Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Ejersa
- Member
- Posts: 3978
- Joined: 05 Nov 2019, 10:39
Post
by Ejersa » 23 Mar 2023, 12:17
በትግራይ፥ "ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ" የሚለው በግነት የተሞላ ትርክት ከራሱ ከትርክቱ መነሻ ጋር ሦስት ትውልድ በልቷል። አያት፣ አባትና ልጅን የሕይወት ዘመን የአካል ጉዳተኛ አድርጓቸዋል።
በትጥቅ ትግሉ፣ በባድመ ጦርነት እና በአሁኑ ጦርነት አያት፣ አባትና ልጅ አካለ ጎደሎ የሆኑበት የትግራይ ፖለቲካ ሙሉ ትራጀዲ ለኢትዮጵያም የተረፈ መሆኑ ይሰመርበት።
ዛሬ በትግራይ ያለ አካለ ጎደሎ 'የጉዳት መቼት' ለማወቅ 'የደርጉ ነው ወይስ የብልጽግናው?' እንዲህ ያደረገህ ብሎ መጠየቅ ግድ የሚልበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
አያት፣ አባትና ልጅ አካለ ጎደሎ ለመሆን ያበቃቸውን፤ ከአማራ፣ አፋርና ኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አፋሳሽ ቅራኔ ውስጥ የከተታቸውን የእብደት ፖለቲካቸውን መርምሮ ለመከለስ/ለማረም ከመነሳሳት ይልቅ ዛሬም ለአራተኛ ዙር ጦርነት ምልመላ፣ ልምምድና ስልጠና ላይ ናቸው።

-
Right
- Member
- Posts: 4818
- Joined: 09 Jan 2022, 13:05
Post
by Right » 23 Mar 2023, 12:33
EJ,
Through the permission of your idle, they are back in town..
We will see if they trick or wrestle the saddle from Abiye.
This time though Ethiopians will not be used to protect.
The TPLF definitely will outsmart Abiye in the game. It is a matter of when. The CIA has a benefit of knowing when.
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 15436
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 23 Mar 2023, 12:39
ጥላቻ ይጎዱበታል እንጅ አይጠቀሙበትም። ለሌሎች የበጠበጠውን (የጎሳ) መርዝ እራሱ ጠጥቶ ሰክሮ የሞተ ትውልድ የትግራይ ትውልድ ነው። በምን አይነት የታሪክ ምሳሌ መጭው ትውልድ እንደሚያስታውሳቸው ይገርመኛል። 50 አመታት በላይ የተዋጉበት አላማ የሌሎችን በመስረቅ እና በመዋሸት የእራስ ማድረግ። እንድህ ያለ ታሪክ ተሰምቶ አይታወቅም። ሰሞኑን ሰላማዊ ሰልፍ የወጣውን የራያ አለማጣ ህዝብ ብዛት አይቸ እጅግ ተደነቀኩኝ ያንን ሁሉ ነው በጉልበት ትግሬ ሁን ተብሎ በመሳርያ አፈሙዝ ተገዶ 30 አመት ሲረገጥ የኖረው። ምን አይነት ዕብደት ምን አይነት ስካር እንደያዛቸው የትግራይ ትውልድ ይገርማል። አሁንም የጥላት መጠቀምያ መሳርያ ከመሆን ስለማይዘሉ ሌላ ውደቀት እጣ ፈንታቸው መሆኑ አይቀርም። በሰላም እና በፍቅር መጠቀም ሲችሉ በትዕቢት እና በጥላቻ ስር ወድቀው በጦርነት፤በችግር ሲማቅቁ ይኖራሉ። ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ሲያለቅስ ይኖራል ነው እና አማራ፤አፋር እና ኤርትራ እንድሁ ይህን ከባለፈው የማይማር ህዝብ እንድሁ ሲመክሩም: ሲቀጡም ይኖራሉ።