Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39779
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ወረሚያ፡ ልጓዝ በሞት ጎዳና በወደቀው ወያኔ ፋና!

Post by Horus » 11 Apr 2023, 09:39

ይህቺ ትንቢት አዘል ድምዳሜዬ ሶስት ሰዎች አይወዱትም ፤ የአቢየ ኦነግ የወረሞ ኤሊት፣ ወያኔያዊ የትግሬ ኤሊት እና ሻአቢያዊ የኤርትራ ኤሊት ። እኔ ቃላት በመፍለጥ አንብቢን አላሰለችም ። መልዕክቴ ግልጽ፣ አጭርና ግዙፍ ነው ። ከላይ የጠቀስኳቸው ሶስት የፖለቲካ ኤሊት የገዥ መደቦች ላለፈው 60 አመታት ሶስት ምናባዊ አላማዎችን ለማሳካት እንደ ባከኑ አሉ። እነዚህም አላማዎች የኦሮሙማ ኢምፓየር፣ አባይ ትግሬ/ታላቋ ትግሬ፣ እና ሲንጋፓራዊ ኤርትራ ። ሶስቱም አላማዎች ሊሚገነቡ የታሰቡት ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር አፍርሶ ነበር ።

ይሃው እስከ ዛሬም ኢትዮጵያ አልፈርስም ብላ ነገሮች አንድ በአንድ በተቃራኒው የታሪክ ፋና እየተጓዙ ነው ። አው ኤርትራ ተገንጥላ አገር ሆናለች ። ሕዝቧ ግን ከ30 አመት ጦርነት በኋላ ከንጉሱ ዘመን በወረደ ድህነት ውስጥ መኖር ከጀመረ ሌላ 30 አመት ሆነው ። ኤርትራ ሲንጋፖር አልሆነችም፣ ሕዝቧም በአለም ተበተኑ፣ ብዙ መከራም ቀመሱ፣ የትግሬ ገዚ መደብ ታላቁ የትግሬ ኢምፓየር ለማቆም 17 አመት ተዋግቶ 27 አመት ኢትዮጵያን ከዘረፈ አይደለም ታላቅ ትግሬ እራሱን መመገብ የማይችል ተመጽዏችና የሰዎች መከራ ሲኦል ሆነ ።

ከነዚህ ሁለት ግዙፍ የኤርትራዎችና የትግሬዎች ታሪካዊ ስህተት ያልተማረው (የነሱ ውልድ ስለሆነ) የወረሞ ፖለቲካ ኤሊት (ከኦነግ እስከ አቢያዊ ኦብፓ) ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር ወይም ውጠን አለያም አፍርሰን ያፍሪካ ቀንድ ወረሞ ኢምፓየር እንዘረጋለን የሚል ምናብ አንግቦ በወደቀው የትግሬ ጎዳና እየነጎደ ነው ። ይህ አቢየ ኦነግ የውድመትና የሞት እብደት ምናልባት ማረም ከማይቻልበት ደረጃ ደርሶ ይሆናል ። ያን የሚያውቁት ራሳቸው እብዶቹ ብቻ ስለሆኑ ።

ነገር ግን ይህ የዛሬ ጉዞአቸው ታሪካዊ አቅጣጫ (ሂስቶሪካል ትራጀክተሪ) ከልቀየረ የሚቀጥለው ውድመት በኢትዮጵያዊያን እና በወረሞ ኤሊቶች መሃል ይሆናል ። ውጤቱም ልክ እንደ ትግሬ የወረሞ ሕዝብ ማህበራዊ ሕይወት መፍረስ፣ ሞት፣ እልቂት፣ ረሃብ ፣ ስደትና የመላ አፍሪካ ቀንድ ይህ ነው የማይባል ቀውስና ፍጻሜ ይሆናል ። ኢትዮጵያ ፈርሳ በልቶ የሚያድር ተገንጣይ የለም ፣ አይኖርም ። ጆር ያለው ይስማ!

የጎንደሬ መፈክር፤ ኢትዮጵያን አፍርሶ የሚገነባ ሬፑብሊክ የለም!

ሆረስ ወልደ ብርሃን


Horus
Senior Member+
Posts: 39779
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ወረሚያ፡ ልጓዝ በሞት ጎዳና በወደቀው ወያኔ ፋና!

Post by Horus » 11 Apr 2023, 10:11

የግዜ ጉዳይ እንጂ መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን መሰል ፋሺዝም ለመበተን መነሳቱ አይጠረጠርም !

Lovetarik
Member
Posts: 357
Joined: 10 Apr 2018, 00:39

Re: ወረሚያ፡ ልጓዝ በሞት ጎዳና በወደቀው ወያኔ ፋና!

Post by Lovetarik » 11 Apr 2023, 10:16

ፍጹም ነው እምነቴ ወደ ውድቀት ነው ህይወቴ
ልጓዝ በውድቀት ጎዳና በሙትቻው ወያኔ ፋና

Kuasmeda
Member+
Posts: 6431
Joined: 26 Mar 2015, 08:47

Re: ወረሚያ፡ ልጓዝ በሞት ጎዳና በወደቀው ወያኔ ፋና!

