Page 1 of 1

በአማራ ክልል ህዝባዊ እምቢተኛነት በይፋ ከተጀመረ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን አስቆጠረ!!!!

Posted: 11 Apr 2023, 08:17
by Ejersa

Update from Amhara Region

ሚያዝያ 3 ቀን 2015

ህዝባዊ እምቢተኛነት በይፋ ከተጀመረ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን አስቆጠረ:: ወሎ ኮምቦልቻ ላይ 52 ሰላማዊ ዜጎች በኦሮሙማ ተገድለዋል:: በባህር ዳር ህዝባዊ እንስቃሴው በይፋ ተጀምሯል:: ኦሮሙማ ጎንደር ላይ ሁለት ክፍል ጦር በአየር ለማስገባት አስቧል:: የጎንደር ህዝብ ዝግጁ ነኝ ብሏል:: ደብረ ብርሃን ዛሬ ታሪካዊ ገድል ፈፅማለች:: የሰሜን ሽዋ ህዝብ ሙሉበሙሉ እምቢ ብሎ ተነስቷል:: ከጨፍጫፊው ጋር ፊት ለፊት የገጠሙት የሽዋ አናብስቶች በጠላት ላይ ትልቅ ድል ተቀዳጅተዋል:: የይታገሱ አምላክ ይርዳችሁ!

ለአንድ ሳምንትብቻ የሚቆይ foreign currency reserve ብቻ የቀረው ስርዓት ለመንግስት ሰራተኞችና ወታደሮች ርምወዝ መክፈል ያቃተው ይህ ስርዓት መፍረሱ የማይቀር ነው:: ካዝናው ባዶ ነው:: አንድ ጥይት በተኮሰ ቁጥር እየከሰረ የሚሄድበት ሁኔታ ነው:: ለወታደራዊ ሎጂስቲክ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለማመላለስ ነዳጅ ይፈልጋል:: ነዳጅ ደግሞ የሚመጣው በዶላር ነው:: አማራ ይህ የጀመረውን ትግል እስከ መጨረሻው ድረስ ታግሎ ከግብ ሳይደርስ አይመልሰም:: ጥያቄው የልዮሀይል መሳሪያ ፍታ አልፈታም ከሚለው ወደ ስልጣን ልቀቅ ተሸጋግሯል::

የአማራ ህዝብ የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አፋር ሱማሌ ጋምቤላ ቤነሻንጉል ሲዳማ ጉራጌ ወላይታ ደቡብ ሁሉም ኢትዮጵያውያን መቀላቀል አለበት:: ዜጎች በሀገራቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረው ቤታቸው እላያቸው ላይ በግሪደር እያፈረሰ የሚያፈናቅል ስርዓት አንድም ቀን ማደር የለብትም:: የ አማራ ህዝብ ባለፉት አምስት አመታት በመንግስት በሚደገፈው አውሬ ሰራዊት ኦሮሚያ በሚባለው ክልል በተለይ በወለጋ በየቀኑ ሲጨፈጨፍ "ለውጡ እንዳይቅለበስ" እየተባለ ሁሉም ይህን ጭፍጨፋ በዝምታ ሲያልፍ ቆየ::

በ30 ሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናትና ሴቶች ሽማግሌዎችና አቅመ ደካሞች ሰፋሪ እየተባሉ እንደ ዶሮ ሲጨፈጨፉ ቆዮ:: በሚልዮኖች ደግሞ የለፉብትን ሃብትና ንብረት በመዝረፍ እንዲፈናቀሉ ተደረገ:: ይህ ስደተኛ ህዝብ አዲስ አበባ አትግባም ተብሎ ዛሬ በአማራ የተለያዮ መጠለያ ካምፕ እርዳታ እየጠበቁ ይገኛል:: አማራ ክህክምናና ለሌሎች ጉዳዮችን ለማስፈጸም ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ መንገድ ተዘጋብት:: ትእግስትም ልክ አለው::

የአማራ ህዝባዊ ንቅናቄ የስርዓት ለውጥ ሳያመጣ በፍጹም ሊቆም አይችልም:: ወደ አማራ "ክልል" የገባው የጥፋት ሃይል እንዳይወጣ የሚመጣውም እንዳይገባ በሁሉም አቅጣጫዎች መንገዶችን መዝጋትና ህዝባዊ ሃይሉ አካባቢውን ይጠብቅ:: የውስጥ አርበኞች ካሉም የማያዳግም እርምጃ ይወሰድባቸው:: የኦሮሙማ ጨፍጫፊ መንግስት እነዚህን የውስጥ አርበኞች ተጠቅሞ ጥቃት ለማድረስ እየሞከረ ቢሆንም የአማራ ህዝብን ለሆዱ አሳልፎ የሚሰጥ ካለ ወንድም ወይም እህት ቢሆን ምህረት አይደረግለትም:: ይህ የአማራ ህዝብ የሞት ሽረት ትግል ነው:: የቀረው ምርጫ መጥፋት ወይም መኖር ነው::

ትግሉ አሁን ባለብት ሁኔታ ከቀጠለ ሌሎች አካባቢዎችን ይህን ህዝባዊ ንቅናቄ በመቀላቀል መታገል ይጠበቅባቸዋል:: ይህ bankrupt የሆነ ስርዓት ምንም ደምወዝ መክፈል ሳይችል 50 ሚልዮን ህዝብ ላይ ጦርንት አውጇል:: በአማራ ግዛት ብቻ 13 ሚልዮን ወጣት ሲኖር አብይ አለኝ ከሚለው 700 ሺህ ወታደሮችን እንኳን ቢያሰለፍ ሊያሽንፈው የማይችል ልበ ሙሉ ጠንካራ ቆራጥ ወጣት እንዳለን አንርሳ::

በሰሜኑ ጦርነት ኦሮሙማ ከፊት እያስቀደመ ያስጨረሳቸው ከደቡብ ኢትዮ የመጡ ወታደሮች ዳግም ወደ አማራ ዘምታቹ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዳትከፍሉ:: መዋጋት ከፈለገ ኦሮሙማ በ40 ዙር ያሰለጠነውን ሃይል ያስገባና ያኔ ጥሩ ይሆናል:: ይህ የአዲስ አበባን ህዝብ ለማረድ የተዘጋጀ ጦር አማራ ክልል መቀበሪያው ይሆናል:: ለማንኛውም እንበርታ ትግሉ ፈርና መስመር እየያዘ ነው:: ሁሉም አማራ ወንድ ሴት ህፃን አዋቂ ሽማግሌ አቅመ ደካማ ሳይል በህብረት በመቆም የአማራ ህዝባዊ ሃይሉን በሚችልው ሁሉ ይደግፍ:: አስፈላጊውን ሎጂስቲክና መረጃዎችን በማቅረብ ይረባረብ:: I can guarantee you አማራ ያሸንፋል !

ድል ለአማራ ህዝብ!!

Re: በአማራ ክልል ህዝባዊ እምቢተኛነት በይፋ ከተጀመረ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን አስቆጠረ!!!!

Posted: 11 Apr 2023, 08:28
by Ejersa