Page 1 of 1

"የኢትዮጵያ መከላከያ የሚባል ነገር የለም፣ አሁን ያለው የኢትትዮጵያ መከላከያ ሳይሆን የኦሮሞ/ኦነግ መከላከያ ነው!" ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን!!

Posted: 12 Apr 2023, 04:21
by Wedi
"የኢትዮጵያ መከላከያ የሚባል ነገር የለም፣ አሁን ያለው የኢትትዮጵያ መከላከያ ሳይሆን የኦሮሞ/ኦነግ መከላከያ ነው!" ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን!!

Mesay Mekonnen
·
ጠ/ሚሩ አሁንም የማይነካ ነገር ነክተዋል። ባለፈው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጦርነት ሲያውጁ እንደለመዱት አጭበርብረውና አሸማቀው በአሸናፊነት የሚያጠናቅቁት መስሎአቸው ነበር። የማይነካ ነገር ነክተው ኋላ ላይ ራሳቸው የወረወሩት ሰይፍ ተመልሶ የአይን ብሌናቸው ላይ ሊሰካ ሲል ተንደፋድፈው ነገሩን አበረዱት። አሁንም የማይነካ ነገር ነክተዋል። መከላከያ ሰራዊቱን የግላቸው ኪስ ከተዉት አንድ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል። እዚህ ላይ መከላከያ ሰራዊቱን በተመለከተ አንዳንድ ወዳጆች የያዙት አቋም ማስመሰልና መውሸልሸል ያጠላበት አጉል አርበኛ ሆኖ ለመታየት የሚደረግ ትርጉም የሌለው፡ ሀገርን የማይጠቅም፡ የአንድ አምባገነንና ዘረኛ ቡድንን የጥፋት መንገድ አጅቦ ከመጓዝ ያለፈ ፋይዳ የሌለው መሆኑን በግልጽ መናገር ያስፈልጋል።

መከላከያ ሰራዊቱን ከፓርቲ ወገንተኝነት አላቆ ለህዝብና ለህገመንግስቱ(?) ብቻ ታማኝ ሆኖ እንዲደራጅ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው በሚል አሸሼ ገዳሜው ቀልጦ እንደነበረ አስታውሳለሁ። ቀዩ ደብተር ተቀዶ በአረንጓዴው ተተክቷል አይነት ከበሮም ሲደለቅ ነበረ። እኔም በወቅቱ ኢትዮጵያን የሚመስል የመከላከያ ሰራዊት እየተገነባ ነው በሚል በተስፋ የተሞሉ መልዕክቶችን ለህዝብ ሳሰራጭ ቆይቼአለሁ። አንድ ሀገር ማንን ትመስላለች ከተባለ መከላከያ ሰራዊቷን ነው የሚለውን ተስፈኛ ብሂል ወደውስጤ ከትቼው እየተገነባ ያለው መከላከያ ሰራዊት የምር ኢትዮጵያዊ ከሆነ ኢትዮጵያ ጠነከረች፡ ተከበረች፡ ብዬ ጮቤ የምረግጥበትን ቀን ስናፍቅ እንደነበረ አስታውሳለሁ። የነበረኝ ተስፋ እንጂ የተጨበጠ ነገር አይደለም። አሁን በማየው ሁኔታ ግን ተስፋውም እንደጉም በኖ ከውስጤ ጠፍቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፓርቲያቸውም በታች አውርደውት የግላቸው ዘብ እንዲሆን አድርገውታል። እነጄነራል አበባው ብቅ እያሉ ''ኢትዮጵያዊ'' ሰራዊት ነው የሚል ቅብ እውነት ለመንገር የሚያደርጉትና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ለከት ያጣ ቅዠት ሀገራዊ ራዕይ አስመስለው ሊያስረዱ የሚሞክሯት ነገር በእጅጉን ታሳፍራለች።

