Page 1 of 1

Abiye Ahmed on the Gurage demand to be killil ON HIS OWN WORDS

Posted: 29 Mar 2023, 17:19
by Right
የጉራጌ ሕዝብ ሰሞኑን የክልል መንግሥትነት ሲጠይቅ አቢይ ምን አለ? “ክልል እንድትሆኑ ብፈልግ አምስት ደቂቃ አይፈጅብኝም፡፡ ግን ስለማይጠቅማችሁ አልፈቅድም፡፡”

አዲዮስ ፓርላማ! አዲዮስ የሚኒስትሮች ካቢኔ! በአንድ ሰው በጎ ፈቃድ ውሎ የሚያድር የምሥኪን 120 ሚሊዮን ሕዝብ ሕይወት በምናባችሁ ይታያችሁ፡፡ በቅርቡ በቀን ስንቴ መተንፈስ፣ ስንቴ ዐይኖቻችንን ማርገብገብ እንደሚኖርብን በዐዋጅ ሳይደነግግ ይቀራል? የአቢይ መንግሥት እኮ ምን ዓይነት ቀለም የተነከረ ልብስ መልበስ እንዳለብን የሚወስን፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማትን ከመጥላቱ የተነሣ በልብሳችንም ሆነ በሰውነታችን እነዚህን ቀለማት ብናሳይ አይቀጡ ቅጣት የሚቀጣን ምስኪን ዞምቤዎች ሆነናል፡፡ ዞምቤ ማለት በሰው አምሳል የተፈጠረ እንደኛው ተናጋሪ እንስሳ ማለት ነው፡፡