Page 1 of 1

በእውቀቱ ስዩም : ሁሉም ለቅሶ ላይ ነው

Posted: 24 Mar 2023, 09:09
by Thomas H
Bewketu Seyoum

አገር በሚያልፍበት ባዘቦት መንገዱ
(በእውቀቱ ስዩም)
አገር በሚያልፍበት ፥ ባዘቦት ጎዳና
በሁሉም ሰው ፊት ላይ ፥ትካዜ ተስሎ
ሲመስል ደመና
ማን ከማን ተሽሎ
ማን ማንን ሊያጽናና?
በዕንባ ስፍር እንጂ የምንለያየው
ክንብንቡን ገልጦ፥ ቀረብ ብሎ ላየው
ሁሉም ልቅሶ ላይ ነው ::
በየትኛው ዘመን ፥ይፈርሳል ድንኳኑ
የምስራች መምጫው መቼ ይሆን ቀኑ?
ብየ ብጠይቅም
መልሱን ግን አላውቅም::
አገር በሚያልፍበት፥ ባዘቦት መንገዱ
ባስፋልት በሐዲዱ
መርዶ እየዘለለ
ብስራት ግን ይድሀል
በዚህ ሁሉ መሀል
እኔን ስታስቢ
ፈገግታሽ ፤ ከናደው
ፊትሽ አካባቢ
ያንዣበበውን ጉም
በሕይወት መኖሬ፥ አለው ትልቅ ትርጉም::