አንድ ግልጽ የሆነ ሀቅ አለ። መከላከያ ሰራዊቱ ትዕዛዝ የሚቀበለው ከፖለቲካው አመራር ነው። አለቀ። አድርግ ሲሉት የሚያደርግ፥ ተነስ ተቀመጥ ሲሉትም የተባለውን ከማድረግ የሚመለስ አይደለም። አሁን ባለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ስልጣን የያዘው ቡድን እልም ያለ ዘረኛና ጎሰኛ ነው። የለውጡ አምስተኛ ዓመት ዝክር በአንድ ክልል ብቻ እንዲከበር የተፈለገበት ምክንያት ከምንጊዜው በላይ አራት ኪሎ የተቀመጠው አገዛዝ የሀገር ጥብቆውን አውልቆ የጎሳ ከረጢት ውስጥ መግባቱን ዳግም ያረጋገጥንበት አጋጣሚ ነው። እናም መከላከያ ሰራዊቱ ትዕዛዝ የሚቀበለው ከዚህ ጠባብ ጎሰኛ ስርዓት ነው። የሌለውን ከየትም አያመጣም። ጎሰኛና ዘረኛ ስርዓት ባለባት ሀገር ኢትዮጵያዊ መከላከያ ሰራዊት መገንባት ፈጽሞ የሚቻል አይደለም። ጠ/ሚሩ እሳቸውም ጠበው ከረጢት ውስጥ እየገቡ ጄነራሎቻቸውን ሰብስበው እባካችሁን በብሄር ራሳችሁን ለክታችሁ ሰራዊቱንም አታውርዱት ብለው ሲመክሩ ሰምቼ የሰውዬውን ስነልቦናና የአእምሮ ደረጃ አግራሞ እስኪጭርብኝ ታዘብኩት። አንድ ወዳጄ በዓለም ላይ ሁለት ደፋሮችን አውቃለሁ፡ አንዱ አዶልፍ ሂትለር ሲሆን ሁለተኛው ጠ/ሚር አብይ ናቸው ያለኝን ለራሴው አስታወስኩት። ሲበዛ ደፋር ናቸው። አጉል ደፋር።

ለማንኛውም መከላከያ ሰራዊቱ የፖለቲካ አመራሩን ትዕዛዝ እስካስፈጸመና ታማኝነቱን ለዚሁ ዘረኛ ስርዓት አድርጎ እስከተንቀሳቀሰ ድረስ ''የኢትዮጵያዊነት የመጨረሻ ምሽግ ነው'' እያሉ ማላዘን እርባና የለውም። ራስን ከማታለል ያለፈ ለሀገርም ለህዝብም አይጠቅምም። ይህን ስል ኢትዮጵያዊ መከላከያ ሰራዊት ሆኖ እንዲዋቀር የሚለፉ የሚደክሙ የሉም ማለቴ አይደለም። የእነዚያ ሰዎችን ልፋትና ድካም ዋጋ መስጠት አለብኝ። ግን ከላይ የተቀመጠው ዘረኛ የፖለቲካ አመራር የእነዚህን ሰዎች ልፋትና ድካም ከንቱ አድርጎታል። እናም መከላከያ ሰራዊቱን እንዳትነኩት አብይን ግን መቃወም ትችላላችሁ የሚሉ ቅንጦተኛ ሰባኪያንን የምሰማበት ጆሮዬ ግንዱ ዝሏል። ሁሉ ነገር በልኩ ካልተነገረ አያዋጣም። ትርፉ እንደሀገር ኪሳራና አውዳሚ ነው።

ወደ ተነሳሁበት ነጥብ ልመለስና ጠ/ሚሩ የማይነካ ነገር ነክተዋል። ጂኒውን ከጠርሙሱ አውጥተው ዳግም በትነውታል። ያ ጂኒ አማራ ክልልን እያመሰ ነው። እሳቸውም ሆነ ሌላው ወገን አሸናፊ ሆኖ የማይወጣበትን ደም አፋሳሽ ግጭት ፊሻካውን ነፍተው አስጀምረውታል። በሴኩሪቲ መስታወት ውስጥ ስለተሸሸጉና መከላከያ ሰራዊቱን በ'መሳሪያ' ስለገነቡት የፈለጉትን የሚያደርጉ መስሎአቸው ሊሆን ይችላል። እንደሳቸው በሾርት ሜሞሪ የተጠቃ በእርግጥ ማንም ያለ አይመስልም። ራሳቸው እየነገሩን ራሳቸው የተጠለፉበት ነው። ከህወሀት መማር አልቻሉም። ከደርግ መንግስት ግዙፍ ሰራዊት መጨረሻ የቀሰሙት ልምድ የለም። የሊቢያውን መሪ አስከፊ ፍጻሜ ዘንግተውታል። በሀሳብ የበላይነት ሀገር መምራት ሲሳናቸው በጡንቻ ስልጣኔን አራዝማለሁ ብለው ጦር ሰብቀዋል። እንግዲህ መጨረሻውን አብረን የምናየው ይሆናል። ከወዲሁ ጂኒውን ወደ ጠርሙሱ መልሰው እንዲያስገቡ ከአንድ ተራ ኢትዮጵይዊ ወንድማቸው ምክሬን ከሰሙኝ ይድረሳቸው። የጀመሩት መንገድ መዳረሻው ጥፋት ብቻ ነው። የማይነካ ነገር አይነካምና እጅዎን ይሰብስቡ።

:!:
Please wait, video is loading...