Post by Kuasmeda » 11 Apr 2023, 10:47

The rotten old man Horus! You will never stop your stinky mouth against the independent sovereign state of Eritrea. You are utterly ignorant of how things are unfolding in Eritrea & the Horn of Africa. Self-reliance is the key to Eritrea’s independence and development. We happily prefer death to grovel. The righteousness and the justness of our position and self-reliance give us strength and courage to stand proudly amongst the countries of the region and the world. Whether we like it or not, SELF RELIANCE is the sole bullet to boot out colonialism in Africa. Africa’s complete freedom won’t be achieved without opting for Self-reliance. We have to get rid of the prejudice that Africa cannot develop without foreign aid. This is only a Western-invented syndrome to justify Western activities in the continent. Africa can be self-reliant. However, the foreign aid cycle and culture of dependency often leave Ethiopia & other African countries more debt-laden, more corruption-prone, and more vulnerable and fragile countries.

Abere
Senior Member
Posts: 14740
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ወረሚያ፡ ልጓዝ በሞት ጎዳና በወደቀው ወያኔ ፋና!

Post by Abere » 11 Apr 2023, 11:06


በላበትን ወጭት ሰባሪ የሚለው ብሂል እንድሁ ዕቃውን ከመስበር ጋር ብቻ የሚቀር ድርጊት አይደለም። ብሂሉ እጅ ይጥልሃል - የማታ የማታ (በመጨረሻ) በችግር እና በርሃብ እግዜር ይቀጥሃል ነው - ያች ያበላች ወጭት በዐይንህ ትዞራለች እንደ ማለት ነው። ይህ ድርጊት በግልጽ በትግሬ ተገንጣይ ወያኔ ደርሷል። ቢያንስ ከ55 አመት በላይ ኢትዮጵያን ሲነክስ፤ሲያደማ ፤ ሲገድል፤ ሲያቃርጥ ቆይቶ በመጨረሻ የሰበሰበው ሃብት እና እኩይ ዝና ዐመድ ሆነ። የደረቅ አጠገብ እርጥቡ ይነዳል ሆነ እና 1 ሚልዮን ትግሬ በትርጉም አልባ ጦርነት አስፈጀ።
አሁን ለ32 አመታት ያልሰራ ሴራ መቸም እንደማይሰራ ሳይንሳዊ ሃቅ ሁኖ በዚህ 5 አመታት ተረጋገጠ። ወያኔ በጠፋበት መንገድ እኔም እጠፋለሁ ያለው ወረሙማ እንድሁ 5 አመት ሙሉ ጊዜውን በከንቱ ሰው በመጨረስ ፈጀው - የመንግስትነት አፍላ ሳይኖረው። ወረሞን 1ኛ ዜጋ አደርጋለሁ ቢሉም የተረበሸት፤ የታወከች፤ የተቸገረች፤ የመንጋ መናኸሪያ እንጅ ሌለ ምንም አላተረፈችም - በርካታ ተበቃዮች ግን በደን አፍርታለች። በወረሙማ ላይም ጸሀይ እየጠለቀች ነው - ከ 60 አመታት ከንቱ ልፋት በኋላ።

Horus
Senior Member+
Posts: 39779
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ወረሚያ፡ ልጓዝ በሞት ጎዳና በወደቀው ወያኔ ፋና!

Post by Horus » 11 Apr 2023, 14:26

አበረ፣
ዝሆን ሲከሳና ሃብታም ሲፈሳ (ሲከስር) አይታወቅም ይባላል። ዛሬ ስዉ ሁሉ አመጽ፣ ችግርና ቀውስ ያለው በትግሬ፣ ባማራና ጉራጌ ብቻ ይመስለዋል ። በተለይ የወረሞ ኤሊቶች! ነገ ላይ የሚፈነዱትን ቅብር ቦምቦችን ትተን የዛሬን ወረሚያ ብንመለከት በምስራቅ የድርቀትና ረሃብ አደጋ ብቻ ሳይሆን የወረሞ እና ሱማሌ አይቀሬ ጦርነት አለ ። ከምራብ አሩሲ እስከ ሲዳማ ድረስ እንዲሁ የተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን የማይቀረው የወረሞና ሲዳማ ጦርነት አለ ። ዛሬ ላይ ሳይቀር የወደመው ወለቃ ብቻ ሳይሆን ከሻንጉሎች እና ከመተከል አማራ የማይቀረው ጦርነት አለ ። በመሃል ኢትዮጵያ ስንቱ የጦርነት ምንጭ ይቆጠራል ። ጎጃም በግድ ህዝብና ምርቱን በአምቦ መስመር ያስገባል (በውድ ካልሆነ በጦር)፣ ሰሜን ሸዋም እንዲሁ፣ ስሊ ስከ ወሎ ። በደቡብ ምራብ ሸዋ ውስጥ ውስጡን የሚፈላው መጓሸም አዲሳባ ይደርሳል ። በስሜት አይኑ ላለታወረ ወረሞ ኤሊት ዛሬ ዛሬ ላይ እራሱ ወረሚያ ቀውስ ውስጥ ነው ። ይህ የታሪክ ቀስት በያዘው ፋና ከቀጠለና የነአቢየ ወነግ ስልቀጣ ራሱን ካልገታ መላ ወረሚያ የጦር ቀጠና እንደ ሚሆን ጥርጥር የለውም። አይን የራሱን ጉድፍ አያይም እንደ ሚባለው አቢይ አህመድ የሌሎች መብት ለመርገጥና ቤታቸውን ለማፍረስ ከመባከኑ ቀድሞ በራሱ ቤት ያለውን ፈንጂ ያምክን እንላለን ።


Post Reply