English,) fōdjan (Gothic)
የእኔ ግምት ስህተት ይሁን ኣይሁን ኣላዉቅም። ቋንቋዎቹን ተናጋሪ እንጂ ስለ ቋንቋዎች ኣልተማርኩም። ስህተት መሆኑን ወይም ኣለመሆኑን ኣንተ እና አቤ አብረሃም ማረጋገጥ ትችላላችሁ።
ኢድ ሙባረክ
ብሩክ ማዕድ
ማዲን ሃ በረከቱ
Re: Eid Mubarak
Posted: 21 Apr 2023, 18:10
by Abere
Nag Tuma,
Do not be tricked by accidental similarity of words. For instance in Bantu, Swahili, priest means kuhani. If you look at the Bantu word "kuhani" it sounds like the Hebrew (Kahn) or Amharic/Geez name of ካህን. But this happens by accident.
Re: Eid Mubarak
Posted: 21 Apr 2023, 19:33
by Abe Abraham
Horus wrote: ↑21 Apr 2023, 14:51
አቤ፣
ኢድ ሙባረክ!
ብሩክ ማዕድ!
በነገራችን ላይ 'ኢድ' የሚለው ቃል በግዕዝ፣ በሂታይት፣ በሴም፣ አረብኛ፣ በሳንስክሪት፣ በላቲን፣ በግሪክ፣ በእንግሊዝኛ 'ኢት' ፣ ወዘተ ... ሁሉም 'መብላት' 'ምግብ' ማለት ነው ። ማዕድ በማዕድ ቤት ይቀመጣል እንዲሉ !!!!
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
وكل عام وأنتم بخير
قالوا بأن أصل عيد : عِوْد ، وجمعه : أعياد ، وإنما جمع بالياء مع أن الجمع يرد الأشياء إلىٰ أصولها ؛ للزومها في الواحد .
فما مرادهم بـ( لزومها في الواحد ) ؟
ካንተ ያቀረብከውን ሃሳብ ተነስቼ ስፈልግና ሳነብ የላይኛውን የኣረብኛ ጽሁፍ ኣገኘሁ ። ጽሁፍ እንዲህ ይላል ፥
1_"ዒይድ" የሚለውን ቃል መሰረቱ " ዒውድ " ሆኖ ሲባዛ "ኣዕያድ" የሚል ገጽ ይይዛል ።
2_እንደሚባለው በኣረብኛ ቃላቶች የፕሉራል ቅርጽ ሲይዙ - በቫወል ኣመለካከት - ወደ ዋነኛው መስረታቸው ይመለሳሉ ።
3_ቫወላዊ መሰረቱ " ወ " ሆኖ በሲንግዩላር " የ " ይዞ የቀረበው ሲባዛ " ወ " ይዞ ይመለስና የቃሉ መስረት " ወ " መሆኑን ማረጋገጫ ይዞልህ ይቀርባል ።
4_የጠያቂው ጥያቄ ፥ ለምን " ዒይድ " /ሲንግዩላር ሲባዛ " ኣዕያድ " ሆነ ?
ለኛ ኣስፈላጊው የጥያቄው መልስ ሳይሆን የዒይድን መሰረት ዒውድ መሆኑን የሚያመለክት ግንዛቤ ነው ። ለምን ? "ወ" ን ያቀፈ " ዒውድ " ወደ " ዓውደ-ዓመት " ስለሚወስደን !!!!!
በኣረብኛ የመኣዲ/በትግርኛ ማእድ/በግእዝ ወንድም የሆነ " ማኢዳ " የሚባል ቃል ኣለ ።
ሰሰናዩ/ኬር!!
