Page 1 of 1

የብአደን (አዴፓ) አገራችሁን አድኑ ጩኸት ለማን እና ከነማን ነው?

Posted: 22 Feb 2023, 10:50
by Abere
የብአደን (አዴፓ) አገራችሁን አድኑ ጩኸት ለማን እና ከነማን ነው? እንደ እኔ የአደፓን ጩኸት ቀለል አድርጌ አላየውም። ይህ ጩኸት ስልጣኔ ሊነካብኝ ነው ከሚል የላቀ ይመስለኛል። ወንበሬ ሊነካብኝ ነው ጉዳይ የሚጣል ባይሆንም ከዚህ ከበድ ያለ የአገሪቱን ህልውና ሊያጠፋ የሚችል ሴራ እንዳለ አሁን የገባቸው ይመስላል። It is a whistle blower of imminent crisis and collapse of the leadership of the country. አንዳንድ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ይህ ጥሪ ለአማራ ህዝብ የሚመስለውም ይኖራል - እርሱም ትክክል አይደለም። የአማራ ህዝብ ቀደም ብሎ አደፓን ሲጠራው እና ሲፈልገው ነበር። በፊት ሲፈለግ የጠፋ አሁን ፈላጊ ሊሆን እንደት ይችላል? ይህ ጥሪ ከአማራ ውጭ ጭምር ነው። ይህ አገርህ ፈረሰችልህ ኡኡ ታ በድፍን አገሪቱ በኦሮሙማ ለሚሰቃየው ለወላይታ፥ ለጋሞ፥ጉራጌ፥ ጌደዎ ፤ ዳዋሮ ፥(ደቡብ ኢትዮጵያዊያን)፤ ለሱማሌ፥ ለአፋር፥ ለጋማቤላ፤ ለትግሬ፥ ለአማራ፥ ለኦሮሞ እንድሁ ለእስላም ክርስቲያኑ፤ ወዘተ ነው ይሚል አመለካከት አለኝ።

ይህ በብልጽግና መካከል ሰፊ የመሰንጠቅ ምልክት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ፤የሰላም፣ የመረጋጋት እና የፓለቲካ ቀውስጥ ያለች የፈረሰች ( የወደቀ) መንግስት አገር ናት ማለት ነው። አንዳንድ ተንታኞች አብይ አህመድ አስታራቂ በመሆን ስንጥቁን ለመድፈን ይሞክራል - ገድል እንደ ሰራም ይደሰኮርበታል ይላሉ። እኔ ግን እላለሁ ቢጠገንም ሊሆን የሚችል አይደለም - ብዙ እርቀት አያስከድም። የፈራረሰ ጉዳይ ነው። ስለዚህ አገር ወይም ህዝብ ምን ከወድሁ ምን ማድረግ ይጠበቅበታል? ህዝብ የሞራል እና የስነ-ምግባር ልዕልና ሊኖረው ይጠበቃል እንደዚህ ባለ የውደቀት ዘመን። ይህም ማለት ሰው ሁኖ እንደ ሰው ማስብ እና ማድረግ። ከግፍ እና ከብቀላ መራቅ። ጎረቤት ጎረቤቱን ማስዘረፍ እና መዝረፍ ሳይሆም ጎሳ እና ሃይማኖት ሳይለይ የጎረቤቱ ጠባቂ መሆን። የጠፋውን ክቡር ኢትዮጵያዊን ባህል እና ምግባር ፈልጎ ማላማት። እውነተኛውን አቀንቃኝ ከሀሰተኛው መለየት። ህዝብ የለውጥ መሪ እንጅ ተሳፋሪ መሆን የለበትም። ሳያስብ ሳያጤን ሙሴ እያለ የደም ባህር ውስጥ የሚያሰጥምው ሳይሆን እራሱ የለውጡ ባለቤት መሆን አለበት። ለውጥ ይመጣል - አይቀሬ ነው፡ በሞራል እና ስነ ምግባር ግን ዝግጁ መሆን የግድ ይላል። ከመንጋ አስተሳሰብ መፋታት ለመኖር ግደታ መስፈርት ነው።

Re: የብአደን (አዴፓ) አገራችሁን አድኑ ጩኸት ለማን እና ከነማን ነው?

Posted: 23 Feb 2023, 12:03
by Abere
በዚህ የቀውስ ስርዐት ውስጥ ኢትዮጵያዊያኖች እጃቸውን አጣምረው በመቀመጥ ተመልካች መሆን አይጠበቅባቸውም። ይህ የተመልካችነት ባህል በርካታ ዕድሎችን አምክኖ ያስቀረ ነው። ይህን የንቃተ ህሌና ስንፈት በመተው የአገራቸንን ዕጣ እራሳችን ወሳኝ መሆን አለብን። መልካም አጋጣሚዎች እንደ ንጋት ጸሀይ ደግመው ደግመው አይውጡም - እንደ መጡ መጠቀም ብቻ። እነዚህ አጋጣሚዎች ዝምን ብለውም በዘፈቀደ አይመጡም - በበርካታ የመስዋእትነት ዋጋ ነው። ታዲያ ያተረፈውን ገንዘብ ሿብትን የሚያደርግ ምን አይነት ከንቱ ነው? ባለፉት 4 አመታት እና አሁን የምናየው ስቃይ እና ቀውስ የመጣው የተገኘውን ለውጥ ለቀጣፊ እና አስመሳዮች ሿብትን ተደርጎ ወይም ማጅራት በመመታቱ ነው።

