Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15436
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የሁለት ትዩዩሽ ዓለማት ጉዳይ--> ትራምፕ በአሜሪካ ገንዘብ ከፍለህ ሴት አዳሪ አማግጠሃል ተብሎ እስራት ሲቆረጥበት፤ በኢትዮጵያ 1 ሚልዮን ነፍስ የበላ ወያኔ እና ኦነግ-ብልጽግና ነጻ ይኖራል

Post by Abere » 31 Mar 2023, 11:03

የሁለት ትዩዩሽ ዓለማት ጉዳይ--> ትራምፕ በአሜሪካ ገንዘብ ከፍለህ ሴት አዳሪ አማግጠሃል ተብሎ እስራት ሲቆረጥበት፤ በኢትዮጵያ 1 ሚልዮን ነፍስ የበላ ወያኔ እና ኦነግ-ብልጽግና ነጻ ይኖራል።

ይህ የአሜሪካው ዳኛ እና ፍርድ ቤት በጥቂቱ የሚከተሉት ወንጀሎች ላይ ምን ይፈርዱ የሆን?

1) ልጇን በብዙ ጥይት ከገደሉ በኋላ አናት በልጇ አስከሬን ለረጅም ደቂቃዎች ሳታለቅስ እንድት ቀመጥ ባደረጉት ላይ፤ [ የኦሮሞ እናት መከራ ያስታውሱ]

2) ባል የኋልዮሽ በገመድ ከወንብር ጋር ታስሮ ሚስት በደረሱ ልጇቿ ፊት በመንጋ ስትደፈር - የግብረ-ስጋ መጫዎቻ አሻንጉሊት ስትሆን። [ የቡራዮ ጋሞዎችን ዋይታ ያስታውሱ]

3) እርጉዝ ነፍሰ-ጡር እናት ሆድቃዋ በሳንጃ ተቀድዶ ጽንሱ ወጥቶ ሲበላ ወይም ሲጣል [ የወለጋ አማራዎች እንባ ያስታውሱ]

4) በአደባባይ በጠራራ ጸሀይ መቀጣጫ የሆኑ እና ከተማውን ጥለው የትም እንድ ሰደዱ በድንጋይ ተወግረው የተገደሉት ምስኪኖች ሞት [ አዋሳ ከተማ የወላይታ ለቅሶ ያስታውሱ]

5) ከአሜሪካን አገር በእንግድነት ለሚገባው መቀበያ ይሆን ዘንድ በሻሼመኔ ከተማ እንዴ መስዋዕትነት በግ በእንጨት ላይ ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ ነፍሱ እስኪ ወጣ እያጨበጨቡ ትርኢት የታደመበት [ የሻሼመኔ የግፍ ጥግ ያስታውሱ]

6) በጎንደር ማይ-ካዲራ ቤታቸው ተዘግቶ በድቅድቅ ጨለማ አንገታቸው የተቀላ - ቤት ተዘግቶ በእሳት የነደዱት አማራዎች [ የወልቃይት ሁመራ ግፍ ያስታውሱ]

7) ሰላማዊ የአዲስ አበባ ከተማ ኗሪዎች በሌሊት ቤታቸው ላያቸው ላይ በዶዘር የፈረሰባቸው - ልጆቻቸውን በጅብ ተነጥቀው መከራ የወረደባቸውን

8) የቤት እንሰሳት እንደ ጥላት ተቆጥረው በጥይት ተደብድብው ከተፈጥሮ ውጭ በሆነ ጭካኔ የተረሸኑት ( የወሎ እና ጎንደር አርሶ አደር ጥሪት ላይ የተፈጸመውን ግፍ ያስታውሱ]

9) የወሎ ግብር ከፋይ ዜጋ በእራሱ ገንዘብ በተገዛ የጦር መሳርያ በ 3 ምልልስ (ዙር) የታሰበበት መንግሳትዊ ወረራ፤ግድያ፤ዝርፊያ፤ ጥቃት የተፈጸመበትን [ 450 ቢልዮን ሃብት ውድመት ያስታውሱ ]

10) ወዘተ......... [ ህልቆ መስፈርት የሌላቸው የ31 አመታት ግፎችን ሁሉ ያስታውሱ]