-
ዓሳክ ምን ዓዋዳ ( ለብዙ ዓሳኩም ምን ዓዋዳ) / የያንዳንድ ጋልፍ ኣረብ ኣገሮች የዒይድ ሰላምታ ...እንደ እንኳን ...ማለት ነው ።
Re: Eid Mubarak
Posted: 21 Apr 2023, 21:04
by Horus
Naga Tuma,
እኔም የለጠፍኩትን ለጥፌ ስራ ከሄድኩ በኋላ ትዝ አለኝ የቡዴና (ሙዴና ይሉታል በሸዋ) የሚለው ወረሞፋ በትክክል ማዕድ ከሚለው የተቀዳ ነው ። ሌሎችም ብዙ የግዕዝ ቃላት ወረሞፋ ውስጥ አሉ ። ለምሳሌ እራት ማለት ምን ይባላል ብዬ ጠይቄ ያገኘሁት መልስ ኧርባታ/ኢርባታ የሚል ነው ። ይህ ቃል ግዕዝ ነው ። በአማርኛ ሳጥረው እራት ይሉታል እንጂ ኧርባት ነው ቃሉ። ኧርብ ማለት የጸሃይ መጥለቅ፣ ሰን ሴት ማለት ነው ። ከሰን ሴት በኋላ የሚበላ ማለት ነው ። ምዕራብ ማለት ነው ። ምራብ ወይም ምዕራብ ማለት ጸሃይ የሚጠልቅበት ቦታ ማለት ነው ።
በተማሳሳይ አቤ እንዳለው በስዋሂሊ ውስጥ ያለው ካህን (ኮሀን) የተውሶ ነው ።እስዋሂሊ ውስጥ ብዙ አረብኛ አለ፣ ከአረብ የባሪያ ንግድ ጋር በተያያዘ ። ካህን/ኮሀን ማለት እጅግ ጥንታዊና ታላቁ የግብጽ ንጉስ አከን አተን የተጠራበት ቃል ነው ። አከን አተን ማለት የአተን (የጸሃይ አምላክ) አገልጋይ፣ የአተን ካህን ማለት ነው ። ካህን የፈጣሪ አገልጋይ ማለት ።
ስለ አንድ ቃል ስረ አመጣጥ ታሪክ ስናወራ የውጭ ኤክስተርናል ኤቪደንስ ማቅረብ አለብን ። ለምሳሌ ካህን ቱባ ግዕዝ ለሆኑ ቅኔ፣ ቀኖና፣ ቂና፣ መቀኒያ፣ ክንውን እያልን በሰፌው በዚያ ቋንቋና ካልቸር ውስጥ መኖሩን ማሳየት አለብን ። ቅኔ መቀናት፣ ማድረግ፣ መፍጠር ነው። ቀኖና ድርጊት ትግበራ ማለት ነው። ጉራጌ ምን ትቂናው ካለ ምን ታደርጋለን፣ ምን ትከውናለህ ማለት ነው ። ይህ ሁሉ አከን፣ ካህን፣ ኮሀን የሚለው ጽንሰ ቃል ነው ።
አቤ፣
በትክክል ከዚህ በፊት እንዳልነው በ፣ ወ፣ የ፣ መ ሺፍት የሚያርጉ ድምጾች ናቸው ። እንዲሁም አንድ ቃል ስናበዛ፣ የነገር ስም ስናደርግ ፣ ለማተንከር ቅጽል ስንፈጥር ብዙ ግዜ ቃሉን እንደግመዋለን (ከፍከፍ፣ ሞቅሞቅ) ወይም ከፊቱ (ፕሪፊክስ) ወይም ከኋላው (ሰፊክስ) ወይም እንዳልከው መሃል ላይ ሌላ ድምጽ እናስገባለን ። ታስታውስ ከሆነ 'ነ' እንዴት በዘፈቀደ ለማንበቢያ ምቹነት እንደ ምንከት አይናል ። ለምሳሌ ጉራጌ ኬር የሚለው በአረብኛ ኬይር ፣ በወሎ ሄይር ነው ። ሃል የሚለው ሃይል ነው የምንለው !!
