የኢትዮጵያዊ ፕሮቴስታንትነትን ማስተዋል ከልጅነቴ ነዉ የጀመረዉ። የካቶሊክ ፕሮቴስታንት ልጅ መሆኑ በቅርቡ ነዉ የገባኝ።
ከሁሉ በላይ የማልረሳዉ ገጠመኝ ግን የዛሬ የሃገር ኣዛዉንት፣ ከዛም በፊት የኢትዮጵያ ኣጼ፣ ካዛም በፊት የደቡብ ኢትዮጵያ መሪ፣ ከዛም በፊት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መሪ እና ዲን፣ ከዛም በፊት ኣስተዋይ ኣስተማሪ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የነበረበት ተማሪ ሆኜ የነበረ ጊዜ ነዉ።
ኣንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አረት ብዬ ስማቸዉን ልጠራ የምችል ብሩህ ተማሪዎች እዉቀትን ከመቅሰም ወደ ትሁት ኣማኞች የተቀየሩ ወይም ያዘነበሉ ኣስተዉዬ ኣዝኛለሁ። ዛሬ ሳይሆን ያኔ።
ለምሳሌ ኣንዱ የኢትዮጵያን የማትሪክ ፈተና ከእኔ ጋር ተመሳሳይ ዉጤት ኣግኝቶ ያለፈ ነዉ። ምናልባትም ከእኔ የተሻለ ዉጤት የነበረዉ እንደሆን ኣላዉቅም። እኔ ሆነ ብዬ ለአምስት ትምህርቶች ብቻ ነበር የተዘጋጀሁኝ። የዉጤት ቁጥር ዉስጥ የሚገቡ የነበሩ።
ሁለታችንም የባሌ ልጆች ኣይዴለንም። እሱ የባሌ ሰዉ ነዉ።
ትምህርት ላይ እያለን ነዉ መቀየሩን የሰማሁኝ። እኔ ሰዉ ለምን የመሰለዉን ሃይማኖት ይከተላል ብዬ ኣልከራከርም። ሃይማኖት ዉስጥ ስላሉት ጭብጥ ሀሳቦች ላይ ዉይይት ከተነሳ ሀሳቤን እሰጣለሁ።
ብሩህ ተማሪዎች፣ በተለይ እዉቀት በሰፊዉ መቅሰም በሚችሉበት ዕድሜ እና ቦታ በስብከት ምክንያት ሲዘናጉ ሳይ ወይም ስሰማ ስለኣዲስ ሃይማኖት ስለተማሩት ሳይሆን እዉቀትን ከመቅሰም ስለተዘናጉት ኣዝናለሁ። ኣዝኛለሁ።
ያ ሰዉ ዛሬ ዬት እንዳለ ኣላዉቅም። ትምህርት ላይ እያለን ኣንድ ቀን ካፍቴርያ ዉስጥ እራት እየበላን የተወያየነዉን የፕሮባብሊቲ እና ስታቲስክስ ኮርስ እና ስለነበረዉ ብሩህነት በደንብ ኣስታዉሳለሁ።
ኣሜርካ ደርሼ ተመሳሳይ ኮርስ ወስጄ ማለፌን ያጤነች የኣሜሪካ ከፈተኛ ትምህርት ባለስልጣን ይህን ኮርስ ካለፍክ ችሎታ ኣለህ ማለት ነዉ ስትል ስሰማ ቀነኒሳ ሀይሌን ወደ ኋላ ዞሮ እንዳየዉ ያን ብሩህ ተማሪ ኣስታወስኩኝ። ኮርሱን ማለፍ ከባድ መሆኑን ነዉ የተናገረችዉ።
የማዉቀዉ የኢትዮጵያ የማትሪክ ፈተና፣ በተለይ ሂሰቡ፣ ከወሰድኳቸዉ ሌሎች ፍተናዎች፣ የኣሜሪካዉን ጂአርኢ ኳንቲቴቲቭ ክፍል ጨምሮ፣ የላቀ ቢሆን እንጂ ያነሰ አይመስለኝም።
ስለዚህ የኢትዮጵያዊ የካቶሊክ ፕሮቴስታንነት የኢትዮጵያ ከፈተኛ ትምህርት ላይ ጎጂ ነዉ ወይስ ጠቃሚ ጎኑ ነዉ የምያመዝነዉ? የኢትዮጵያዊ ሃይማኖት ፕሮቴስታንትነት የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከጊዜ ጋር እንዲራመድ ፕሮቴስት ማድረግ ከሆነ ወደ ጎፍታ/ጎይታ/ጌታ ወይም ጦሳ ካላመራ ኢትዮጵያዊ ፕሮቴስታንት እዉን ፕሮቴስታንት ነዉ ወይስ ኢትዮጵያዊ የካቶሊክ ፕሮቴስታንት? መልሱን ኣላዉቅም።