አቢይ አህመድ የመንደር ጎረምሳ፡ መሳይ መኮንን ይናገራል!! እውነት እውነቱን !!!
Posted: 17 Apr 2023, 14:12
ባለፈው ሳምንት የሳዑዲ አረቢያው ከፍተኛ ባለስልጣን የመጡትም አብይ አህመድ ከኤሜራትስ ጎን ተሰልፎ ሱዳን ላይ ያነሳውን ሰይፍ ወደ አፎቱ እንዲያስገባ ለመምከርና ለማስጠንቀቅ ነው። የኤርዶጋንም አመጣጥ ለዚሁ ነው። ሌላ ነገር የለም። በአብይ አህመድ ናፍቆት እህል አልበላ ብሏቸው ስለተቸገሩ የመጡ አስመስለው ሊነግሩን የሚቃጣቸው የብልጽግና ዲጂታል ሰራዊት አባላት እንዳሉ እየታዘብኩ ነው። ከሁሉም የአብኑ ጣሂር መሀመድ ''የኢትዮጵያ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የተመሰከረበት ጉብኝት'' የሚል ልጥፍ ይዞ ሲመጣ ገርሞኝ የትላንቱን ጣሂር ማሰብ ጀመርኩ። ሰው በዚህ ደረጃ ቂልና ጅል ሲሆን ያስደምማል።