Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42798
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

መደመርና መደበር፤ የመንትዮቹ ፍቅረ ቃል (ፊሎሎጂ)

Post by Horus » 21 Mar 2023, 00:16

ውጭ የተሰጣ ነገር ፀኃይ መሞቁ አይቀርም ። ከዚህ ቀደም መደመር የተባለው ሲሊቻ የለማኝ እህል ማከማቻ ወልቀሎ ፍሬምወርክ ነው ብዬ ነበር ። እኔ ሃተታ አላበዛም ። የለማኝ እህል ፈረንጆች ኤክሌክቲሲዝም ይሉታል ። ያ ደሞ ቂርማ ከዚም ከዛም የተለቀመ የተቃረመ ክምችት ማለት ነው ።

ቂርማ አከማቸው ማለት ደመረ፣ ከመረ፣ ስለቀጠ፣ ዋጠ፣ ደበለቀ፣ አከማቸው ሰበሰሰ፣ ዋጠ፣ ቀማ፣ ጎተረ ፣ ከተረ፣ ሰበሰበ፣ ከመረ፣ ደመረ፣ ተቆጣጠር፣ ዲካተተረ ደከተረ እንደ አምባ ገነነ !!! አገር ደሀየ ዋጋ ናረ! ሌብነት እንደ አምባ ገነነ!! የህዝብ ኑሮ ቀነስ፣ ተቀነሰ፣ ወረደ፣ አዘቀዘቀ! ሁሉም ነገር አልተደምሮማአል ! አል ተደደመረ እያለ በአዎንታም በአሉታም የረባል ።

አንድ ነገር እንደ ቆጬ ተካማችቶ፣ ተኮማትሮ፣ ተጣጥፎ ስብስብ ብሎ ቁጭ ሲል ተደመረ ተደበረ፣ ተደረደረ ፣ ተገተረ ድብር አለ፣ ድብርት ሆነ፣ በደብሩ ተቀመጠ ማለት ነው። መደመር መደበር ነው ። የተደበረ ነገር ደሞ ፈዘዘ፣ ደነዘዘ፣ መንቀሳቀስ አቆመ፣ በደነ፣ በድን ሆነ ማለት ።

በፈረንጆች ዘንድ እንደ እቃ ተደምሮ እንደ እሬሳ የሚደበር ያይምሮ ህመምተኛ ዲፕሬድ ሆነ፣ ከህይወት ወጣ፣ አንጎሉና አይምሮው ፈዘዘ፣ ደነዘዘ ይባላል ። እጅግ ጠንካራ የሳይኮሎጂ በሽታ ነው ። ተደማምሮ በደበር ማለት እንደ ድንጋይና በድን አሻንጉሊት እቃ መሆን ማለት ነው።

ጤነኛ አንጎልና ብሩህ አይምሮ ያለው የሚያስብ ነጻ ሰው ንቃተ ህሊና ያለው ተመራማሪና ጠያቂ ሰው ጠያቂ ትውልድ ዝም ብሎ እንደ ከብት እየተነዳ አይደመርም፣ ተደምሮም አይደበረም! ተደመረ ተደበረ ! በቃ!!!