ጦርነቱ አዲስ አበባ ደርሷል - አዲስ አበባ ተረኛዋ በሻሻ
Posted: 02 Mar 2023, 10:18
ጦርነቱ አዲስ አበባ ደርሷል - አዲስ አበባ ተረኛዋ በሻሻ
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ!
አንችንም በሻሻ ሊያደርጉሽ ነወይ!?
የጥንቷ በራራ - የዳዊት ከተማ፥
የጣይቱ አበባ - የኢትዮጵያ ማማ፥
ዋይታ እና ጩኸትሽ ከእርቀት ተሰማ።
መንገዱ ተዘግቷል ወገን እንዳይረዳሽ፤
እንደ ንፍሮ ዘግቶተው አንችን ሊቀቅሉሽ፤
ማገዶ ሰብስበው በእሳት ሊያጋግሙሽ፤
ፈልተሽ ወይ ገንፍለሽ አጥፊያቸው ከዙሪያሽ።
በበሻሻ ስሟ እየተማማሉ - እየተገዘቱ፤
አስበዋል እንጅ እኝህ ዘረ ገልቱ።
ጦርነቱ አንች ላይ መሆኑን አውቀሽ፥
ድል መንሳት አለብሽ ጥርስሽን ነክሰሽ፥
እባቡ እግርሽን ሲል እራሱ መትረሽ።
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ!
አንችንም በሻሻ ሊያደርጉሽ ነወይ!?
የጥንቷ በራራ - የዳዊት ከተማ፥
የጣይቱ አበባ - የኢትዮጵያ ማማ፥
ዋይታ እና ጩኸትሽ ከእርቀት ተሰማ።
መንገዱ ተዘግቷል ወገን እንዳይረዳሽ፤
እንደ ንፍሮ ዘግቶተው አንችን ሊቀቅሉሽ፤
ማገዶ ሰብስበው በእሳት ሊያጋግሙሽ፤
ፈልተሽ ወይ ገንፍለሽ አጥፊያቸው ከዙሪያሽ።
በበሻሻ ስሟ እየተማማሉ - እየተገዘቱ፤
አስበዋል እንጅ እኝህ ዘረ ገልቱ።
ጦርነቱ አንች ላይ መሆኑን አውቀሽ፥
ድል መንሳት አለብሽ ጥርስሽን ነክሰሽ፥
እባቡ እግርሽን ሲል እራሱ መትረሽ።