ስለሆነም አገራችን ከገባችበት የጎሳ ፓለቲካ ቅርቃር ማውጣት የሁሉም ዜጋ ግደታ ነው።እራሱን ኦሮሙማ ብሎ የሚጠራው እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን ደግሞ የ2ኛ ወይም የ3ኛ ደረጃ ዜግነት የሚሰጥ የኋላቀር ድርጅትን ማስወገድ እንደ ዜጋ ለመኖር የግደታ ነው። ህዝብ አስር ጊዜ እየተቋጠረ የሚፈታው ለኦሮሙማ ሲባል ብቻ ነው - በጣም ኢ-ፍትሃዊ ብቻ ሳይሆን እጅግ ጸያፍ። ለምሳሌ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ እንመልከት። የደቡብ ኢትዮጵያ ዜጋዎች በቁጥር ብዙ ናቸው - በአገሪቱ በህዝብ ብዛት 3ኛ ይሆናል። ይህ ክልል ለኦሮሙማ ሲባል ብቻ ከአንዱ ጆንያ ወደ ሌላው ጆንያ ይገለበጣል - የመጨረሻ ግቡ ግን ግልጽ ነው። ታዲያ ከዚህ ክልል ለምሳሌ አንድ የጋሞ ጎሳ ወይም ወላይታ እንደት አድርጎ ነው እንደ ኦሮሙማዎች 1ኛ ደረጃ ዜግነት አለኝ ማለት የሚችለው? በፍጹም መጀመርያ ዝቅ አድርገው አናሳ ጎሳ አደረጉት፤ ቀጥለው ወደ ዞን ወይም ክልል አወረዱት ከዚያ በመጨረሻ የአገሪቱ 3ኛ ዜጋ ሆነ ማለት ነው። ይህ ስርዐት መጥፋት አለበት። ያለምንም አይነት ኮተት (criteria) አንድ ጋሞ ወይም ወላይት በዜግነት ብቻ ከሌላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እኩል ሊሆን የሚያስችል የርዕዮት አለም ስርዐት አገራችን የምተፈልገው። አንዱ አንገቱን ደፍቶ ሌላው ደግሞ 1ቁጥር ዜጋ ሊሆን አይገባም።

Re: የብአደን (አዴፓ) አገራችሁን አድኑ ጩኸት ለማን እና ከነማን ነው?

Posted: 23 Feb 2023, 12:37
by Za-Ilmaknun
That was a call to save the motherland. OLF seems to have pulled the last card and putting every possible means to realize the greater Oromia project. ADP seems to not only be tired of the bullies but also clearly seeing the danger that is directed at the leadership from all corners. Abiy Ahmed is now rejected by all camps other than those who are using him as an opportunity to further their own agenda, and ultimately bring him down once they achieve their immediate objectives. In a short five years of time, the emperor's new clothes are now public and more is in the offing... :mrgreen:

Re: የብአደን (አዴፓ) አገራችሁን አድኑ ጩኸት ለማን እና ከነማን ነው?

Posted: 23 Feb 2023, 14:56
by Axumezana
ለአለፉት፥ አምስት፥ አመታት፥ ለምን፥ አልጮሁም? ያሁኑ፥ ልቅሶ፥ ከኢሳያስና፥ ከነአምን፥ ዘለቀ፥ሰፈር፥ የታዘዘ፥የድረሱልን፥ ጩኽት፥ ነው።
አብይ፥ ከወያኔ፥ ጋር፥ በመታረቁ፥ የተነሳ፥ አቧራ፥ ነው።

Re: የብአደን (አዴፓ) አገራችሁን አድኑ ጩኸት ለማን እና ከነማን ነው?

Posted: 23 Feb 2023, 17:11
by Abere
I think that should not be holding them back. It all depends on God's perfect time. That could be the reason.
I guess the painful tribal era imposed by TPLF/OLF is over. Everything happens according to God's calendar. When God calls to save you, you shall tune to that call.

Axumezana wrote:
23 Feb 2023, 14:56
ለአለፉት፥ አምስት፥ አመታት፥ ለምን፥ አልጮሁም? ያሁኑ፥ ልቅሶ፥ ከኢሳያስና፥ ከነአምን፥ ዘለቀ፥ሰፈር፥ የታዘዘ፥የድረሱልን፥ ጩኽት፥ ነው።
አብይ፥ ከወያኔ፥ ጋር፥ በመታረቁ፥ የተነሳ፥ አቧራ፥ ነው።