የግፍ ግፍ: በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከ6ኛ ፎቅ የወደቀችው ሠራተኛ በሕይወት ተረፈች
Posted: 30 Mar 2023, 09:02
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዕድሜዋ 40 የተገመት አንዲት የሆስፒታሉ ሰራተኛ ትላንት ሌሊት 10:30 ላይ ከ6ኛ ፎቅ ላይ "ዘላ ወደ ምድር በመዉደቋ ከባድ ጉዳት ደርሶባታል" ሲል የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ለኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥሪ የተደረገውም፥ ከ6ኛ ፎቅ ወደ ታችኛዉ ወለል ወደ ቤዝመንት ዉስጥ የወደቀችዉን ተጎጂ ከወደቀችበት ለማንሳት ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ መሆኑ ተገልጿል።
የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም በመሰላልና በገመድ በመጠቀም ተጎጂዋን በህይወት ማውጣት ችለዋል። ተጎጂዋ ከአደጋዉ በህይወት ብትተርፍም ከባድ ጉዳት ደርሷባታል ተብሏል።
ከ1 ሳምንት በፊት መኖሪያ ቤቷ በከንቲባ አበደች ደደቤ ትእዛዝ የፈረሰባት ተጎጂዋ በሆስፒታሉ ተረኛ አዋላጅ ነርስ ሆና ምሽቱን የተለመደ ስራዋን ከባልደረቦቿ ጋር ስታከናዉን እንደነበር ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።