አውድ የሚለው ቃል ላይ ምርምር ማድረግ አለብኝ ። እኔ ከዚህ ቀደም ባጠናሁን አውድ ማለት ነገር፣ መንገር፣ የምስራች ማለት ። እናም አውደ አመት (የአመት በኣል) የአመት ምግብ ፌስታ (ኢድ) ወይስ የአመት ምስራች የዜና ፌስታ? እርግጠኛ አይደለሁም ።
ይህን የምልህ ለምንድን መሰለህ? ለምሳሌ ፋሲካ የሚለው ቃል ለብዙ ሰው መፈሰክ፣ ከጾም በኋላ መብላት የመስለዋል ። ሌላው ቀርቶ በጉራጌኛ ፊቸ ይባላል ፣ መስታት ማለት ነው ። ግን የቃሉ ግንድ ፋሽካ ሞት፣ ሃዘን ፣ ለቅሶ ማለት ነው ። የክርስቶስ ሞት የሚያሳይ ነው ። የዚህ ጥንታዊ ቃል ትክክለኛ ትርጉሙ ዛሬ ብሸ በምንለው ቃልና ባህል ውስጥ ያለው ነው ። ብሸ፣ ለቅሶ፣ ሃዘን ማለት ነው ። ዛሬ ሙሾ የምንለው ነው ።
ስለሆነም የአውደ አመት ትርጉም አንዱ እኛ በታሪክ አውድ ወዘተ ብምንለው አለ ። በበአልነት ያለው ትርጉም ላይ ማጥናት አለብኝ!
ኬር
ኬይር
ብሩክ ማዕድ!
Re: Eid Mubarak
Posted: 26 Apr 2023, 17:35
by Naga Tuma
Horus wrote: ↑21 Apr 2023, 21:04
Naga Tuma,
እኔም የለጠፍኩትን ለጥፌ ስራ ከሄድኩ በኋላ ትዝ አለኝ የቡዴና (ሙዴና ይሉታል በሸዋ) የሚለው ወረሞፋ በትክክል ማዕድ ከሚለው የተቀዳ ነው ። ሌሎችም ብዙ የግዕዝ ቃላት ወረሞፋ ውስጥ አሉ ። ለምሳሌ እራት ማለት ምን ይባላል ብዬ ጠይቄ ያገኘሁት መልስ ኧርባታ/ኢርባታ የሚል ነው ። ይህ ቃል ግዕዝ ነው ። በአማርኛ ሳጥረው እራት ይሉታል እንጂ ኧርባት ነው ቃሉ። ኧርብ ማለት የጸሃይ መጥለቅ፣ ሰን ሴት ማለት ነው ። ከሰን ሴት በኋላ የሚበላ ማለት ነው ። ምዕራብ ማለት ነው ። ምራብ ወይም ምዕራብ ማለት ጸሃይ የሚጠልቅበት ቦታ ማለት ነው ።
ሆረስ፥
ወደዚህ ርዕስ ኣሁን መመለሴ ነዉ። የቡዴናን እና ማዕድን መመሳሰል የገመትኩትን ነዉ ያረጋገጥክልኝ። የእኔ ጥያቄ መመሳሰላቸዉ ቢወራረሱ ነዉ ወይ የሚል ነበር። እንዴት የተወራረሱ ቃላት ሊሆኑ ቻሉ የሚለዉ ክርክር ዉስጥ ኣልገባም። ኣንድ ቀን የግዕዝ ዲክሽነሪን እንደማገኝ ተስፋ ኣለኝ።
ኬር።
አበረ፥
እንደ ይሁኔ በላይ አከም ነጉማ እያልክ ነዉ፣ ሰከን በሉን ማስተማር ሳይጀምር በፊት፣ ወይስ እደሆረስ ድሮ አባ እና ኣዴ ሰፈራችን ኣልተሰሙም ነበር እያልክ ነዉ ብዬ ልጠይቅህ ኣሰብኩ። የሆረስ መልስ ጥያቄዬን ኣስረሳኝ።
ጤና ይስጥልኝ።