Page 1 of 1

ጉራጌ መረሮ!

Posted: 21 Mar 2023, 21:27
by Horus


ይህ እጅግ ግዜያዊ ነጠላ ዜማ ዛሬ የተለቀቀ ነው ! ጉራጌ መረሮ ማለት ጉራጌ ተቆጣ ማለት ነው ! አቢይ አህመድ የጉራጌ ሕዝብን ከፋፍሎ በግድ በክለስተር ጭፍልቆ ጉራጌ የተባለ ሕዝብና ካልቸር ሊያከስም በሚያሴርበትና በነገው ሃሙስ ከጉራጌ ባለሃብቶች ጋራ ሊዶልት በተዘጋጀበት ሰዓት ይህ ዜማ ከክስታኔ ጉራጌ (ከሶዶ ጉራጌ) ክልልን በመደገፍ መውጣቱ ደስ የሚያሰኝ ብቻ ሳይሆን መላ ጉራጌ በአንድ ድምጽ ክልልነት ብቻ እንደ ሚደግፍ መልክቱ እንዲደርሰው ይሁን!! ኤቦ ለታላቁ የጉራጌ ሕዝብ በጎጎት ቃል ኪዳን ለጸናው !!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ጉራጌ አንድ ነው !!



Re: ጉራጌ መረሮ!

Posted: 21 Mar 2023, 21:52
by Horus
ጉራጌ አገር አቀፍ ፓርቲውን ጎጎት ፓርቲን ባቋቋመ እና አቢይ የፓርቲው መሪዎችን ገና ከስብሰባ ሲወጡ ባሰረ በሳምንቱ ጉራጌን ለመከፋፈል፣ ለማታለል፣ ለማስፈራራት ነው ለነገ ሃሙስ ስብሰባ የጠራው ! ስልጣን ላይ ከመጣ ጀምሮ ጉራጌን ሲታፍን፣ ሲያስር ሲግድል ከርሞ ዛሬ ለምን?

ጉራጌ ገና በከፍተኛ ደረጃ ይደራጃል! አንድ ይሆናል መብቱ እስከ ሚከበር ድረስ !

Re: ጉራጌ መረሮ!

Posted: 21 Mar 2023, 22:26
by Horus