Page 1 of 1

የኦነጉ አገዛዝ መከላከያውን ከ ትግራይ ሃሎች ጋር በማናበብ የዐማራ ህዝብ ላይ ለማዝመት ዝግጅቱን እያደረገ ነው

Posted: 23 Feb 2023, 12:07
by Za-Ilmaknun
በኤርትራና በአማራ ሃይሎች ከመጥፋት የዳነው መከላከያ፥ ዛሬ ላይ በ ኦነጉ መሪ አብይ አህመድ ትእዛዝ የአማራ ህዝብ ላይ ጥፋት ለመፈፀም እየተዘጋጀ ይገኛል። በወለጋ፥ በአጣዬ፥ በሻሸመኔ፥ በአበርገሌ ንፁሃን በሽፍታ ስጨፈጨፉ፥ ትእዛዝ አልተሰጠኝም እያለ የሚያለግመው ሃይል ዛሬ ላይ ከውድቀትና ከጥፋት የታደጉትን ሃይሎች ከድቶ፥ ሊዘምትባቸው ፥ ሲዘጋጅ ማየቱ፥ የአራት ኪሎው የጥፋት ቡድን ሃገር ለማፍረስ ቁርጠኝነቱን ማሳደጉን ግልፅ ያደርገዋል፣፥

በግፍ አገዛዝ ስር የወደቀው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የኦነግን ስርዐት በቃህ ካላለው፥ ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ ሃገር እንደማይኖረን መረዳቱ ከባድ አይሆንም። አማራውና ክርስቲያኑ ላይ የተያዘው ዘመቻ፥ የ አብይ አህመድን ፖለቲካዊ ፍላጎት ያሳየ ብቻ ሳይሆን፥ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከባድ የፍጅት አደጋ የደቀነ እንቅስቃሴም ነው።መከላከያው የ ኦነግ መጠቀሚያ ከመሆን ራሱን ካልጠበቀ፥ የመከላከያውም ህልውና ማክተሚያው ብቻም ሳይሆን፥ ለሚፈጠረው ከባድ ደም አፋሳሽ የ እርስ በርስ ጦርነት አበርክቶቱ ከፍተኛ ነው።