https://mereja.com/forum/viewtopic.php? ... B#p1350091
ብርጋዴል ጀነራል ሃይሉ ጎንፋ ይናገራል:: ለማ መገርሳም አብይ አህመድም ኦነግ ሸኔ ናቸው ይለናል:: እኔን ጨምሮ እዚህ ያላችሁትም ኦነግ ሸኔ ናችሁ ሲላቸው አዳራሹን በጭብጨባ እና በፉጨት ያቀልጡታል:: ለመሆኑ የአማራ ብልፅግና ቢጠይቅ ምን ይል ይሆን?
የኦነግ ለሙኛችሁ ፖለቲካ የአብይ አምላኪዎች የዱኩማን ገደል ማሚቱዎች የሚያስተጋቡት
እንደ ታዘብኩት ከሆነ:-

የዘር ፖለቲካው ተወግዶ የዜግነት ፖለቲካ መመስረት አለበት ማለት አሃዳውያን፣ ትምክህተኛ ያስብላል::

የዘር ፖለቲካው ከቀጠለ አማራ እንደ አንድ ብሔር ራሱን የሚያስተዳድርበት፣ የሚከላከልበት እድል ማግኘት አለበት ሲባል በዘር የተደራጁትም ዘረኛ ይሉታል።

ሲገደል እራሱን ለመከላከል ጥረት ሲያደርግ እና ለመደራጀት ዳዴ ሲል "ፅንፈኛ" ይባላል።

አማራ ተገደለ ሲባል አንድ ቢባል ጭጭ የሚሉ፣ በሌላ በኩል አዘኑ እንዲባሉ ገዳዩ እየጠራ የገደለበት ስም እንዳይነሳ የተለያየ ምክኒያት እየፈጠሩ ሰው ሞተ ብቻ በሉ ይላሉ::

በመንግሥት አጋዥነት መጨፍጨፉ በዝቶበት የወገኑ ደም ባሰከረው ወኔ በሌለው አቅም ቀጥታ የመጣበትን ሞት ለመመከት ሲሞክር ትርክቱን በብርሃን ፍጥነት ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ያዞሩና ገዳይን ሊጠቅም በሚችል መልኩ ፖለቲካ መስራት ይጀምራሉ።
እኔ ግን እላለሁ! በአጠቃላይ ይህንን ትብታብ በጣጥሶ የማይወጣ የአማራ ትግል ለምስኪኑ ህዝብ የአርመኖቹን እጣ ፋንታ ከማጎናፀፍ ያለፈ ፋይዳ የለውም::
ማንም ምንም ይበል ህልውናውን ከመጥፋት ለመታደግ ይሉኝታ ቢስ ትግል መደረግ አለበት ብዬ የማምን ሰው ነኝ! ምንም እንኳን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከልቤ የምወድ እና የምሳሳለት ቢሆነም በአማራው ሞት ላይ የምትቆም ጤነኛ ኢትዮጵያ ልትኖር እንደማትችል ጠንቅቄ አውቃለሁ::
አይዳ (ቃል እና ቀለም)