Page 1 of 1

የኢትዮጵያ እናት እምዬ ምኒልክ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንነትና ማንነት ቀይ መስመር!

Posted: 25 Feb 2023, 20:28
by Horus
ተራ በተራ ተነስተው የሚወድቁ የጎሳ ሹክሻኮች ለዘመነ ዘመናት ቢታክቱ እምዬ ምኒልክ ዳግማዊን ከአድዋ! ኢትዮጵያን ከምኒልክ! ምኒልክን ከልሙጡ ሰንደቅ ለመለየት ቀይ መስመር ፋውል ረጋጭ ሁሉ እንዳለፉት የኢትዮጵያ ጠላቶች ወደ ታሪክ ትቢያ ይጣላሉ !

በሚቅጥሉት 4 ቀናት ብዙ ድራማ፣ ብዙ ቲያትር እናያለን ። የኦሮሞ ተገንጣይ ልፋት ምኒልክን ከአድዋ የሚገነጥል አድዋ እንደ ክብር ምኒልክ እንደ ወራሪ ለመተረክ የሚዳክሩት አዲሱ ቆሻሻ የጎሳ ናሬቲቭ ያው እንደ ተለመደው አፍንጫቸው ላይ ይፈነዳል ።

ታላቁ መሪ መቃብሩ ውስጥ እንዳያርፍ ይህን ዘመን ሁሉ ለፉ ባከኑ ። ዛሬ የኢትዮጵያ ማነንት፣ የሕዝቧ ህልውና መገለጫው ፈተና፣ ውዝግብ፣ የማይታለፍ ቀይ መስመር የኢትዮጵያ እናት እምዬ ምኒልክ ነው ።

ደሞ ትግሉ ይቀጥላል እንጂ አድዋ በወያኔ ባንዲራ አይከበርም ። ኣድዋን አለ ምኒልክ፣ ምኒልክን አለ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ወይ ፍንክች ! መንግስት የመጣል መንግስት ይሄዳል ! ማንም ይህን ቀይ መስመር ሊጥስ አይችልም !

ለሚቀጥለው 4 ቀናት ጆሮአችን በኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ እንደ ሚዶነቁር ተጠባበቁ!

Re: የኢትዮጵያ እናት እምዬ ምኒልክ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንነትና ማንነት ቀይ መስመር!

Posted: 25 Feb 2023, 20:44
by Horus